Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Breaking News

Published Posted on by | By TZTA News

ቃለ መጠይቅ

አቶ ብርሃኑ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴረሽን በሰሜን አሜሪካ የሕዝብ ግንኙንት ሲሆኑ 30ኛው የስፖርትና ባህል ዝግጅት በጁን 30 ቀን 2013 ዓ.ም. እስክ ሃምለ 6 ቀን 2013  በሜር ላንድ አሜሪካ ይካሄዳል። አቶ ዮሐንስ ክናዳን ውክለው በፈድሬሽን ውስጥ እያገለገሉ ይገኛሉ። ስለሆነም በይበልጥ ለዚህ ትላቅ ክብር ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው ነበር እነሆ።

ትዝታ   
ስለ ራስህ ለአንባቢያን ብትገልጽልኝ?

አቶ ዮሐንስ 
ስሜ ዮሐንስ ብርሃኑ ይባላል፣ የቶሮንቶ ልጅ ነኝ፣  በቶሮንቶ ሳገለግል ቆይቼ ለፌዴሬሽኑ ማሟዋላት ያለብኝን ነገሮች አሟልቼ ካመለከትኩ በኋላ ለህዝብ ግንኙንት ተወዳደርኩ። ከዚያም አሁን ለኢትዮጵያ ፌዴሬሽን በኖርዝ አሜሪካን ለሚገኘው እያገለገልኩ እገኛለሁ።

ትዝታ 
የኢትዮጵያ እስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ መቼ ተቋቋመ ዋና አላማውስ ምንድነው?

አቶ ዮሐንስ 
የኢትዮጵያ እስፖርት ፌዴሬሽን በ1984 ዓ.ም.  በዊስተን ከተማ ተቆቆመ። ሶስት አራት ቡድኖች በመሆን ማንነታቸውን ዜግነታቸውን በማሳወቅና ባካባቢ ላለው ሰው በማሳወቅና ኢትዮጵያውያን ለመዝናኛና ያገራቸውን ናፍቆት የሚወጡበት እንዲሆን ሆኖአል እና ይሄ ነገር እየቀጠለ በመሄዱ ይሄው ለሰላሳ አመት በቅቶአል።

ትዝታ
እስኪ አመጣጡን ታሪኩን  ባጭእሩ  ብትገልጽልኝ?

አቶ ዮሐንስ
እውነት ለመናገር በሰላሳ አመት ውስጥ እንደዚህ አይነት ደረጃ ላይ መድረሱ ያሰራርና ያላማ ጉዳይ ነው። አላማ ስንል ኢትዮጵያዊነትን በዘር በሐይማኖት በጎሳ በፖለቲካ ሳይከፈል በአንድነት በቃ በዛች ብቻ ተጨዋቾቹ ባንዲራቸውን ይዘው በስሜትና በወኔ አገራቸውን ኢትዮጵያን በማሰብ ነው የሚጫወቱት ያ ደግሞ በትክክል ሃላፊነትን ወስደው እንዲጫወቱ ሆኖአል። ኮሚኒቲ ውስጥ ገብተው በትክክለኛው ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት ግንዘብ ያዥ በማድረግ አዋቅረውት በአሜሪካ መንግስት ስር ደግሞ ተመዝግቦ ስራው እንዲሰራ ተደርጎ ነው እና እነዚህ ሰዎች በየአመቱ በየከተማው ሄደን ይሔንን ነገር አድርገን ገንዘባችንን ሴቭ እናደርጋለን በማለት ነው። ለዚህም ደግሞ ማስረዳት የምፈልገው የቶሮንቶ ቡድን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በሚያስገርም ሁኔታ እየተራመድ ይገኛል። እንደነ አቶ ሽመልስ በፕሬዝዳንት በጸሐፊነት ብዙ የቶሮንቶ ሰዎች ሰርተዋል እንደዚህ ስኬታማ እንዲሆን ያደርጉት ብዙዉን የቶሮንቶ ሰዎች ናቸው ተወካዮችም አሉ።

ትዝታ
በዚህ በሰላሳ ዓመት ጊዜ ውስጥ የጋጠሙ ችግሮችን ብትነግረኝ?

አቶ ዮሐንስ
እስካሁን ድረስ መቸም ትልቁና ዋናው ችግር ያለፈው አመት የተፈጠርው ጉዳይ ነው። ከዛ በፊትም በክብር እንግዳ ከፖለቲካው ተሳታፊዎች ውስጥ የምንጋብዛቸው ሰዎች ጉዳይ ነው። ለምሳሌ እንደ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳን በጋበዝንበት ጊዜ ችግር ነበር። ከዛ በፊትም እንዲሁ፣ ግን ዋናው ትልቁ ችግር የሆነው ፌዴሬሽኑ ቡርቱካንን እንደግዳ እንድትሆን ባቀረበበት ጊዜ ችግሩ እሱ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ፕሮሲጀር ለብዙ ጊዜ ሲሰራበት የነበረውን መተዳደሪያ ደንብ ባግባቡ ባለመያዙ በወቅቱ የነበሩት ሰዎች የፌዴሬሽኑ ዋነኛ አላማ ሳይሆን በእስፖንሰር በኩል በሚመጣው ጥቅም የበለጠ ፌዴሬሽኑ የቆመለትን ዋነኛ አላማ ተዘንግቶ ወደጎን ነበር የሚኬደው። አሁን ብርቱካን ስትመጣ የብርቱካን ምክንያት አይደለም፣ ፕሮሲጀሩ አይደልም፣ ጋዜጠኞችም ሲሉ የነበረው እኛ ማንም ይምጣ ማንም ይምጣ ያ አይደለም ችግሩ ቡርቱካን ሜዴቅሳ ባትመጣም የሚሉ አሉ! ፕሮሲጀሩን አለ አይደልም ወይ? ጥያቄው እሱ ነበረ አሁን እሱን መጠየቅ ስለጀመርን፣ ፌዴሬሽኑ በግልጽ ለህዝብ መታየት ጀመረ። እቢ ያሉ የፌዴሬሽኑ ሰዎች በቃ እኛ በእንደዚህ አይነት መንገድ አንቀጥልም ወቀሳ እየመጣብን ነው ፌዴሬሽናችንን ልናጣ ነው ማስተካከል አለብን ብለው የተነሱ ሰዎች ናቸው ለውጥን ያመጡት።

ትዝታ
ታድያ እዚህ ላይ ምን መፍትሄ ተደረገ?

