|
የአብዮትና የረሃብ አዙሪት
ክፍል 1 አሥራዳው (ከፈረንሳይ)

መንደርደሪያ:
I. በቀዲማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን፤
*« የምትወደንና የምንወድህ ሕዝባችን ሆይ ! » እየተባለ፤
« አባባ ጃንሆይ የኛ እናት አባት፤
አሳድገውናል በማር በወተት »
« ኃይለሥላሴ ሃዋርያ፤
የሰላም መሪ ባለሞያ »…..ወዘተ እያለ በችጋር ረገፈ፤
በዚህ የተነሳ፤
* « በደልና ጥቃት ለምደህ አልነሳም ካልከኝ፤
ቀሚሴን ልኬያለሁ ሱሪህን ላክልኝ : » የሚለው
የቀድሞ የእተጌ መነን አዳሪ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች የትግል ጥሪ :
* « አትነሳም ወይ! አትነሳም ወይ!፤
የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ ! »
በቃ፤ ተነስ ! በቃ፤ ተነስ !
በሚለው የተማሪዎች ትግል ተጀምሮ እንድያ እንዲያ እያለ፤ በወሎ ድርቅና ረሃብ ታጅቦ፤ አብዮት ፈነዳ፤ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተሰናበቱ፤
II. ወታደር ሥልጣን ያዘ፤
* ያለምንም ደም እንከኗ ይውደም፤
በቀና መንፈስ ኢትዮጵያ ትቅደም፤ ……..ብሎ፤ ወደ
* የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት፤
እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት፤….. በሚለው ተተካ :
ከፎካሪው ዓላማ በተቃረነ መልኩ በመጠቀም ተዜመ፤ …. ከዚያም፤
ዲሞን በዲሞትፈር ! አናርኪስቶች አብዮቱን አይቀብሱም!
አብዮቱ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል !……..ወዘተ እያለ ቆይቶ ሲጨነግፍ በዚያው በጨንጋፋ ማሕጸን ውስጥ፤ ሌላ የአልባኒያ ሶሻሊዝም አቀንቃኝ ተረግዞ፤
III. የወያኔ አብዮት ተወለደ፤
*ከአሁን በኋላ ጠመንጃና መድፍ ተቀጥቅጠው ማረሻ ይሆናሉ! በተባለ ማግስት ሻዕቢያና ወያኔ ሲሰርቁ ሳይሆን፤ ሲካፈሉ ስለተጣሉ በባድመ የጦርነት እልቂት ሆነ፤ ወገኖቻችን እንደ ቅጠል ረገፉ፤ ሃብት ባከነ:: አሁን ማን ይሙት : ምክንያቱ ለኛ የማይነገር ሆኖባቸው እንጂ የበሬ ግንባር በማታክል መሬት ያ ሁለ ወገናችን ከሁለቱም በኩል ማለቅ ነበረበት?
* ከአሁን በኋላ ሕዝቦች በቀን ሦስቴ ይበላል! ተብሎ፤ ሦስቴ ቀርቶ አንደም ጭንቅ ሆኖ አረፈው::
* ከአሁን በኋላ በቆሎ ከራሳችን ተርፎ ወደ ውጪ እንልካለን! በተባለ ማግስት የልመና አቁማዳ ተይዞ በዓለም ዙሪያ ቀፈፋ ተጀመረ::
* የግልገል ጊቤ ግድብ የሃይል አቅርቦታችንን አሟልቶ ወደ ውጪ እንልካለን! ተብሎ ከበሮ በተደለቀ ማግስት ግድቡ ፍርስርስ ተስፋውም ፍርክስክስ አለና ሕዝቡን ጨለማ ወረሰው::
* ከአሁን በኋላ አገሩን በዘይት እናጥለቀልቀዋለን! በተባለ ማግስት፤ ሕዝቦች የኑሮ ዘይት እያዳለጣቸው እንክትክት፤ የሚላስ የሚቀመስ ጥፍት፤ አለ። (በነገራችን ላይ ሕዝቦች የሚለው የነሱ አጠራር የብዙዎች ብዙ በመሆኑ አጸያፊ ሲሆን በሰዋሰዋዊ ብዜት አሕዛብ ነጠላ ሲሆን ሕዝብ ደግሞ ብዙ በመሆኑ ሌላ ብዜት አያሻውም፤ እየተንኳኩ ለማደናቆር ካልሆነ በቀር)
* ስኳር የጠፋው ገበሬው ስኳር መላስ ስለጀመረ ነው! ባለ ማግስት ስኳር ከከተማ እብስ….ወዘተ እረ ስንቱ!!
እሳቸውን አይቶ መለስ ከማለት ይልቅ፤ አይቶ አያልቅበት ብለን ብንጠራቸው በይበልጥ ምግባራቸውንና ሰብዕናቸውን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል ::
* አሁን ደግሞ፤ የአባይ ግድብ ሕዳሴ ይሉናል! ጉድ እኮ ነው: ድሪቶ ተለብሶ አቁማዳ ተሸክሞ እየቀፈፉ ሕዳሴ! « ቂጥ ገልቦ ክንብንብ! » ይሏችኋል ይች ናት:. እስቲ የዓባይን ግድብ በተመለከተ ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ፤
1. ለምን የአምስት ዓመት የዕድገትና Transformation እቅድ ውስጥ ሳይገባ ቀረ?
2. ዓባይን የመገደቡ ጉዳይ ለምን አሁን ተነሳ ?
3. ለአቶ መለስ ይችን ሃሳብ ማን ሹክ አላቸው ?
4. በዚህ ጫጫታ የወያኔ ትርፍ ምንድ ነው ?
5. ለምን ዘርፈ ብዙ የሆነ ግደብ እንዳይሠራ ተፈለገ ?
6. ለምን ሱዳን ጠረፍ ላይ ሄድ መገንባት አስፈለገ ?
7. ለምን እጅግ ትልቅ ግድብ እንዲሆን ተመረጠ ?.…ወዘተ ቁጥር 3 እና 6 ን ጨረፍ አዴርጌ የቀሩትን ለናንተ እተዋለሁ፤ ተወያዩበት !
ቁ.3 የሰሜን አፍሪካና የአረብ አገር አምባ ገነኖችን የመታው ሕዝባዊ አውሎ ንፋስ እንቅሌፍ የነሳው እሳቸውንና እሳቸውን መሰል አምባ ገነኖችን ብቻ ሳይሆን በአረብ አገራት ዙሪያዋን የተከበበችው እስራኤሌንም ጭምር በይበልጥ አስጨንቋታል፤ በተለይ የግብጽና የእስራኤሌ የሠላም ስምምነት ይናጋ ይሆናል የሚለው አንዱ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ፤ ግብፆች ከኢራኖች ጋር እያደረጉ ያለት መቀራረብ፤ ሁለቱ የፍሌስጤም ነፃ አውጪ ድርጅቶች በግብጽ አማካኝነት እርቅ ማድረጋቸው…. ወዘተ የእስራኤልን ስጋት ጨምረዋል::
ታዲያ ይህን ስጋት ለማስተንፈስና ግብጽን ተይ የምትሠሪው ሥራ ለኛ አይበጅም ለማት አማራጭ ሲፈለግ፤ ግብጽን ከአናት ሆና የምታስፈራራ አገር ኢትዮጵያ ተገኘች፤ ፈጥነው እስራኤልች ለአቶ መለስ ይችን ሹክ ሲሏቸው፤ ዘወትር ባገኙት አጋጣሚ ላይ ቶሎ ፍጢጥ የሚሉት የዘወትር የገጠመኝ ተጠቃሚው አቶ መለስ (opportuniste)፤ አንካሳ ዶሮ ሳትቀድማቸው 20 ዓመት ሙለ ትዝ ያላላቸውን ኢትዮጵያዊነትና የዓባይን ግድብ እንገንባ፤ አታሞ መደለቅና ማስደለቅ ጀመሩ::
ይቺ የፖለቲካ ቁማር በመጠኑም ቢሆን ለጊዜው የሠራች ይመስላል፤ ግብጾች ጉዳዩ ስላሳሰባችው መልክተኞች ልከው ከአቶ መለስ ጋር እንዲነጋገሩ በማድረግ፤ የግድቡ ሥራ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ተደርጓል፤ ፤ ይህ ሁሉ ውሳኔ የተደረገው በአንድ ፈላጭ ቆራጩ አቶ መለስ ዜናዊ ብቻ ሲሆን፤ በፓርላማ እንደ በግ አጉረው፤ እሳቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲሳደቡና ሲያንጓጥጡ፤ ለመሳቅ፤ ሲደነፉ ለማጨብጨብ፤ ከደሃው ወገናችን በተሰበሰበ ቀረጥ የደለበ ደሞዝ የሚከፈላቸው የፓርላማ አባል ተብዬዎች የሚያውቁት አንድም ነገር የለም። ሌላው አስቂኝ ድራማ ግብጾች በግንባታው ሥራ እንዲሳተፉ የተጠየቁት ሲሆን፤ ስንት ዘመን የቅኝ ገዢዎች የዓባይ ውሃ ስምምነት እንዳይለወጥብን እያለ ሲጮሁ የነበሩ፤ ማን ይሙት ዛሬ ለኛ ቅን አሳቢ ሆነው፤ ለግንባታው ወይስ ለጥፋቱ ሊሳተፉ?! ነገሩ ሁሉ የአንባ ገነን የጣር የነብስ አውጪኝ ጩኸት ሲሆን፤ በአንፃሩ አሳዛኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኑሮው ውድነት አልበቃ ብሎት፤ አፍንጫውን እየተሰነገ፤ ለዓባይ ግድብ ገንዘብ አዋጣ መባል ነው::
ዓባይ እንዳይገደብ የሚፈልግ አንድም ኢትዮጵያዊ እንደማይኖር እርግርጠኛ ነኝ፤ ግን እንደ ብል ከስር ስር ያገኙትን ጭዳ የሚያደርጉ፤ ነቀዞች (ሙሰኞች) አገሪቷን እያነቀዙ ባሉበት፤ አገሪቱ የማፍያዎች መፈልፈያ በሆነችበት ወቅት፤ እንዴት ተደርጎ ይህ ዕቅድ በሥራ ላይ ይውላል?
በተጨማሪ የአቶ መለስን የተለመደ ደባ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው፤ «እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው» እንዲሉ፤ ካልጠፋ ቦታ ሱዳን ጠረፍ ላይ ሄደው፤ የዓባይን ግድብ ካልገነባን ብለው፤ የኑሮ ውድነት የፈነካከተውን ቁስለኛ ሕዝብ ውጥር አርገው በመያዝ፤ ቁም ስቅለን ማሳየታቸው ነው :: ዓባይ መገንባቱ ባልከፋ፤ «አክሱም ለመሃል አገር ሰው ምኑ ነው?» እንዳሉን ነገ ደግሞ የአባይ ግድብ ለሱዳን እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑ ነው ቢሉንስ? እሳቸው እንደሆነ በርበሬ ከመቀንጠስ ይልቅ አገር መቀንጠስ ይቀላቸዋል፤ አያስነጠሳቸው ዓይናቸው አየቀላ:!!
ታዲያ መጠርጠር ይነሰን? « ያልጠረጠረ ተመነጠረ » እንዲሉ ሆኖ አይደል፣ ከወታደር አገዛዝ የከፋ: ምንም ቢሆን አይመጣም በማለት: ሕዝብ እጁን ዘርግቶ ቢቀበላቸው ዛሬ ጀርባው ላይ ፊጢጥ ብለው: ለም መሬቱን ለባዕድ እየቸበቸቡ እሱን በችጋር የሚያስለበልቡት::
ከዓባይ ግድብ ከተል አርገው እስራኤሎች ከፍሌስጤማውያን ወንድሞቻቸው ለመለየት የገነቡት የሃፍረት ግንብ (Le mur de la honte) ዓይነት በኛና በትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መሃል ትልቅ የዘር ግንብ እንዲገነባ በዕቅድ ላይ ሳይሆን ይቀራል?! ጠርጥር እሸቱ ሳይጠጥር!!