አቶ ዮሐንስ
መፍትሄ የተደርገው ፊትለፊት ውይይት ተብሎ በቶሮንቶ ቲም ነው የተጠቆመው፣ ባይግርምህ የቶሮንቶ ቲም ያው የቶሮንቶ ጋዜጠኛ ስለሆንክ ነው የምነግርህ ከማናቸውም ባላነሰ ሁኔታ ለፌዴሬሽኑ የሚሟገት ቡድን ነው። ከመስራችም አካሎች አንዱ ነን ማለት እችላለሁ። የፌዴሬሽኑን የልብ ትርታ የሚጠብቁ የቶሮንቶ ነዋሪዎች በኮሚኒቲ ደረጃ ያሉ ሰዎች በሙሉ ሲሰሙ ይሄ ነገር ካልተስተካከለ በመጥፎ አቅጣጫ ይሄዳል ብለው ነበር። በዚያም ወቅት የቶሮንቶ የስፖርቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ሱራፌል መንግስቱ ፊት ለፊት ውይይት በሚል ስብሰባ እንዲሆን ተደረገ። ያስብሰባ ነውያለውን መሰረታዊ ችግር ፈቶ አዲስ ሰዎች አስመርጦ ከንስቲቲሽኑ ወገናዊ አድርጎ የራሱ አርጎ ስራውን ማካሄድ ነበር እና ያኔ በምንሞክርበት ሰአት በውስጡ ለብዙ አመት ስር ሰደው የተቀመጡ ሰዎች አልዋጥላቸው ብሎ ትልቅ ብጥብጥ ተነስቶ ነበር። እኛም እረጋ ብለን የያዝነው ነገር ትልቁና አገራዊ ጉዳይ ስለሆነ እዚያ የምንራበሽበት ሳይሆን እርቁን ብቻ ፎከስ አድርገን የቻልነውን ችለን ስንሰደብም፣ ሲነነገሩንም፣ ሲጮሁብንም ዝም ብለን እስከ መጨረሻ አድርሰናቸው በመጨረሻ እራሳቸው ጥለው እንዲወጡ አደረግን ማለት ነው። እሱ ብቻ አይደለም ከወጡም ብኋላ በኛው ስም እንደገና ማቋቋም ሞከሩ እኛው እያለን ማለት ነው፤ በኛ ላይ ግን አልሆነም። ለመጀመርያ ጊዜ ዳህላስ ላይ ትልቅ ዝግጅት ነበረ፣ በጣም ነው ደስ ያለን1 ማንነታችንን አሳወቅን፣ በዛን ጊዜ ሕዝብ የሚጠብቀው እውነት ተካፍለዋል ወይ እውነት ብቻቸውን ይችላሉ ወይ እውነት ዝም ብለው ነበር የሚለው ነገር ነበር። እኔ በቦታው ነበርኩና ትልቁ ነገር የታየኝ ምንድነው፣ እኛ እንግዲህ ኢትዮጵያውያኖችን እናምጣ ካልን በመክፈቻው ቀን ይህንን ለህዝብ ማሳየት አለብን ብዬ ተንሳሁ። አንዳንድ ሰዎች ያልገባቸው ነበሩ። አላፊነትም ስለነበረብኝ የራሴን ላይፍ ወደጎን አድርጌ ያላደርኩት ነገር አልነበረም። ሰዎችን በማሰባሰብ ኮሚቲ አቋቋምኩኝ አንዳንድ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን አዘጋጀሁ፣ ያለን በጀት ያን ያህል አልነበርም፣ ሁሉም ጥልውን ሄደዋል። እኛ ለዳላስ ኮሚኒቲ እንዲዘጋጁ ነገርን፣  ይሄ ነገር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንደገና መወለድ እንደሆነ ለተጨዋቾቹ አስረዳን፣ ለኮሚቲዎቹ ሁሉ ተነጋገርን የእግዚአብሄር ነገር ሆኖ ሁሉም ተሳካ። እያንዳንዱ ቲም በትክክለኛው ሰአት ባነራቸውን ያዙ። ባነሩ የተሰራው እዚህ ቶሮንቶ ነው። ያንንም ያደረግንበት ምክንያት ባለፈው ጊዜ ባነሩን ይዘውብን ሄዱ። በህጉ መሰረት የኛን ሎጎ የኛን ባነር መጠቀም አይችሉም ግን የኛን መውደቅና የኛ መፈረካከስ ወደ ኋላ በመተው ተሰብስበን ሜዳ ውስጥ ስለገባን ከተለያየ ቦታ መምጣታችንን  ማንነታችንን ለሕዝብ አሳየን። ሕዝብ ያንን አየ፣ ይገርምሃል ዳህላስ ላይ ተጫዋቾቹ በሰልፍ፣ ወደ ሜዳው ገቡ። ፌዴሬሽኑ ሜዳው ላይ “አልሰጥም አለ” እያሉ ሲጨፍሩ የማያለቅስና የማይደሰት ሰው አልነበረም። ይሄ እንግዲህ ያመጣው ምንድነው ፌዴሬሽኑ ሰውብቻ ወይም እንሰሳ ብቻ አይደለም ሕይወት ያለው ሰዎችም አንድ ቦታ ተሰብስበው ሲሰሩ ባንድ ላይ ሕይወትን የመሰለ ነገር ይፈጥራሉ በአንድነት እዚያ ሜዳላይ ይታይ የነበረው ትልቅ ደስታ ትልቅ ያልኩህ ምንድነው ተጨዋቾቹ እየጨፈሩ ደግሞ መጨረሻ ላይ ፈርስ አዘጋጅተን ነበረ፣ ሚኒሊክን የመሰለ ባንዲራ ይዞ እየጋለበ በሚገባበት ጊዜ ያኔ ፌዴሬሽኑ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሰረቱን ጥሎ ጀመረ ማለት ነው። ይሄው ከዛ በኋላ ያደረግናቸው ነገሮች ሰባቱን ቀን በሙሉ ሰዎች እየተጋፉ የሚገቡበት ወቅት ነበር። በተለይ የኢትዮጵያን ቀን በምናከብርበት ጊዜ ካሰር ሺህ ሰው ያላነሰ የመጣበት፣ የተሳተፈበት፣ ቤቱ የተናጋበት ሁኔታነው የተፈጠረው። ያመጣናቸው ዘፋኞች የሚገርምህ ነገር በፖለቲካውም በምኑም ችግር ነበረ፣ ግን እነዚህ የቁርጥ ቀን ልጆች የምላቸው እንደነ ጋሽ መሃሙድ የኢትዮጵያን አንድነትን እፈልጋለሁና መስራት አለብኝ የሚል መጥቼ አገለግላለሁ የሚል መቶ ባንዲራውን እያውለበለበ እኛ መሃል ነው የገባው። እና ያ ሁሉ ሰው ስላደረገው የሚሆን አይመስለኝም የኢትዮጵያ አምላክ ነው ማለት እችላለሁ። እኛ አቅም ኖሮን አይደለም ያደርግነው፣ ነገር ግን ቅን ነገር የምታደርግ ከሆነና ለሰው ልጅ ህልውና ለምታደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመለከታል ያልነው። የተፈጠረው የልባዊ ደስታ ነው የሰጠኝ አሁን እንግዲህ ሰላሳኛ አመቱ ነው።