ሰሞኑን ደግሞ ሳር ቅጠለ ሳይቀር ሽብርተኛ ሆነ ብለው፤ ተሸብረው ያሸብራለ:: ጋዜጠኞች ሽብርተኛ፤ እከሌ ሽብርተኛ፤ እነእከሌ ሽብርተኛ፤ ግንቦት7 ሽብርተኛ፤ ብለው ፈራርጀው ሲያበቁ፤ «የዘመድ ጥል የስጋ ትል» ሆነባቸው መሰለኝ እንደ እንቁላል አቅፎ የፈለፈላቸው ሻዕቢያን በሽብርተኝነት አለመፈረጃቸውን ስንመለከት፤ የአቶ መለስ ዜናዊና የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጥል ለኛ ለማስመሰያ እንጂ ለብቻቸው ቢገናኙ፤ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው አጁሃ ከሜአላሃ ከተባባሉ በኋላ ለመቶ አመት የሰጡንን የቤት ሥራ እምን እንዳደረሱት ቁጭ ብለው እየተሳሳቁ እንደሚያወጉ አንጠራጠርም:: «ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣሌ» ይሏችኋል ይቺ ናት:: ለነገሩ አልኩ እንጂ፤ የኛ ሰው ነቄ ነው እንኳን ይችን የዝንብ ጠንጋራ በጨረቃ ነቅሶ ያወጣል ::
የሚያሳዝነው፤ ከሚወራው ሁሉ አንዱ እንኳን በተግባር የማይውልባት አገራችን፤ መከረኛው ሕዝብ፤ ኑሮን ለመኖር ሳይሆን፤ ለመከራ የተፈጠረ፤ በስሙ እየማሉና እየነገዱ በጀርባው ላይ የሚያናጥሩበትን ተሸክሞ ጀርባው እንደጎበጠ ወደ መቃብር የሚያዘግም፤ በምድራዊ ገሃነም ውስጥ የሚኖር፤ ያልታደለ የመከራ አምራቾች አስተናጋጅ መሆኑ ነው::
በየጊዜው ከ5 እስከ7 ሚሉዮን የሚሆን ሕዝብ መራቡ አሳሳቢ እንዳልሆነ በመቁጠር፤ እንደነሱ አባባል የተለመደ «Normal» መሆኑን የወያኔ ባለስልጣናት ባንድ ወቅት ገልጸዋል፤ እንግዲህ እነዚህ ወገኖቻችን የወያኔ የመለመኛ አቁማዳ ለመሙያ እንደ መያዣ እንዲያገለግል የተፈረደባቸው መሆኑን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊረዳው ይገባል::
ወያኔ ለሕዝባችን መራብ ተጠያቂ ነው! በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ፤ እንደ ወያኔ ዘመን ያህል ዕርዳታ የዘነበበት፤ ብድር የተነከርንበት ጊዜ የለም፤ ታዲያ ይህ ሁለ ሆኖ የረሃብና የአብዮት አዙሪት አላበቃም!
በሰለጠነው ዓለም ውሻና ድመት…..እንኳን ተራቡ ተብሎ ለእንስሳት መብት ሲጮህ: በኛ አገር የሰው ልጅ ሲራብ የተለመደ ነው ይባላል:: …………
ክፍሌ 2 ይቀጥላል
|
የካናዳ የመብቶችና ነፃነቶች ቻርተር
የመብቶችና ነፃነቶች ዋስትና፣
- የካናዳ መብቶችና ነፃነቶች ቻርተር በውስጡ የተዘረዘሩትን መብቶችንና ነፃነቶችን ዋስትና ይሰጣል። እነዚህ መብቶችና ነፃነቶች ዲሞክራሲያዊና ነፃ በሆነ ሕብረተሰብ ውስጥ ተገቢነቱ በግልፅ ሊያረጋግጥ የሚችል ሕግ ከሚያበጀው መጠናዊ ወሰን በስተቀር ገደብ አይኖራቸውም።
መሠረታዊ ነፃነቶች፣
- ማንም ቢሆን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት መሠረታዊ መብቶች አሉት።
ሀ. የሂሊናና የሃይማኖት ነፃነት፣
ለ. ያስተሳሰብ፣ የእምነት፣ የአመለካከት እንዲሁም የፕሬስና ሌሎች መገናኛ ዘዴዎችን ያካተተ አስተሳሰብን፣ እምነትንና አመለካከትን የመግለፅ ነፃነት፣
ሐ. ሰላማዊ ጉባዔ፣
መ. የመደራጀት ነፃነት፣
ዲሞክራሲዊ ነፃነቶች
- ማንኛውም የካናዳ ዜጋ በፌደራላዊ የመማክርት ሸንጎ ወይም ክፍለሃገራዊ የሕግ ሸንጎ አባላት ምርጫ ወቅት ድምፅ የመስጠት እንዲሁም የነዚህ ሸንጎዎች እጩ አባል ሆኖ የመቅረብ መብት አለው።
- (1) የትኛውም ፌደራላዊ የመማክርት ሸንጎ ወይም ክፍለሃገራዊ የሕግ ሸንጎ ከአምስት እመት በላይ በሥራ ላይ መቆየት አይችልም። የአምስት አመቱ ገደብ የሚሰጡ የሸንጎው አባላት አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ሸንጎውን የመበተኛ ቀን ገደብ ተብሎ ከተቆጠረው ቀን አንስቶ ነው።
(2) ጦርነት፣ ወረራ ወይም ዓመፅ ከተነሳ ወይም የመነሳት አዝማሚያ በቅጡ ከታየ ፌደሬላዊ ፓርላማ ፈደረላዊውን የመማክርት ሸንጎ፣ ክፍለሃገራዊ ሕግ ደንጋጊ አካል ደግሞ ክፍለሃገራዊውን ሸንጎ ከአምስት አመት በላይ በሥራ ላይ እንዲቆይ ማድረግ ይችላል። ይህ የሚሆነው ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሆኑ የፌዴሬላዊው ሸንጎ አባላት የፌዴሬላዊው የመማክርት ሸንጎን፣ የክፍለሃገራዊ ሸንጎ አባላት ደግሞ የክፍለሃገራዊ ሸንጎን የሥራ ዘመን መራዘምን ካልተቃወሙት ነው።
- ፓርላማውም ሆነ እያንዳንዱ ክፍለሃገራዊ ሸንጎ ቢያንስ በአሥራ ሁለት ወር አንድ ጊዜ ለጉባዔ
መቀመጥ ይኖርበታል።
ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ነፃነት