ትዝታትዝታ
እስኪ በጣም የምታደንቀው ነገር ምንድነው ?

አቶ ዮሐንስ
እኔ በጣም የማደንቀው የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ያላቸው ሰዎች የሚያሳዩትና የሚያደርጉት ሁኔታ ምንም ገንዘብ ለማያገኙበት ነገር የፕሌን ትኬታቸውን ከፍለው ከቤተሰቦቸቸው እርቀው ከጠዋት እስከ ማታ የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሰው እያገለገሉ ይገኛሉ። እስከአሁን ሰልቸን ደከመን እያሉ ሳይሉ በቅንነት ይህን ፈደሬሽን የሚያገለግሉ አሉ።  መመስገን አለባቸው። ለምሳሌ ፋንፍራንሲስኮም አቶ ሽመልስም አሉ ከድሮ ጀምሮ አስካሁን ድረስ ስራ እያላቸው በትልቅ ደረጃ ቲማችንን  እና ቦርዳችንን ይዘው ለፌዴሬሽኑ የሚያስፈልገውን በህግ ደረጃ ለምሳሌ ገንዘብ በሚያስፈልግበት ጊዜ ጠበቃ በነፃ ሌላም ሌላም። ፕሬዝዳንታችን በአሁን ጊዜ ያለው በፋንያንስ ውስጥ ከጠዋት እስከማታ እየሰሩ ነው ያሉት። አቶ ደሳለኝ የቴክሳሱ እንደዚሁ ባለፈው አመት አንድ ሳምንት ነበር የቀረን ምንም ሜዳ አልነበረንም በሳምንት ውስጥ ሜዳ አገኙ ይህን ያደርጉ አቶ ደሳለኝ ናቸው። አቶ ደሳለኝ ናቸው የዳህላስ ነዋሪ ቲም አላቸው። እራሳቸው የፌዴሬሽኑ መዝገብ ሁሉ ሬስቶራንታቸው እዚያ በቦክስ ተቀምጦ አንድ ነገር ስንፋልግ በቃ እዚያ ተኬዶ ነው የምንወስደው እንደነዚህ አይነት ሰዎች አሉ ለማለት ነው። አሁን ደግሞ ሌላው እዚህ ቶሮንቶ ውስጥ አቶ ሽመልስ አሉ ፌዴሬሽኑ መሰረታዊ ለውጥ እንዲያመጣ የራሱ አካውንት እንዲኖረው ለምሳሌ ቶሮንቶ ላይ በተደረገ ጊዜ ገንዘብ ያዥ የነበሩት የቶሮንቶ ሰዎች ናቸው። ቶሮንቶ እውነት ለመናገር ከሚያስደስተኝ አንዱ የቶሮንቶ ቡድን ኖርዝ አሜሪካ አዘጋጅ መባል ይችላል። ቶሮንቶ አንድ ብቻውን ሆኖ ነው ኖርዝ አሜርካ ሊባል የቻለው። እዚያ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ያለውን ችግር ቶሮንቶ ከዲሲ ቀጥሎ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ስለሚኖሩበት ነው እንዲረሳ አልፈልግም። እኔም ባብዛኛው የምገልጽው ሃይሉ ያለው ሚዛኑ ባብዛኛው በቤተክርስትያንም ሲታይ በብዙ ቦታ ሲታይ የተደራጀን ሕብረተሰቦች ነን። እዚህ ስለኮሚኒቲ ምንነት ስለአብሮ ማደግ ምንም ጊዜ ቢወስድም የፈለግንበት ቦታ ባንደርስም ግን እናውቃለን። እደሌላው የውስጥ ከተማዎች በጥቂት እንደሚኖሩት አይደለንም ቶሮንቶ ያደረገው አሰዋጽዎ በሃይል ያስደስተኛል።

ትዝታትዝታ
በቅርቡ ከጁን ሰላሳ እስከ ጁላይ ስድስት ይካሄዳል ተብሏል ለአንባብያን ብትገልጽልኝ?

አቶ ዮሐንስ
ስለዝግጅቱ እንግዲህ ዋናው አንባቢያን እንዲያውቁ የምፈልገው ምንድ ነው የስላሳ አመት ውጤት ምንን ይመስላል በቢዝነስም ሆነ አብሮ በመስራትም ሆነ የት ደረስን የሚለው የሚታይበት ነው የሚሆነው። ሰላሳ እመት ቀላል ጊዜ አይደለም። ስላሳ አመት ስናከብር ባሁኑ ሰአት ምን እያደረግን ነው ያለነው? የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ ወደ ሶስት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ ሜዳ ነው። ትንሽ ሜዳ መከራየት እንችል ነበር። እንደ ድሮ ትልልቅ እስፖሰሮች የሉንም። ግን ያንን ሁሉ አድርገን በተስተካከለ ሁኔታ እዚያ አካባቢ እስከ መቶ ሺ የሚገመት አለ። የሚባልበት ቦታ ከሌላም ቦታ ሰው ስለሚመጣ የተወሰንች ቦታ ሀይ እስኩል ውስጥ ዝም ብለን ብናደርገው ለኛ ለኢትዮጵያውያን ስንት አመት ስንት ጀነሬሽን አሜሪካን በተለይ ዲሲ  ይመጥነናል ወይ ለኛ ሕብረተሰብ  የዩኒቨርስቲ ሜዳ ለኛ አይገባንም ወይ ኢትዮጵያን አሜሪካን ሌላው ሕብረተሰ ብቻ የሚጠቀምበት ለምንድነው ሌላው የመንግስትን ሰዎች ማነጋገር ያቅተናል ወይ? አብረን መስራት ያቅተናል ወይ? እኛ አሚሪካ ለጆቻችንስ አሜሪካ አይደሉም ወይ? ከተማውስ የኛ አይደለም ወይ? ይሄነው እንግዲህ ሰላሳ አመት ውስጥ መቆየትና አብሮ የመስራቱና ከቢዝነስ ሴንተሮችን አንድላይ አምጥቶ ሀይቅ የሆነ እስቴዲየም ውስጥ ማዘጋጀቱ ሰዉን ማሰባሰቡ ይሄንን ነው አንባቢያን ማውቅ አለባቸው ብዬ የማምነው ይሄንን ነገር አድርገን  ለሚመጣው ሕዝብ መልዕክቱ ምን ይሆናል? ኢትዮጵያውያን መጡ ተሰባሰቡ ሲባል ድልነው የሚሆነው። እኛ ባሁኑ ሰአት እንደ እስፖርተኛም ይሁን እንደኢትዮጵያዊነት ብዙ አንገብጋቢ ጉዳዮች አሉ ግን አንደኛውን ብለን የመረጥነው የኢትዮጵያን ሴቶች በተለይ በዚህ በአረብ አገር ውስጥ አሲድ እየፈሰሰባቸው፣ የፈላውሃ ዘይት እያደረጉ፣ እሬፕ እያተደረጉ፣ ከፎቅ እየተጣሉ፣ በመኪና እየተገጩ፣ በየቦታው እየሞቱ፣ እሬሳቸውን እንኳን የሚወስድ የለም ይህ ያሳሰበናል። ሁል ቀን የሚቆጨን ስለሆነ ይሄ ነገር የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፣ እህቶቻችን ናቸው፣ ለምን እዚህ ቦታ ደረሱ? ለምን ይሆናሉ የሚለው ጥያቄ እኛም እንደስፖርተኛ ሚስትም ልጆችም እናትም አባትም አሉን እና ይሄንን ነገር ለህዝቡ ባግባቡ መልዕክቱ እንዲደርስና ይሄንን የሚመለከቱ የሴቶች ማህበር ለኢትዮጵያ ሴቶች ተሟጋች የሆነ ድርጅትን አብረን እንድንሰራ አርገን እንዲያውም ከምናገኘው ገንዘብ በተወሰነ ደረጃ ወደዚሁ ድርጅት ሄዶ ሴቶችን እንዲረዳ ለማድረግና ሌሎችም የሴቶች ግሩፖች መልዕክታቸውን አስተካክለው ይሄንን መሰረታዊ የሆነ ችግር ለመቅረፍና እንዳለ የሰላሳኛ አመቱ ዋናው መልዕክት ነው። ለዚሁ ጉዳይ ሰውም እንዲገገነዘብ እናደርጋለኝ። በሌላ በኩል ደግሞ የትዝታ አንባቢያን ከቻሉ ዝግጅትም አያስፈልገውም ትንሽ ጊዜ ነው የሚወስደው፣ ዘጠኝ ሰአት ድራይቭ አድርጎ ከውንድሞቻችን ጋር ተቀላቅሉ ይሄነው የሰላሳ አመት ዋና ዋና ጉዳዮች ማለት።

ትዝታ ለመሆኑ ይሄ በጉጉት የሚጠበቅ በአል ወደዛ ለመጝዝ የሚፈልግ ግለሰብ ካለ ምን ሐሳብ ትሰጣለህ ማለትም ከቶሮንቶ?