- (1) የካናዳ ዜጋ የሆነ ሁሉ ወደ ካናዳ የመግባት በሃገሪቱ ውስጥ የመቀመጥ እንዲሁም ካናዳን ለቆ የመውጣት መብት አለው።
(2)የካናዳ ዜጋ የሆነ ሁሉና እንዲሁም በካናዳ ቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ የያዘ ሁሉ
ሀ. ወደየትኛውም የካናዳ ክፍለሃገር የመሄድና በዚያ ኑሮን የመመሥረት እንዲሁም
ለ. በየትኛውም ክፍለሃገር ውስጥ ሠርቶ የማደር መብቶች አሉት።
- ከላይ በአንቀጽ 6 (2) የተጠቀሱትንመብቶች
ሀ. በየክፍለሃገሩ ፀንተው ላሉ ሕግጋት ወይም ሁለገብ የአሠራር ዘዴዎች ተገዢ ናቸው። ማለትም ሕግጋቱና የአሠራር ዘዴዎቹ ግለሰቦች የሚኖሩበትን ወይም ቀድሞ ይኖሩበት የነበረውን የመኖሪያ አድራሻ እንደዋነኛ ምክንያት በመቁጠር መድሎ የማያደርጉ እስከሆነ ድረስ።
ለ. በተጨማሪም እነዚህ መብቶች በሕዝብ ወጪ የሚበረከቱ ግልጋሎቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ መጠነኛ የነዋሪነት መለኪያዎች ለሚነድፉ ሕግጋትተገዢ ናቸው።
- ከላይ በአንቀጽ 6 (2) እና (3)የተጠቀሱት መብቶች በአንድ ክፍለሃገሮች ውስጥ ያለው ሥራ የማግኘት ዕድል በአጠቃላይ ካናዳ ካለው የሥራ ዕድል ጋር ሲነፃፀር በክፍለ ሃገር ውስጥ ያለው ዕድል አናሳ ሆኖ ሲገኝ በክፍለሃገሩ ውስጥ የሚኖሩና በማሕበራዊና በኢኮኖሚያዊ መልክ ወደ ኋላ የቀሩን ግለሰቦችን ሕይዎት ማሻሻል ዋና አላማው የሆነ ሕግ መደንገግን፣ ፕርግራም ወይም እንቅስቃሴ መዘርጋትን አያግዱም።
ሕግ ነክ መብቶች፣
7. ማንም ቢሆና የሕልውና እገታ ነፃ የመሆን፣ እንዲሁም ገለሰብአዊ ደህንነቱ ተጠብቆ የመኖር መብትና እነዚህንም መብቶች መሠረታዊ የፍትህ መረሆዎች በሚፈቅዱት መንገድ ካልሆነ በቀር ያለመነፈግ መብት አለው።
8. ማንም ቢሆን ተገቢ ላልሆነ ፍተሻ ሳይደረግ ንብረቱን ያለአግባብ በቁጥጥር ላይ ሳይውል ተጠብቆ የመኖር መብት አለው።
- ማንም ቢሆን በዘፈቀደ ያለመያዝ ወይም ያለመታሰር መብት አለው።
- ማንም ቢሆን በቁጥጥር ሲውል ወይም ሲታገት የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል
ሀ. በፍጥነትለምን በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ወይም እንደታገደ የማወቅ፣
ለ. ካለአንዳች መዘግየት ጠበቃ የማቆምና ለጠበቃውም መመሪያ የመስጠት እንዲሁም ይህ ዓይነት መብት እንዳለው የመነጋገር፣
ሐ. በሃብየስ ኮርናስ የፍርድ ሂደት የእገዳው ተገቢነት ወይ ተገቢ ያለመሆን የመወሰንና እገታው ሕጋዊ ሆኖ ካልተገኘ ክእገታው የመለቀቅ፣
- በውንጀል የተከሰሰ ማኛውም ግለሰብ የሚከተሉት መብቶች አሉት
ሀ. የተከሰሰበት ወንጀል በትክክል ምን እንደሆነ ከልክ በላይ ሳይዘገይ መናገር፣
ለ. መጠናዊ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለፍርድ መቅረብ
ሐ. ክሱንና እሱን አስመልክተው በሚካሄዱ (ችሎቶችና) ሌሎች የፍርድ ክንዋኔዎች ላይ ታግዶ ቃል ወይም ምሥክርነት አይሰጥም፣
መ. ጥፋጠኝነቱ ከተፅእኖ ነፃ በሆነና ባልተወሰነ የፍርድ መንበር እንዲሁም ሚዛናዊና ግልፅ በሆነ ችሎት እስኪረጋገጥ ድረስ ከወንጀሉ ንፁሕ ነው ተብሎ መቆጠርን፣
ሠ. ያለአንዳች ፍትሃዊ ምክንያት ተገቢ የሆነ የዋስ መብቱን ያለመንፈግ
ረ. ወታደራዊ ሕግጋትን በሚፃረር ወንጀል ተከሶ በወታደራዊ የፍትህ ችሎት ፊት የሚቀርብን ተከሳሽ ሳይጨምር ማንም እስክ አምስት አመት ወይም ከዚያም በላይ በሆነ የእስራት ቅጣት ሊይስቀጣ በሚችል ወንጀል የተከሰሰ ሁሉ በዳኛና ከብጤዎቹ በተወጣጣ ችሎት የመዳኘት መብት አለው።
ሸ. የፈፀመው ድርጊት ወይም ባልፈፀመው የቀረው ግዴታ በካናዳ ወይም በአለም አቀፋት ሕግጋት ዘንድ ወይም የሃገራት ስብሰባ አምኖ በተቀበላችው አጠቃላይ የሕግ መረጃዎች ዘንድ ወንጀል ሆኖ ካልተወሰነ በስተቀር አንድን ድርጊት ስለአደረገ ወይም አንድን ግዴታ ሳይፈጽም ስለቀረ ብቻ ጥፋተኛ ተብሎ አይፈረድበትም።
ቀ. ከተከሰሰበት ወንጀል ነፃ ነው ተብሎ ከተፈረደበት በኋላ እንደገና በዚያው ወንጀል ለፍርድ አይቀርብም። እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ቅጣቱን ከተቀበለ በኋላ በዚያው ወንጀል እንደገና ፍርድ ቤት አይቀርብም ወይም በድጋሚ አይቀጣም።
በተጨማሪም፣
በ. በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ፍርዱን ሲቀበል ወንጀሉን በፈፀመበትና ፍርዱን በሚቀበልበት ቀን መሐከል ባለው ጊዜ ውስጥ ለወንጀሉ በሕግ የተደነገገው የቅጣት መጠን ከተለወጠ በነባሩና በአዲሱ ቅጣት መሐከል ከሁለቱ በአነስተኛው የመቀጣት እድል አለው።
- ማንም ቢሆን ጭካኔ ለተሞላበት እንግዳ ለሆነ ድርጊት ወይም ቅጣት ያለመዳረግ መብት አለው።