አቶ ዮሐንስ
በተለይ በቶሮንቶ አካባቢ ተጫዋቾቻችን አንድ አራት አምስት ሆኖ ትኬት ቆርጦ በአይሮፕላን ከመሄድ የአራት መቶ የአምስት መቶ መኪና ተከራይቶ ዲሲ መሄድ ይቻላል። እዚያ ከተደረሰ በኋላ በቅናሽ መቶ ሃምሳ ወም ዶላር መቶ ዶላር የሚያወጡ ሆቴሎች በሰመሩ በሰማኒያዶላር  በዘጠና ዶላር አዘጋጅተናል። ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ሌሎች እየፈለግን ነው እዚያም እየሞላ ነውና ሳምንቱን በሙሉ መቀመጥ የሚችል ሰው ካለ ከመጀመሪያው ጁን 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቢመጣ ጥሩ ነው። ግን ሳምንቱን መቀመጥ የማይችል ሰው ከሃሙስ ጀምሮ አርብ ቅዳሜን ጨምሮ ቢሆን ጥሩ ነው። ዘመዶቹን በነፃ ያገኛል ምክንያቱም አርብ ቅዳሜ አሜሪካ ብሔራዊ እርፍት ቀን ነው። በአል ስለሆነ ተደስቶ የማይመጣ ሰው የለም። ስማቸው የገነነ ትልልቅ ዘፋኞች ሁሉ በዚያ እለት ከሮብ ሃሙስ ቅዳሜ ጨምሮ ዝግጅት አለ። በተፈለገው መልኩ እያንዳንዱ ሬስቶራንት ያላመጣው ዘፋኝ የለም፣ እያንዳዱ ቦታ መዝናኛ አለ፣ ሁሉ ቦታ የተዘጋጀ ነው ያለውና ከዚህ የሚሄደው ሰው እውነት ለመናገር በጣም ይደሰታል። ባለፈው ጊዜ እንጀራ ሁሉ አልቆ ነበር ብዙ ማሰብ አያስፈልግም። እሮብ ማታ ወይም ሃሙስ ማታ ተነስተው አንድ ላይ ሆኖ ሄዶ ሆቴል ተቀምጦ ይህን የመሰለ በዓል እንዳያመልጣችሁ። በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያዊ ስንል አደጋ ላይ ነን ያለነው፣ ለምን እኛ አባቶቻችን ባሳለፉልን ስም እስከዛሬ ኖረናል አሁን ደግሞ የኛ ፋንታ ነው። እች ኢትዮጵያ የምትለዋን አገር ወደፊት ለማስኬድ በዘር እየተደራጁ እኛ በምናዘጋጀው እለት ሊበግሩን አይችሉም። እኛ እነዚያ ሰዎች ለምን ሄዱ አይደለም የምንለው እኛ ኢትዮጵያዊነትን አላስተማርንም ለዚህነው የሄዱት አሁንም ወደኢትዮጵያዊነታቸው ተመልሰው ይመጣሉ። እኛ አሁን እየደከመን በምንመጣበት ጊዜ እኛ ልጆቻችንን እኛ ጨርቃችንን ብለን በምንቀርበት ጊዜ ሌላው ዘር እያየ በሚመጣበት ጊዜ ያች የምንወዳት አገር ታሪክ ያላት እየመነመነች እየኮሰሰች ትመጣለች፣ ልንጠግነው የማንችለው ደረጃ ልንደርስ እንችላለን። ይህን የምናገረው ለማስፈራራት አይደለም ሌሎች እንዲህ ሳያደርጉ ተበትነው የቀሩ አሉ። ሆምርካችን ምንድነው መሆን ያለበት እንደዚህ የኢትዮአጵያ ቸርች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሙስሊሙ ኮሚኒቲ ብለው ያቋቋሙትን ስፖርት የማድረግ ሐላፊነት አለብን። እኛ እናቀርባለን ዝግጅቱን ሆቴሎች እናቀርባለን መተው ካላዩልን ምንድነው የምናደርገው የቶሮንቶ ህዝብ አራት አምስት ሰው ሆኖ መኪና ተከራይቶ ዲሲ ድረስ መሄድ ነው በሰማኒያ ብር ሆቴል ተከራይቶ ከአራት ቀን በሁዋላ መመለስ ነው አንደኛ ደስታ ነው ሁለተኛ ኢትዮጵያዊነትንም አድሶ ሶስተኛም ለፌዴሬሽኑም ለሚቀጥለው ሰላሳና አርባ አመት ቀጣይነት እንዲኖረው አድርጎ መምጣት ይቻላል ማለት ነው።

ትዝታ
ለዚህ ለዘንድሮው እንግዳ ሆኖ የሚመጡ እነማን ናቸው?

አቶ ዮሐንስ 
የክብር እንግዳ እንግዲህ ባለፈው ብዙ ሞክረን ነበር፤ አረፈ አይኔን ብለናል ባለፈው አመት በቪዛ ምክንያት መምጣት አልቻሉም። ግን በኦሎፒክ ሶስቱ ሴቶች በሩጫ ወርቅ ያሸነፉትን ጡሩነሽ ዲባባን፣ መሰረት ደፋርን ሌላዋን እንሱን ጋብዘናል። እንደማስበው የፕሮግራም መቃወስ ሳይኖር አይቀርም ምናልባት ላይመጡ ይችሉ ይሆናል የኢትዮጵያ እስፖርት ፌዴሬሽን የኢትዮጵያን እግርኳስ ኢትዮጵያ ያለውን አሰልጣኝ ልከን ነበር ግን በጁን አስራ ሰባት አስራ ስምንት እንደገና አሁን ባለፈው ቦስዋናን አሸንፈናል አሁን እንደገና ከሳውዝ አፍሪካ ወሳኝ ጨዋታ አለ እና ለዛም እየተዘጋጁ ስለሆነ መምጣት እንደማይችሉ ደውለውልናል እና እነዚህ ናቸው። እንግዶቻችን ሌሎችም በቦስተን አካባቢ ለብዙ አመት በቡድን ውስጥ በፌዴሬሽን ውስጥ ያገለገሉ የነበሩትን ከራሳችን አቶ መለሰን የክብር እንግዳ አድርገናል ማለት ነው።

ትዝታ
ቅድም ጠቀስ አርገኽዋል ወጣት ሰቶች ወጣት ውዶችም አሉ መሰለኝ ላንባቢያን ምንትላለህ?