- በማንኛውም ችሎት ወይም የፍትህ ሂደት ላይ ምሥክርነት የሚሰጥ ሁሉ የገዛ ራሱን ለወንጀል የሚያጋልጥ ምሥክርነት ያለመስጠት መብት አለው። የገዛ ራሱን ለወንጀል የሚዳርግ ምሥክርነት ከሰጠም ይህ ቃሉ በሃሰት በመመሥከርና እርስ በርሱ የሚያቃርን መረጃ በመስጠት ከሚያስወነጅለው በስተቀር በሌላ ችሎት በወንጀል ተከሶ እንዲቀርብ አያደርገውም።
- በማንኛውም ችሎት ወይም የፍትህ ሂደት ላይ የሚሳተፍ ባለጉዳይ ወይም ምሥክር ቋንቋው ችሎቱ ወይም የፍትህ ሂደቱ ከሚካሄድበት ቋንቋ ጋር አንድ ካልሆነ ወይም ቋንቋውን የማይረዳ ከሆነ ወይም መስማት የተሳነው ከሆነ ያስተርጓሚ ግልጋሎት የማግኘት መብት አለው።
የእኩልነት መብቶች፡
- (1) ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት በሕግ ሥር እኩልና ካላንዳች አድሎ ማለትም በዘሩ፣ በብሔሩ፣ ወይም በሕብረሰባዊ ትውልዱ፣ በቆዳው ቀለም፣ በሃይማኖቱ በፆታው በዕድሜው ወይም ከአካላዊ ጉድለቱ ምክንያት አድሎ ሳይደረግበት መብቱ በሕግ እኩል ተጠብቆ የመኖር ከሕግም እኩል ጠቀሜታ የማግኘት መብት አለው።
(2) ንዑስ አንቀፅ (1) ከጥቅም የተገለሉ ግለሰቦችን የሕብረተሰቡን አካላት ማለት በዘር፣ በብሔራዊ ወይም ብሄረሰባዊ ትውልድ፣ በቆዳ ቀለም፣ በሃይማኖት፣ በፆታ፣ በዕድሜ ወይም በአዕምሮአዊ ወይም በአካላዊ ግድለት ምክንያት ከጥቅም የተግለሉን ጨምሮ የኑሮ ሁኔታን ማሻሻልን ዓላማው አድርጎ የሚወጣን ሕግ የሚዘጋ ፕሮግራም ወይም እንቅስቃሴ አያደርግም።
የካናዳ የፋ ቋንቋዎች፣
- (1) እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ የካናዳ ይፋ ቋንቋዎች ናቸው። በአጠቃላይ ረገድም ማለትም በሁሉም የፓርላማውና የካናዳ መንግሥት ተቋማት ውስጥ እነዚህ ቋንቋዎች በሥራ ላይ ሲውሉ እኩል ደረጃ፣ እኩል መብቶችና እኩል ልዩ መብቶች አሏቸው።
(2) እንግሊዘኛና ፈረንሣይኛ የኒው ብራንስዊክ ክፍለሃገር ይፋ ቋንቋዎች ናቸው። በአጠቃቀም ረገድም ማለትም በሁልም የክፍለ ሃገር የሕግ ሸንጎና የክፍለ ሃገሩ መንግሥት ተቋማት ውስጥ እነዚህ ቋንቋዎች በሥራ ላይ ሲውሉ እኩል ደረጃ እኩል መብቶችና እኩል ልዩ መብቶች አሏቸው።
(3) ፓርላማውም ሆነ ክፍለሃገራዊ የሕግ ሸንጎዎች ሥልጣን ማለትም የእንግሊዘኛንም ሆነ ፈረንሣይኛን የእኩልነትደረጃም ወይም በስራላይ የማዋል የዞታ የማጎልበት ስልጣን በዚህ ቻርተር ውስጥ በተጠቀሰ አንዳችም ነገር ገደብ አልተደረገበትም።
16.1 (1) በኒውብራንስዊክ ክፍለሃገር ያሉ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ማህበረሰቦችና ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ማህበረሰቦች እኩል ደረጃ እኩል መብቶችና እኩል ልዩ መብቶች አሏቸው። እነዚህ መብቶች ማህበረሰቡ የየራሳቸው የሆኑ የትምህርት ተቋማት የማግኘት መብትን እንዲሁም እነዚህ ማህበረሰባት ተጠብቀውና አብበው እንዲኖሩ የሚያደርጉ ልዩ የባህል ተቋማት የማግኘት መብትን ያካትታሉ።
(2) የኒውብረንስዊክ ክፍለሃገራዊ የህግ ሸንጎና የመንግስት ከላይ በንዑስ አንቀጽ አንድ የተዘረዘሩትን የእኩልነት ደረጃዎች መብቶችና ልዩ መብቶች ተጠብቀውና እንዲቆዩ የማድረግና እንዲያብቡ የማድረግ ሚና ሲኖራቸው ይህም ሚናቸው በድጋሚ በዚህ ቻርተር ተረጋግጧል።
17 (1) ማንም ቢሆን በፓርላማ ውስጥ በሚደረጉ ክርክሮች ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ፓርላማ ነክ ተግባራት ላይ እንግሊዝኛን ወይም ፈረንሳይኛን የመጠቀም መብት አለው።
(2) ማንም ቢሆን በኒውበረንስዊክ የህግ ሸንጎ ውስጥ በሚደረጉ ክርክሮች ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮች ላይ እንግሊዝኛን ወይም ፈረንሳይኛን የመጠቀም መብት አለው።
18 (1) በፓርላማ የሚደነገጉ ሕግጋት፤ የፓርላማው መዝገበ ልሳኖች በእንግልዝኛና በፈረንሳይኛ መታተማቸው ግዴታ ሲሆን በሁለቱም ቋንቋ የተዘጋጁት ቅጅዎች አኩል ተቀባይነት ኣላቸው።
(2)በኒውበረንስዊክ የህግ ሸንጎ የሚደነገጉ ሕግጋት የሸንጎው መዛግብት አንዲሁም ልሳኖች በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ መታተማቸው ግዴታ ሲሆን በሁለቱም ቋንቋ የተዘጋጁት ቅጅዎች እኩል ተቀባይነት አላቸው።
19 (1) ማንኛውም ግለሰብ በፓርላማው ስልጣን በተቋቋሙ ፍርድ ቤቶችም ሆነ በነዚህ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡ ማመልከቻዎችና መዛግብት በተመለከተ እንዲሁም በእነዚህ ፍርድ ቤቶች ስልጣን በሚከናወኑ ማንኛውም የፍትህ ሂደቶች ላይ በእንግሊዝኛ ወይም በፈረንሳይኛ ማሳተፍ ወይም ማመልከቻዎችንና የመሳሰሉትን ዶኩመንቶች ከነዚህ በአንዱ ቋንቋ ማቅረብ ይቻላል።
(2) ማንኛውም ግለሰብ በማናቸውም የኒውበረንሰዊክ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ወይም በፍርድ ቤቶቹ ስልጣን በሚከናወኑ ማናቸውም የፍትህ ሂደቶች ላይ በእንግሊዝኛ ወይም በፈረንሳይኛ መሳተፍ ወይም ከነዚህ ቋንቋዎች በአንዱ ማመልከቻና የመሳሰሉትና የህግ ዶክመንቶች የማቅረብ መብት ነው።
20 (1) ማንኛውም በካናዳ የህብረተሰቡ አካል የሆነ ሁሉ በፓርላማው ወይም በካናዳ መንግስት ስር ካሉ ተቋማት ዋና መስሪያ ቤቶች ወይም መአከላዊ ቢሮዎች ጋር በእንግሊዘኛ ወይም በፈረንሳይኛ ግንኙነት ሊያደርግ ወይም ከተቋማቱ ከሁለቱ ይፋ ቋንቋዎች በአንዱ ግልጋሎት ሊያገኝ መብት አለው። በተጨማሪም ከሚከተሉት መመዘኛዎች አንዱ ተሟልቶ ሲገኝ በእነዚህ ተቋማት ስር ካሉ ሌሎች ቢሮዎች ተመሳሳይ ግልጋሎቶች ሊያገኝ መብት አለው።
(ሀ) ጉዳዩ ትኩረት የተደረገበት ቢሮ በዚያ ቋንቋ ግልጋሎት እንዲሰጥ የሚፈልገው ተጠቃሚ ቁጥር በዛ ያለ ሆኖ ሲገኝ
(ለ) የቢሮ የስራ ጸባይ በሁለቱም ይፋ ቋንቋዎች ግንኙነት ማድረጉና ግልጋሎቱንም በሁለቱም ቋንቋዎች መሰጠቱ ተገቢ ሆኖ ሲገኝ
(2) ማንኛውንም የኒውበረንስዊክ ህብረተሰብ አካል በክፍለ ሃገሩ ሸንጎ ወይም በክፍለ ሃገሩ መንግስት ስር ካሉ ተቋማት የትኛውም ቢሮዎች ጋር በእንግሊዝኛ ወይም በፈረንሳይኛ ቋንቋ ግንኙነት የማድረግን ከእነዚህ ቋንቋዎች በአንዱ ግልጋሎት የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው።
21. ከአንቀጽ 16 እስከ 20 የተጠቀሱት አንዳቸውም ጉዳዮች በካናዳ ሕገ መንግስት ሌሎች አንቀጾች አማካይነት እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ወይም ከሁለቱ አንዱን በተመለከተ ፀድቆ ካለና ወደፊት የሚኖርን ማንኛውም መብት እንዲሁም ልዩ መብት ወይም ግዴታን አያፈርሱም ወይም ይህን መሰል መብት ልዩ መብት ወይም ግዴታ አይቀንሱም።
22. ከአንቀጽ 16 እስከ 20 የተጠቀሱት አንዳቸውም ጉዳይዎች ይህ ቻርተር በስራ ላይ ከመዋሉም በፊትም በኋላ ከእንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ ውጭ የሆነ ሌላ ሶስተኛ ቋንቋን በህግም ሆነ በልማድ የተጎናጸፈውን መብት አያፈርሱም ወይም ከዚያ መብት ላይ ምንም አይቀንሱም።
ቋንቋቸው በብዛት በጥቅም ላይ በማይውልበት አካባቢ የሚኖሩ ካናዳውያን መብት
23) (1) የካናዳ ዜጎች
ሀ) በመጀመሪያ የቀሰሙትና በወቅቱም የሚገባቸው ቋንቋ በሚኖሩበት ክፍለሃገር ውስጥ ያሉ የእንግሊዘኛ ወይም የፈረንሣይኛ ተናጋሪ አናሳ ማህበረሰብ ቋንቋ አባላት ቋንቋ ከሆነ ወይም
ለ) የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በካናዳ በእንግሊዘኛ ወይም በፈረንሣይኛ ተከታትለው ሳለ ትምህርታቸውን የተከታተሉበት ቋንቋ በሚኖሩበት ክፍለሃገር ውስጥ ያሉ የኢንግሊዘኛ ወይም ፈረንሣይኛ ተናጋሪ አናሳ ማሕበራት ቋንቋ ከሆነ
ልጆቻቸው የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው በዚያ ቋንቋና በዚያው በሚኖሩበት ክፍለሃገር የመከታተል መብት አላቸው።
- የካናዳ ዜጎች የሆኑና ከልጆቻቸውም ውስጥ አንዱ የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በእንግሊዘኛ ወይም በፈረንሣይኝ የተከታተለ ከሆነ ወይም እየተከታተለ ካለ የተቀሩ ልጆቻቸው በዚያው ቋንቋ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የመከታተል መብት አላቸው።
- ከላይ በኑኡስ አንቀጽ አንድና ሁለት የተጠቀሱት የካናዳ ዜጎች መብቶች ማለትም ልጆቻቸው በሚኖሩበት ክፍለሃገር ውስጥ ባሉ የእንግሊዘኛ ወይም የፈረንሣይኛ አናሳ ማሕበራት ቋንቋ በአንዱ የመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የመከታተል መብት
ሀ. በተግባር ላይ የሚውለው በክፍለሃገሩ ውስጥ የዚህ ዓይነት መብት ባለቤቶች የሆኑ የካናዳ ዜጎች ልጆች ቁጥር በሕዝብ ገንዘብ በአናሳ ማሕበረሰባት ቋንቋ ትምህርት ከመስጠት ጋር ሲነፃፀር ትምህሩን በቋንቋው መሰጠቱ ተገቢ ሆኖ ሲገኝ ነው።
ለ) ከላይ የተጠቀሰው ማለትም የልጆቹ ቁጥር መጠን የትምህርቱን በቋንቋው መሰጠት ተገቢ ሲያደርገው በንኡስ አንቀፅ (1) እና (2) የተጠቀሰው መብት በሕዝብ ገንዘብ በሚካሄድ የአናሳ ማሕበረሰብ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትምህርቱን የመከታተልን መብት ያካትታል።