አቶ ዮሐንስ
አዎ ሴቶች አሉ እንዲያውም የሴቶች ቡድን ሲጫወቱ ይገርምሃል ህዝቡ ልክ እንደአለም ዋንጫ ነው የሚያየው። በቶሮንቶ አካባቢ ሞክሬ ነበር ሁለት ጊዜ እኔ ጸሐፊ በነበርኩበት ጊዜ ለማቋቋም ቶሮንቶን ወክለው እንዲሄዱ መክሬ ነበር፣ በዚህ አጋጣሚ የቶሮንቶ ሴቶች ይህን የሚሰሙ ካሉ መጓዝ የሚፈልጉ እና ሰባትና ስምንት እንኳን ከደረሱ ማለት ብዛታቸው ሌላውን ከዛው መጨመር ይቻላልና ካለው ቲም ጋር ሆኖ በመስራት አንዳንድ ነገሮችን ተሸፍኖ የሚኬድበትን ሁኔታ፣ የሆቴሉን አውቃለሁ ይቻላል፣ አሁን ያንን ካልኩ በኋላ ባሁኑ ጊዜ ከፊላደልፊያም ከሌላም ሕጽናትና ሴቶች ይዘው የሚመጡ አሉና አምስት ስድስት ብድኖች አሉ እንዚህ ቡድኖች በት/ቤት ውስጥ እግር ኳስ የሚጫወቱ ናቸውና የነሱም ዝግጅት አለ።

ትዝታ
የቶሮንቶ በሰሜን አሜሪካ እስፖርት ምን ያህል ዝግጅት አድርጓል ብለው ይገምታሉ?

አቶ ዮሐንስ
የቶሮንቶ ቡድን ባለፈው አመት ታሪክ ሰርቶ ነው የመጣው ዳኽላስ ላይ አትላንታ ላይ ካመት በፊት በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት በቂ ዝግጅት ባለማድረጉ ወደሰከንድ ዲቪዥን ወርደን ነበር፣ ዳኽላስ ላይ ግን ያ ቁጭቱ ስለነበር የቡድኑ ተጨዋቾችም ሆኑ አመራሩ ፌዴሬሽኑ ሁሉም ነገር ብዙዉን ለሁለት ከፍሎ ስለነበረ ያ እኛ ላይ ተንጽባርቆ ነበረ፣ በኋላ ግን ያ ሁሉ አልፎ መፍትሔ ከተገኘ በኋላ በፖለቲካ በዘር ሳንከፋፈል አንድ ላይ ሆነን አምጥተነው ዳህላስ ሄድን ማለት ነው። አንደኛ  የወጣነው፣ አሁን ዲሲ ላይ ስንሄድ የመጀመሪያ ዲቪዥን ሆነን ነው የገባነው፣ የትልቁም ዋንጫ ባለቤት መሆን እንችላለን ማለት ነው። የንን የዳህላስ አሰላለፋችንን ያዩ የዋንጫ ተሻሚዎች እንሆናለን ነው የሚሉት እና ጥሩ ቻንስ አለን የማሸነፍ መሰናዶ የሚያደርገው ደግሞ ጥሩ ዜና ይዘን ወደቶሮንቶ እንመጣለን ነው የምለው።

ትዝታ
ለመሆኑ ወደ ቶሮንቶ የሚመጣውና ግጥሚያ የሚደረገው  መቼ ነው? በሰላሳ አመት ውስጥ ስንት ጊዜ መጣ?

አቶ ዮሐንስ
ወደ ቶሮንቶ የመጣው ሁለት ጊዜ ነው። ባልሳሳት ጥሩ ቻንስ የነበርን አትላንታ ላይ የተደረገ ጊዜ ነው። ዘመቻ አድርገን ነበረ ያትላንታው ወደዚህ እንዲሆን፣ ዋንኛው ትልቁ ችግር የፌዴሬሽኑ በሕጉ ያለመተዳደር ሲሆን ቶሮንቶ ያቀረበው ፓኬጅ ጥሩ ሆኖ ሳለ ሸራተን ሆቴልም ኪንግና ደፍሪን ላይ ያለውን ሜዳን  ኮሚሽኑን አምጥተን ኢትዮጵያን ኮሚኒቲን አምጥተን ሬስቶራንቶችን ሁሉ አሰባስበን የቱሪዝም ኮሚሽኑ ተቀብሎ ሸራተን ሆቴል ላይ በኢትዮጵያ ባንዲራ በጥሩ መስተንግዶ ተደርጎ እናንተ ጋ ነው የሚመጣው ተብሎ ከተንገረን በኋላ ነው፣ ያነገር የተቀየረው፣ ያ ቅድም ከነገርኩህ አንዳንድ አሰራሮች ጋር ተደምሮ ነው እንግዲህ ትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገባው። አሁን ግን መቼ ይመጣል ለሚለው፣ ቶሮንቶ በሜዳ በኩል ችግር አለብን። ሜዳው ውድ ነው። ሌላው በፊት የምናዘጋጅበት ሴኒቲኒያል የሚባለው እኛ በምናዘጋጅበት ጊዜ እነሱም ዝግጅት አላቸው። የሜዳ ጥያቄ ስለሆነ ነው እንጅ የኛ ሕብረተሰብ ቶሮንቶ ውስጥ ያለው ሁልግዜ ቡድኑ ለማምጣት ሁልግዜ ዝግጁ ነው።

ትዝታ
የሜዳው ችግር መፍትሄው ምንድነው ትላለህ ?

አቶ ዮሐንስ
መፍትሄው ምን አለ መሰለሕ፤ ዲሲም ከተማ ነው ሜዳ የለም ትልልቁ ብቻ ነው ያለው። ለዲሲ ከተማ ይሄን ያሕል ገንዘብ ከወጣ ለቶሮንቶ ከተማ ያን ያሕል ውደ መቶ ሽህ ብር አውጥተን የቶሮንቶን ሕዝብ አሰባስበን እንዲመጣ ማድረግ የምንችል ከሆነ ሃያ ብር በር ላይ ብናስከፍል አንድ ሺህ ሰው ቢመጣ ሃያ ሺህ ነው። በቀን የኛ የትርፍ ድርጅቶች አይደለንም፣ እንደምታውቀው ገንዘቡ ባላንስ አውት ካደረገ ይዘነው የመጣነው ገንዘብ ከተመለሰልን ኢትዮጵያውያኖች ከተሰባሰቡልን ያንን ነው የምንፈልገው፣ እንደፌዴሬሽን እንደማስበው የማንችልበት ምክንያት አይኖርም። አሁን ያለው የቶሮንቶ አመራር ለቱ ታውዘንድ አስራ አራት አስራ  ስድስት አስገብቶአል ምናልባት ያንን ካሸነፋ ወደ ቶሮንቶ እንመጣለን ።

ትዝታ
በዚህ ታላቅ በአል ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ይመጣሉ ብለህ ታስባለህ ?