መብትና ነፃነትን ማስከበር
24) (1) በዚህ ቻርተር ዋስትና ያገኙ መብቶች ወይም ነፃነቶች የተደፈሩበት ወይም የተነፈጉት ግለሰብ ሁሉ ይህን ዓይነት ጉዳይ ለመዳኘት ብቃት ላለው የፍርድ አካል አቤት ማለትና ችሎቱም ከፊቱ ለቀረበው ጉዳይ ተገቢና ፍትህ ነው ብሎ የሚፈርደውን ካሣ ማግኘት ይችላል።
(2) ከላይ በንኡስ አንቀጽ አንድ የተጠቀሰው የፍርዱ ክንዋኔ ተካሂዶ በማብቂያው ላይ የፍርድ መንበሩ ከአቤት ባዩ የተሰበሰበው መረጃ በዚህ ቻርተር ዋስትና ካገኙት የአቤት ባዩ መብቶችና ነፃነቶችን ውስጥ አንዱንም እንኳን በመድፈር ወይም በመንፈግ የተገኘ ነው ብሎ ከደመደመ ይህ ዓይነቱን ማስረጃንም በፍርዱ ሂደት ላይ መቀበሉም በአጠቃላይ የፍትህ ሥርአቱን ቅሌት ላይ የሚጥል ከሆነ የፍርዱ መንበር ማስረጃዎች ከችሎቱ ፊት ይገለላል ተቀባይነትም አይኖረውም።
አጠቃላይ
25) በዚህ ቻርተር አመካይነት የተወሰኑ ነፃነቶችና መብቶች ዋስትና ማግኘታቸው የከናዳ ቀደምት ነዋሪዎችን ጥንታዊ ወይም በስምምነት የፀደቀ ነፃነቶችንና መብቶች እንደማይሻር ወይም እንደመቀነስ ተደርጎ መታየት የለበትም። በዚህ ቻርተር ያልተሻሩት ወይም ያልተቀነሱት የካናዳ ቀደምት ነዋሪዎች የሚከተሉትን ይጠቀልላሉ።
ሀ. በኦክቶበር 7 ቀን 1763 ዓ.ም. ንጉሣዊ አዋጅ እውቅናን ያገኙ ማናቸውም ነፃነቶች ወይም መብቶች
ለ. የመሬት ይገባኛል ጥያቄን በተመለከተ የተፈረሙ ስምምነቶች የፈጠሯቸው ወይም ወደፊት የሚፈጠሩ መብቶች
26) በዚህ ቻርተር አማካይነት የተወሰኑ ነፃነቶችና መብቶች ዋስትና ማግኘታቸው ከነዚህ መብቶችና ነፃነቶች ሌላ በካናዳ ውስጥ ሌሎች እንደሌሉ አድርጎ እንደመደንገግ ተደርጎ መታየት የለበትም።
27) ይህ ቻርተር የካናዳውያንን ባለ ብዙ ባህል ቅርስ እንደሚጠብቅና እንደሚያጎለብት ተደርጎ መተርጎም ወይም መነበብ ይኖርበታል።
28) በዚህ ቻርተር ውስጥ ምናልባት ሌላ ትርጉም የሚሰጥ ቢኖርም እንኳን በቻርተር ውስጥ ያሉ ነፃነቶችና መብቶች ለወንዶችም ለሴቶችም በእኩልነት ዋስትናቸው የተጠበቀ ነው።
29) የካናዳ ሕገ መንግሥት የሃይማኖትን ወይም አመልክካከትን መሰረት በማድረግ የተቋቋሙ የግል ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ የሰጣችውን ነፃነቶች ወይም ልዩ መብቶች በዚህ ቻርተር ውስጥ የተጠቀሰ አንዳችም ነገር አይሽራቸውም ወይም አይቀንሳቸውም።
30) በዚህ ቻርተር ውስጥ ስለክፍለ ሃገራት ወይም ሰለ ክፍለሃገራዊ የሕግ ሸንጎ ወይም ሕግ ድንጋጌ አካል የተጥቀሱት ሁሉ በዩኮንና በሰሜን ምዕራብ የአስተዳደር ክልሎች ሸንጎዎች ወይም ትመሳሳይ ሽንጎዎች ላይ ሁሉ ይሰራል።
31) በዚህ ቻርተር ላይ የተጠቀስ አንዳችም ነገር የየትኛውንም አካል ወይም ባለሥልጣን የሕግ የመደንገግ ሃይል አያሰፋም።
32) (1) ይህ ቻርተር
ሀ) በካናዳ ፓርላማና መንግሥት ላይ ተቀባይነት አለው። ተፈፃሚነቱም ፓርላማው በሥልጣኑ ሥር ባሉት ማንኛቸውም ጉዳዮች ማለትም የዩኮንና የሰሜን ምዕራብ የአስተዳደር ጉዳዮችን ላይ ጨምሮ ተፈፃሚነት አለው።
ለ) በእየአንዳንዱ ክፍለሃገራዊ ሽንጎና መንግሥታት ሥልጣን ሥር በተካተቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አለው።
(2) ከላይ በንኡስ አንቀጽ እንደየተጠቀሱት እንደአሉ ቢሆኑም የዚህ ቻርተር አንቀጽ 15 ይህ አንቀጽ በሥራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ ሦስት አመት ድረስ ተፈፃሚነት አይኖረውም።
33) (1) ፓርላማውም ሆነ ክፍለሃገራዊ ሸንጎ ንኡስ አንቀጽ (2) ወይም ከንኡስ አንቀጽ 7 እስከ 15 ያልትን አንቀፆች ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው ተፈፃሚነት የሚኖራቸው አዋጆች ማወጅ ይችላሉ።
(2) አንቀጽ (1) በመንተራስ የታወጀ አዋጅ ወይም የዚያ አዋጅ ንኡስ ክፍል በዚህ ቻርተር ውስጥ የተጠቀሱት መብቶችና ነፃነቶች እንዳልተደነገጉ ያህል ሙሉ ተፈፃሚነት ይኖረዋል።
(3) ንኡስ አንቀጽ አንድን በመንተራስ የታወጀ አዋጅ በሥራ ላይ ከዋለበት ከአምስት አመታት በኋላ ወይም በአዋጁ ውስጥ የተደነገገ ክአምስት አምታት ያነስ ገድብ ካልያ ገደብ ሲያልፍ የአዋጁ ተፈጻሚነት ያከትማል።
(4) ፓርላማው ወይም ክፍለሃገራዊ ሸንጎዎች እንዲህ አይነቱን አዋጅ አድሰው ማወጅ ይችላሉ።
(5) ከላይ በንኡስ አንቀጽ ሦስት የተጠቀሱት ሁሉ ንኡስ አንቀጽ አራትን በመንተራስ የሚታደስ አዋጅ ላይ ተፈፃሚነት አላቸው።
|
የኢትዮጵያ ቀንና እንቁጣጣሽ እንደተለመደው በቶሮንቶ ሊከበር ነው!!
በቶሮንቶ የሚከበረው ዓመታዊ የኢትዮጵያ ቀን ዘንድሮም ቅዳሜ ስፕቴምበር 10 ቀን 2011 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር ለዚሁም ታላቅ ዝግጅት የሚደረግ መሆኑንና ያለምንም እንከን ከወገኖቻችን ጋር ተባብረን እናከብራለን በማለት ከማህበሩ ጽ/ቤት የደረሰን ዜና ያረጋግጣል።
በአገራችን አቆጣጠር መስከረም 1 ቀን 2004 ዓ.ም. የዘመን መለወጫና፣ አዲስ ዓመት እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀን ድርብ በዓል ዘወትር በሚከበርበት በቶሮንቶ ብሉርና ክርስቲ መናፈሻ ሲሆን ውዲቱ አገራችንን በማስታወስ በየዕምነታችን ለአምላካችን ምሥጋና የምናቀርብበት፣ ራቅ ብለው ለሚገኙ ወገኖቻችን የምናስታውስበት፣ የኢትዮጵያውያን ወግና ባሕል ማንነታችንን ከማብሰሩም በላይ ዓይን በዓይን በመገናኘት በኢትዮጵያ ወገኖቻችን በቶሮንቶ፣ ካናዳና ሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በአለም ላይ የሚገኙትን ወገኖቻችን የመተሳሰብን፣ ፍቅርና አንድነትንም የሚያንፀባርቅ መሆኑንም ይታመንበታል። ይህም የሆነበት የኢትዮጵያ ማህበር ዋና አዘጋጁ ከፖለቲካ፣ከሃይማኖት፣ ከጎሣ ከተለያዩ ቡድኖች የማይወግን ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን በእኩልነት የሚያሳትፍ ድርጅት በመሆኑ ነው።
በዚህም አንጽፃር አብዛኛውን ኢትዮጵያውያን ውድ አገራቸውን ያለፈቃዳቸው ትተዋት ቢገኙም፣ ኑሮውቸውን በባአድ አገር ላይ በመመሥረት ለትውልድ አገራቸውና ለወገን የሚጠቅም ሥራ የሚሰሩትንና ጥሩ ዓላማቸውን የሚያሳዩበትና የሚያስተዋውቁበት ቀን ነው።
የኢትዮጵያ ቀን በካናዳ ኢትዮጵያውያን ያለንን ባህል ወግ የምናስተዋውቅበት ከፍተኛ መድረክ በመሆኑ ይህ ሕልውናችንን ክብራችንን የምናሳይበት ሌሎቹም ገንቢ የሆነ አድራጎታችንን የሚያደንቁበት እኛም አንቁጣጣሽን እያስታወስን የምንደሰትበት ቀን ነው።
ወጣት ታዳጊ ልጆቻችንም ምንም እንኳን በትውልድ ካናዲያኖች ቢሆኑም የወላጆቻቸውንና የዘር ግንዶቻቸውን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ባሕላቸውንና ወጋቸውን የሚያስታውሱበት ቀን ከመሆኑም በላይ በተሳታፊነትም ተገቢውን ዕውቅና የሚያሳዩበት ለልጆቻቸውም ቀደምትነት የሚሰጡበት በዓልም ነው።
በአሉ ከመድረሱ በፊት ብዙ በጎ ፈቃደኞች ኢትዮጵያውያን በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብ ለመርዳት የሚሳተፉበት ለማህበሩ ጽ/ቤት ስልክ እየደውሉ ወይም በአካል በመገኘት አስፈላጊ አስተዋጾ የሚያደርጉበት ነው። ለዚህ መሠረቱ ኢትዮጵያ ማህበር የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት በመሆኑ ሲሆን ቀጣይነት ያለው እርዳታ መስጠት የውዴታ ግዴታም ስለሆነ አንዱ ጤናማ መንገድ ይህን ለሁሉም እኩል ቤት የሆነውን ማህበር ማጠናከር ነው። ይህም ሲሆን ነው በካናዳ ከፍተኛ ድጋፍ ጥንካሬ ተሰሚነት ማግኝት የሚቻለው።
በአለፈው ተከታታይ አመት የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር የተሳካና ብዙ ኢትዮጵያውያንን ያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ሊሆን የቻለው በፈቃደኞች በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን፣ ጊዚያቸውን እንዲሁም እውቀታቸውን በመሰዋት ሲሆን ሊመሰገኑ ይገባል። መጪው ሴፕቴምበር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሚደረግው በዓልም ምንም ጊዜው አጭር ቢሆንም የተለያየ ንግድና ደርጅት እንዲሁም በጎ ፈቃድኞች ኢትዮጵያውያን እርዳታ ይጠበቅባቸኋል።
በተለያየ ምክንያት መሳተፍ የማትችሉ ኢትዮጵያውያን እለቱን በማስታወስ በበዓሉ
ላይ በፈቃደኝነት መገኘት ይገባል። ከወዲሁም ላልሰሙት በማሰማት ለበአሉ መዘጋጀት ያስፈልጋል።
በበዓሉም ላይ ለመገኘት ፈቃዳዊ ግዴታም እንዳላባችህ በመግለጽ አዲሱ ዓመትና የኢትዮጵያ ቀን የጤና፤ የብልፅግና፤ የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
ትዝታ |
|