አቶ ዮሐንስ
ዲሲ ላይ ሶስት አራት ጊዜ ተደርጎአል። ቁጥሮቹ አሉ ምን መስለሕ ባለፈው ባንድ ቀን ብቻ ሀያ ሺህ ነው የመጣው አሁንም አርብ እለት ያንን የሚያህል ሰው እንጠብቃለን። በአንድ ቀን ከሰአት በኳስ ጨዋታ እንኳን ሁለት ነው ያለን፣ በኢትዮጵያ ቀን ያን እለት የአገር ልብስህን ለብሰህ፣ ማስንቆ ክራር ከበሮ የቢሄራዊ ትያትር ተጨዋቾ፣ ዳንሴሪዎች የተለያዩ ባሕል ልክ ሕዝብ ለሕዝብ የሚመስል ነው። የምናዘጋጀው ፕሮዳክሽኑ ብቻ ወደ ሰማኒያ ሺህብር የሚወስድ ነው፣ ይህንን የምናደርገው ለምንድነው? ሕዝብን ለመሳብ ልጆቹ እንዲያዩ እች ለኛ ካዲላክ ናት። የሚመጣው ሰው ለኢትዮጵያ ቀን እስከ ስላሳ ሺህ እንጠብቃለን። በየቀኑ ቢያንስ አስር ሺህ እንጠብቃለን። ያለፈው 2008 ዓ.ም. የተወሰነ ችግር ነበረብን እስከ እሮብ ድረስ ሰው አልመጣም ነበር አንዳንድ በስፖንሰር ሽፕ በኩል የተፈጠረ ችግር ነበርና ከሚዲያም ጋር ትንሽ ችግር ነብረብን እና አሁን ምንም ነገር ስለሌለ በዛን ጊዜ እንኳን እስክ  አንድ ነጥብ ሚሊየን ነው ልናስገባ የቻልነው ከትኬቱም ከምናምኑም ወጭውም የዚያን ያህል ነው አሁንም ያንን ያህል ህዝብ አለን በዬ ነው የምጠብቀው።

ትዝታ
ለሚቀጥለው አምስት አመት ይሄ ነገር የት ይደርሳል ብለህ ታስባለህ ?

አቶ ዮሐንስ
መቸም እስካሁን ከጠየከኝ ጥያቄዎች በሙሉ ይሄነው ትልቁ ጥያቄ ለምን ብትለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄ ፌዴሬሽኑ ከስንት አመት ብኋላ ማለት ስድስት አመት ወደ ኋላ ስንመለከት ያሰራሩ ህኔታ ተቀይሮ ነበር፣ ሁልጊዜ ቡካችን ላይ የሚያሳየው ኪሳራ ነበር። ይሄ ነገር በተለይ በዚህ አካባቢ የምንሰራ ሰዎች አሳሰበን። ከዲሲ ጀምሮ እንኳን ብንመለከት ሁለት መቶ ሺህ፣ ችካጎ ላይ ወደ መቶ ሺህ ከስረን ሰባት መቶ ሺህ ብቻ የነበረን ሰዎች ነን።  አካውንታችንን መደበቅ አንችልም። አትላንታ ላይ እንደዚሁ ሁለት መቶ ሺህ ብር ተቀበሉ ተብሎ ከስረን ነው የወጣነው። ይሄ እንዴት ይሆናል በዚህ አይነት አካሄድ ኪሳችን ዜሮ እየሆነ መጣ፣ በዲሲ ሰባት መቶ ሺህ የነበረን ሰዎች መቶ ሃምሳ ሶስት ሺህ ዶላር፣ አትላንታ ላይ ስንደርስ ከስድስት አመት በፊት የት ሄደ ገንዘቡ! የት ገባ! ሰዎች ገንዘብ ይዘው መሄድ አይችሉም። እንደዱሮው አይደለም ግን ዝም ብሎ ስራው በትክክል አይሰራም፣ የመጣነው ይሄ ነገር አባቶቻችን ከዚያ በፊት የጀመሩት እንደነሱ መስራት መጀመር አለብን። ይሄ ዝም ብሎ እስፖንሰር መጣ ከኢትዮጵያ እንደዚህ መጣና እንደዚህ ወረደና አይሆንም። እኛ ስንጀምር ህዝብን ጉያችን አድርገን ነው። የጀመርነው አሁንም በዚያ ነው የምንቀጥለው።  እስፖንሰር ከመጣ በስፖንሰር ሽፕ አድርጎ ሲጨርስ ኮንትራቱን በቃ ይሄ የህዝብ ነው። ዳህላስ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ ትርፍ አመጣን። አሁን እንግዲህ አቅጣጫው ተቀይሮአል ማለት ነው ዲሲ ላይም እንዲሁ ገንዘብ እንሰራለን በእውነት ነው የምለው አምስት አመት በተከታታይ ገንዘብ የሚሰራበት ሁኔታዎች አሉ። አሁን የምንከተለው መንገድ ግን እያንዳንዱ ትራንዛክሽን ፌዴሬሽኑ የሚያደርጋቸው ትራንዛክሽኖች በሙሉ በኮንትራት መልክ ተጽፋው ዘፋኞችን የተለያዩ ነገሮችን እስከ አርባ ሺህ ብር ድራስ ወጭ አለበት። በሰማኒያ ሺህ እንጀምራለን እስከ መቶ አርባ ያህል እናውጣለን፣ እየሰፋ ይሄዳል። ነገሩ እያንዳንዱ የማስፈርማቸው ኮንትራቶች በሙሉ አይድለም የሚላቸው የለም አሁን ግን አንድ ኮንትራት ተፈርሞ ፋይናስ ሄዶ ፋይናንስ ፕሬዥርን ጠይቆ፣ አለን ገንዘቡ ይሄን ሰውዬ የምናስፈርምበት ካረጋግጥን በኋላ እሱነው ሄዶ የሚፈርመው፣ አሁን ይሄ ቁጥጥር ስላለ የሚቀጥለው ስድስት አመት ይህ ፌዴሬሽን እውነት ለመንገር  ትልቅ የሆነ ኦርጋናይዜሽን ነው የሚሆነው። በማሰባሰብ እረገድ በዚህ ላይ ደግሞ ልንገርህ በቴክኖሎጅውም በቀጥታ ነው የምናስተላልፈው እስክሪን እናደርገዋለን ይህንን በሙሉ በነጻ ነው። ለምንድነው እየተስማማን ነው። እነሱም ስለሚጠቀሙ የፌዴሬሽኑም ስራ አለ እንዚህ ሰዎች እኛ ጋ በመስራታቸው ብቻ የታወቁ ይሆናሉ። እኛ የፌዴሬሽኑ ስም ሁሉ በስፖንሰር ሽፕ እየተጠቀምንበት ነው። አሁን በዚህ ሰአት ላይ ዲሲ አሉ የሚባሉ ረስቶራንቶች ቡክሌታችን ላይ አድቨርታይዝመንት አድርገዋል። ገንዘብ እየከፈሉ ማለት ነው ወደሰላሳ የሚሆኑ ይህ ማለት ፌዴሬሽኑ እውነት አንጋፋነቱን እያሳየ ነው ማለት ነው እና እንደዚያ ነው በዚህ አይነት መልክነው እየሄድን ያለነው።

ትዝታ
ከላይ ያልጠቀስኩት ለአንባቢያን የምትለው ነገር ካለ ?

አቶ ዮሐንስ
ለአንባቢያን የምለው ካለ በተለይ በቶሮንቶና አካባቢው ወጣቶቹ የምለው እኔ በእውነት ኮሚኒቲዬን እረዳለሁ አገለግላለሁ ብዬ ስመጣ እዚህ በትልቅ ደርጃ በስንት ሺህ ብር ትልልቅ ሰዎች ጋር እስራለሁ ብዬ አይደለም የገመትኩት ግን ለማናቸውም ወጣት ኳስ ተጫዋቾችም ይሁን ምንም ይሁን መጀመሪያ በጎ አድራጎት ለኮሚኒቲ መስራት ማገልገል መማር አለበት ብዬ ነው የምገምተው፣ ያንን እስካደረገ ድረስ ህብረተሰብን ለመርዳት የሚችልበት ትልቅ መንገድ ይከፈትለታል፤ የሰው ልጅ እንዲሁ ተንስቶ አንድ ደረጃ ልደርስ አይችልም ቀስ በቀስ ነው።

በሁለተኛ ደረጃ ልል የምፋልገው የዚህ ፌዴሬሽን ማንነትና ኽልውና ያስጠበቀው የቶሮንቶ ቡድን ማመስገን እፈልጋለሁ፡ የቶሮንቶን ኮሚኒቲን ማመስገን እፈልጋለሁ። የቶሮንቶ የኮሚኒቲ ፕሬዝዳንቶች ሁሉ እዚህ ስብሰባ ላይ ተካፍሎአል። የቶሮንቶ ኮሚኒቲ ጻሐፊ እዚህ ፌዴሬሺን ውስጥ ተካፍሎአል። ይሄን የሚያደርጉትን ሰዎች የዚህ ፌዴሬሽንን ትልቅነት እዚህ መድረስ ህዝብን ማሰባሰብ አንዳንድ ጊዜ ቁጭ ብዬ ሳስበው በጣም ይገርመኛል። እንዴት ይሄ ነገር ሰው ሁሉ እየተጠራራ የሚመጣው ኢትዮጵያዊነት ነው፣ ይሄ እንዲያመልጠን አያስፈልግም። የቶሮንቶ ወጣቶች በተለይ የቶሮንቶ ሰዎች በሙሉ ያውቃሉ ለኮሚኒታችን ሃያ አምስት ሃይ ስድስት አመት የኖሩ ህጋዊነትን ሚስጥሩን እናውቃለን። ዋናው ትልቁ ነገር የኛ ሰው እንዲረዳ የምፈልገው  አብሮ በስራአቱና አንድላይ መምጣቱ ይሄ ፌዴሬሽን ከነበረበት ችግር የቶሮንቶ ኮሚኒቲም ከነበረበት ችግር እንወጣለን። ያኔ ነግሬሃለሁ መቶ ሺህ ዶላር ድረስ ተከሰናል ህግ ነው እንግዲህ ምን ደርጋለን ግን ያለበትን ችግር ለመናገር ነው የዚህን ፌዴሬሽን የኛ ኮሚኒቲ የቶራንቶው ይሄንን ችግሮች ከተወጣ ትልቅ ፌዴሬሽን ነው። ትልቅ ድርጅት ነው፣ እኔ ከቶሮንቶ በመሆኔ በጣም ነው የምኮራው ለቶሮንቶ ኮሚኒቲዬ አገልግያለሁ፣ የወጣቶቹም ቦታ ተሳትፌአለሁ እንደቶሮንቶ በስብሰባም ሆነ ሰውም በመቀበል ሆነ አብሮ በመስራትም ሆነ ለሃገርም እንደመቆም ካየሁአቸው ሁሉ እንደቶሮንቶ ሕዝብ አይቼ አላውቅም እና ባሁኑሰአት በተለያየ ሁኔታዎች ተሰብስቤአለሁ ቶሮንቶ ላይ የተሰበብኩአቸው ስብሰባዎች ልክ አገርቤት ያለሁ ነው የሚመስለኝ የኢትዮጵያዊነት ያንን አንጣ ነው የምለው።

ትዝታ
በጣም አመሰግናልሁ አቶ ይፕሃንስ።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu