Amharic News, Breaking News, Breaking News Amharic, Ethiopian
ስልጣኔና ወንጀል በኢትዮጵያ !! ( አሥራዳው ከፈረንሳይ )
Published Posted on | By TZTA Newsስልጣኔና ወንጀል በኢትዮጵያ !!
( አሥራዯዳው ከፈረንሳይ )
ኢትዮጵያ እድለኛ ናት ፤ የሬሳ ዘር የሚቆጥር መሪ አላት (አግኝታለች) !! ” ቁርጪን ፈርዲራ ኩፍቴ ” !! ጀናኒ
አኒ ሞ፤ ፉንዴሩማቱ ቁርጪን አካም ፤ ፈርዲራ ባቴ ?! ጀዳ ኢንጋፈዲ !
ከኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን፤ ብሂሌ የተወሰደ: ትርጉም
” ቆማጣ ከፈረስ ላይ ወደቀች“!! ቢሉኝ
እኔ ደግም፤ መጀመሪያውኑ: ቆማጣ እንዴት ፈረስ ላይ ወጣች?! ብዬ እጠይቃለሁ! ሰረዝ የተጨመረበት፤ እኔ የጠየኩት ጥያቄ ከነ ትርጉሙ መሆኑን፤ አንባቢ ይረዳለኝ:: ማስታወሻ :
በአገራችን ኢትዮጵያ፤ በስልጣን ዙሪያ ቀደም ብለው የተፈጸሙትን ወንጀሎች፤ እንዳመቺነቱ በቀጣይ፤ እመለስበታለሁ።
አሁን በአገራችን አስገዳጅነት ሁኔታዎች በመኖራቸው፤ ዛሬ እየተፈጸሙ ባለት የስልጣን ወንጀልች መጀመሩን መርጫለሁ።
የሰው ልጅ ያለፈውን በታሪክ መዝገብ መዝግቦ በመያዝ፤ ዳግም ላለመሳሳት ትምህርት እንዲሆነው፤ እራሱ የሠራቸውን ስህተቶች ብቻ ሳይሆን፤ የሌሎችንም ስህተቶች በማከሌ፤ ዛሬን በብልሃትና በጥረት እየኖረ ነገን በተስፋ ያለመልማል :
ሰው የወደፊቱን እንጂ፤ የኋላውን ስለማይኖር፤ እኔም ባለፉር ዘመናት የተሠሩ ስህተቶችን ለጊዜው በማቆየት፤ ትናንትናና ዛሬ፤ በህዝባችን ላይ የተፈጸሙና እየተፈጸሙ ያሉትን፤ የስልጣን ወንጀሎችን ለመዳሰስ እሞክራለሁ።
ምልከታዬ ፍጹማዊ ላይሆን ይችላል፤ እናም፤ የአገር ጉዳይ ግድ ይሆናል የምትሉ ወገኖቼ፤ በጉዲዩ በመሳተፍ፤ የበኩላችሁን እንዲታክለበትና ወደተሻለ መፍትሄ እንድንደርስ እጋብዛለሁ :
ከዳር ሆነን በመመልከት፤ ነገ በሚፈጠረው፤ የአገር መፍረስና፤ የወገኖቻችን መከራና ስቃይ ተጠያቂዎች ላለመሆን፤ ከፈለግን ጊዜው አሁን ነው::
ነገ የኛ ለመሆኑ እርግጠኞች ባለመሆናችን፤ ነገ የሚለውን ትተን፤ ዛሬን ከወገኖቻችን ጋር አብረናቸው እንቁም:: ይህን ስናደርግ ብቻ ነው በጥቂቱም ቢሆን፤ ሰብዕናችን ሰው ሰው የሚሸተው:: ያ ካልሆነ ከሰውነት ተራ ወጥተናልና፤ ኤላስ አከተመ ! አገርም ወገንም አይኖረንም!!
ማሳሰቢያ :
ጠ/ም አብይ አህመድ የሠራቸው ስህተቶች እንዳለ ሆኖ፤ ችግሮቻችን አብይን በመወንጀል፤ ወይም የአብይን ሃጢያት በማብዛት ብቻ፤ ይወገዳል ብል ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው።
ይልቁንም በማወቅም ሆነ፤ ባለማወቅ የህወሓት ወጥመድ ውስጥ ዘለን በመግባት፤ እነሱ የቆፈሩት የዘረኝነትና የጎሠኝነት ቆሻሽ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ ገብተን ስንቦጫረቅ እንድንገኝ፤ አጥብቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል።
ህወሓትና ዘረኞቹ የኦነግ/ኦህዳዴ ጥምር አሽከሮቿ፤ በጠ/ም አብይ አህመድ ላይ ጦር እንድንመዝላቸው፤ ስሌታዊ በሆነ መልኩ፤ አጥብቀው ይሻሉ፤ ለዚህ ምኞታቸው መሳካትም ሌት ተቀን ተግተው ይሠራሉ::
የህወሓት ጥምር አሽከሮች፤ ኦነግና/ኦህዳዴ ፤ አብይን የአንድ ዘርና ጎሣ ጥቅም አላስከበረም እያሉ ሲያብጠለጥሉት፤ እኛ ደግሞ ሌሎች አገራዊ ጉድዮችን በተሻለ መልኩ በሥራ ላይ ባለማዋሉ፤ የምንደቁሰው ከሆነ፤ በድርብ ቅራኔ ከነሱ ጎን አብረን እንዳንሰለፍ አጥብቀን መጠንቀቁ ተገቢ ነው::
ይህ ማለት አብይ ሲሳሳት፤ የአገርና የዜጎችን መብት ሲደፈጥጥ፤ የአገር ሉአሊዊነት ሲያስደፍር፤ የህግ የበላይነት ጠፍቶ ዜጎች የመኖር ዋስትና ሲያጡ፤ የአገር ሃብት ሲመዘበር፤ እያየን ዝም እንበል ማለት እንዳልሆነ እንድትረዱኝ እሻለሁ።
ለ27 አመታት በትጋት ወያኔን የታገለች ብዕሬ፤ ዛሬ ታንቀላፋለች ማለት ዘበት ነው። የአገሬን ልዕልና፤ የፍትህ የበላይነትን፤ የህዝቤን ነፃነትና ሠላም ሳታይ ላለማሸለብ ቃል ገብታለችና!!
ሳይማር ያስተማረኝ ወገኔ እዳ ስላለብኝ፤ እዳውን ቆጥሬ ባልከፈልውም፤ በመከራውና በችግሩ ወቅት አብሬው ዘብ መቆም፤ የሰብዕናዬ ምሰሶ ነው::
በአንፃሩ የአብይን ሰብዕና ጧትና ማታ የብርና የወርቅ ቀለም እየቀቡ፤ ሰማየ ሰማያት በማውጣት እየካቡ፤ አብይን አትንኩብን! ለምን ይተቻል? ለምን ይጠየቃል? ለተፈጠሩ ችግሮች ለምን ሃላፊነት ይወስዳል? ለሚሉን ያስተሳሰብ ድኩማን፤ ትላንት በመለስ አምልኮነት እንደተዘፈቃችሁ፤ ዛሬ ደግሞ በአብይ አምልኮ ላለመዘፈቅ፤ ከትላንቱ ስህተታችሁ ተማሩ እንልቸዋለን::
ሰዎችን ስናቀብጥ፤ የሌላቸውን ሰብዕና፤ በማጎናጸፍና በመካድ፤ ወደ አምባ ገነንነት በማሳደግ እናገዝፋቸዋለን:: እነሱም መሞገስ፤ መደነቅና መሞካሸትን ከከለመዱ፤ አልፈው ተርፈው ወደ አምልኩኝ ደረጃ ያሻቅባሉ:: ከዛም ከህግ በላይ በመሆን፤ በሚሠሩት በደልና ጥፋት፤ መጠየቅ፤ መተቸትና መወቀስ ይቀርና፤ ከተሰቀለበት የሚወርዱት፤ ወይ በግድ በህዝብ አመጽ ሲናደ፤ ወይ ሲሞቱ፤ ብቻ ይሆናል::
ከዚህ አይነቱ አደጋ የምንድነው፤ ዛሬ አብረን እጅ ለእጅ ተያይዘን፤ በጋራ ለአገራችንና ለህዝባችን ለደህንነት ዘብ ስንቆም ብቻ ነው:: ከአሁን በኋላ፤ ወይ ላይ እያንጋጠጡ፤ ከዚህ ሰውረን ማለቱ፤ አይሠራም! በጣም ረፍድዋል!!
እግዚአብሔርም ሰልችቶታል፤ እኛን በአምሳሉ በመፍጠሩ፤ ከማዘኑም በላይ፤ በስንፍናችን በእጅጉ ተጠይፎናል:: የበቀለ ገርባና የጃዋር መሃመድ የህወሓት ሎሌነት ማሳያዎች!
” ጃንደረባ ሎሌ በጌታው ሙርጥ ይኩራራል” እንዲሉ!
* በቀለ ገርባና: የጃዋር መሃመድ፤ ስለ የህወሓት አሽከርነታቸው፤ በራሳቸው አንደበት ከተናገሯቸው ጥቂቶቹን ልጥቀስ፤
– በቀለ ገርባ መቀሌ ድረስ ሄዶ ህወሓት ለእኛ ባለውለታችን ነው ስል፤ እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ ለዳግም ባርነት በእጩነት አቅርቧል:: (ለነገሩ ከራሱ በቀር ማንንም እንደማይወክል አገር ያውቃል)
– በለየለት ዘረኝነቱ፤ ሌላ ቋንቋ ከሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ጋር አብራችሁ አትገበያዩ ብል አውጇል::
– እንደ እኔ፤ ከሁለት ኢትዮጵያዊያን ቤተሰብ አብራክ፤ የተወለድን፣ ልጆችን አስጠቂዎች ሲል ወንጅልናል::
– የአዲስ አበባ ህዝብ እራሱ በመረጣቸው ተወካዮቹ መተዳደር አይችልም ሲል፤ የአዲስ አበቤዎችን መብት ሊደፈጠጥ ይፎክራል…………………….. ወዘተ.
* የጃዋር መሃመድ የለየለት የህወሓት አሽከርነት፤ ከራሱ አንደበት በግላጭ ሲታይ:
-“ደቡብም በምስራቅም ሄጃለሁ፡፡ብዙ ሰዎች ፈርተው አይናሩትም እንጅ አቋማቸው ከህወሃት የተለየ አይደለም፡፡ ፖለቲካ ያስተማሩኝም የብዙ ፓርቲዎች አመራር፣ ምሁራን፣ ወጣቶችም ጭምር በተለያየ ዘዴ አዋርቻቸዋለሁኝ፡፡ በይዘት ህወሃት የሚያራምደውን ፌደራሊዊ ፖለቲካ ይደግፋሉ፡፡ እኛም አሁን ከህወሃት ጋር የሚያጣላን የታክቲክም ሆነ የእስትራቴጂ ልዩነት የለም፡፡ ህወሃቶች ፌደራሊስቶች መሆናቸውን በተደጋጋሚ በተግባርም በአቋምም አሳይተዋል፡፡ ድሮ ብዙ ተባብለናል፡፡ ያለፈው አልፏል፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን በአብይ ዙሪያ ካለት ሰዎች መካከል አብይን ከልብ የሚደግፉ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው፡፡ በስም ሁሉ ልጠራቸው እችላለሁ፡፡ አሁን ኦሮሞ ማድረግ የሌለበት ለእስትራቴጅክ አጋሮቹ አጋርነቱን ማሳየት ነው፡፡ ሽማግሌም ቢሆን ልከን ዋናውን እስትራቴጅያዊ ወዳጅ አብሮን እንዲሰራ እንሞክር፡፡ አብይ ብቻውን ነው እየሄደ ያለው፡፡ እንደተናገርኩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው አጠገቡ ያለት፡፡”
ጃዋር መሃመድ በተለያየ ጊዜ የሚቀባጥረውን በሙሉ ትተን፤ ይህን አባባለን ብቻ ብንወስድ፤ ምን ያህል በህወሓት እግር ስር ተነጥፎ፤ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን፤ ዳግም የህወሓት ባሪያዎች ለማድረግ፤ ደጅ የሚጠና መሆኑን በደንብ እንረዳለን።
እንግዲህ ጃዋርና አጋሮቹ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን፤ ለህውሃት አንዱ ይሁዲ በስንት ብር ለመሸጥ እንደተዋዋለ ባናውቅም፤ ለመሸጥ መወሰናቸውን ግን በደንብ ነግርውናል::
ጠ/ም አብይ አህመድ ” ከወንድማችን ጃዋር መሃመድ ጋር አብረን እንሠራለን፤ አስፈላጊው ጥበቃም ይደረግለታል” ብል በይፋ የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ካስቀጠፈ፤ ብዙ ንብረት እንዲወድም ካስደረገና ለብዙ ቤተክርስትያናት መቃጠል ምክንያት ከሆነ ወንጀለኛ ጋር አብሮ የሚሠራ መሆኑን ነው፤ ሐረር ድረስ ሄዶ ያለ ሃፍረት የተናገረው።
ጠ/ም አብይ አህመዴ የሚጠየቅባቸው የራሱ የሆኑ የጎሉ ስህተቶች እንዲለ ሆኖ፤ አብይን ከለላ በማድረግ፤ አብረውት ያለ በማስመሰል፤ የህወሓትን፤ የዘርና የጎሣ ጥላቻ በማቀንቀን፤ አብይን ዋጋ በማስከፈል፤ በህዝብ ዘንድ ካስጠሉት በኋላ፤ ባገኙት ቀዳዳ ሾልከው ስልጣን ላይ ፊጢጥ ለማለት፤ የሚሯሯጡ የኦነግና የኦህዳዴ አንጃዎች፤ ብብቱ ውስጥ ተሰግስገው፤ አምኖ ተቀብሎት ከነበረው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ ሊያስፍቁት ጥቂት ቀናት ቀርቷቸዋል::
የጠ/ም አብይ አህመዴ ስህተቶች :
1) በግራ እጁ የህወሓትን ማኒፌስቶ አንግቦ፤ በቀኝ እጁ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ፤ አገር ልምራ ማለቱ፤
በግራ እጁ ያነገባት የህወሓት ማኒፌስቶ፤ የጥላቻ አብዮት ታማኝነት ዘብ መቆም አለብህ እያለች ስታስፈራራው፤ በቀኝ እጁ የያዘው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ፤ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችልም ይለዋል:: እናም አብይ በምርጫው ወይ ይድናል፤ ወይ ይጠፋል::
እኛም በትግላችን አብረን በጋራ ጸንተን በመቆም፤ አገራችንና እራሳችንን ከጥፋት እናድናለን፤ ወይም በዘርና በጎሣ ተነጣጥለን በመባላላት አብረን እንጠፋለን::
ምርጫው ለእሱም፤ ለእኛም በጋራ ቀርቧል::
2) የህግ የበላይነትን ለማስከበር ባለመቻል፤ በመላ አገሪቱ የተንሰራፋው ሥርአተ አልበኝነት::
3) በህዝብ ድምጽ ባይመረጥም፤ ለጊዜው የመላ አገሪቱ ዜጎች መሪ መሆኑን እያወቀ፤ ከዘርና የጎሣ ፖለቲከኞች ጋር ትከሻ ለትከሻ በመተሻሸት፤ አገሪቱን ወደ ብጥብጥ መክተቱ ::
4) የኦነግ/ኦህዳዴ ጥምር ዘረኞች በአዲስ አበባ ከተማ በኢሬቻ በዓል ዕለት የዘር ጥላቻ ፉከራ ሲያቅራሩ አደብ ግዙ በማለት ፋንታ፤ በዝምታ ይሁንታውን መስጠቱ ::
5) ያን ያህል ሰው በዘርና በጎሳ ብጥብጥ ሲሞት፤ ጠ/ም አብይ አህመድ ከሩሲያ ጉብኝቱን አቋርጦ ባለመመለሱ፤ ለአገሩ ክብር ከመንፈጉም በላይ፤ በሕዝባችን ልብ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ እንዲፈጠር አድርጓል::
የብዙ አገራት መሪዎች፤ በአገራቸው ውስጥ ችግር ሲፈጠር፤ እንኳን ይኸን ያህል ሰው ሞቶ፤ ወዲያውኑ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ አገራቸው በመመለስ፤ ከህዝባቸው ጋር ሃዘኑን ይካፈላሉ::
እሱ ግን፤ ምንም ነገር እንዳልተፈጸመ፤ ጉብኝቱን ቀጥልዋል:: ለመሆኑ የሄደበት ጉዳይ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደህንነት ፍለጋ፤ ወይስ እንደለመደው የራሱን ክብር (ለጋሲ) የብርና የወርቅ ቀለም ለመቀባት?!
– እንደተመለሰ የሞቱት ወገኖቻችን ክብር ሳይሰጥና፤ ሃዘኑን ሳይገልጽ፤ ሐረር ድረስ ሄዶ “ከወንድማችን ከጃዋር ጋር አብረን እንሠራለን፤ ጥበቃም ይደረግለታል” በማለት፤ የገዳዮችን ልብ ሲያደነድን፤ የኛን ልብ ክፉኛ ሰብሯል::
– ቀደም ብሎ በፓርላማ የተናገረውን ቃል ክዶ፤ “የሁለትአገር ዜግነት ያላችሁ” የሚለውን አባባል፤ በመኪና ጎማ መለወጫና፤ በጥበቃ አስመስሎ በመናገር አገሌ አራዳ ለመሆን በመመኮር፤ ሕዝብን ለማታለል ሞክሮ፤ አልገባንም ቢሉት፤ የሆነና ያልሆነውን ቀባጥሮ፤ ህዝቡን ሳይሆን፤ እራሱን ብቻ አታሎ መመለሱ ትልቅ ትዝብት ውስጥ ከቶታል::
– በእጅጉ ልብ ሰባሪ የሆነው የአብይ ድርጊት፤ ” በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት” እንዲሉ የሞቱት ወገኖቻችን በሙለ ኢትዮጵያዊያን ሆነው ሳለ፤ የሬሳ ዘር ቆጠራ ውስጥ ገብቶ፤ የሰጠው አሳፋሪ መግለጫ ሲሆን፤ ህሊና ካለው ጸጸቱ ህይወቱን ሙሉ እየተከተለ እንደሚያሳድደው አልጠራጠርም::
ሌላዋ የሂሳብ ስሌት ደግሞ፤ የዘርና የጎሣ ፖለቲከኞቹ፤ ከሌላው ዘርና ጎሣ፤ በይበልጥ የሞቱት፤ የኛ ዘሮች ወይም ጎሣዎች ናቸው ብሎ፤ ርካሽ የፖለቲካ ፍጆታ ለመቃረሚያ፤ የወረወራት የአፍ ልፋጭ መሆኗ ነው:: ይህን ደግሞ ጊዜው ወደ ፊት ያሳየናል::
– ለመሆኑ አብይ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ስንት ወገኖቻችን አለቁ?
– ስንቶቹ ተወልደውና አድገው ከኖሩበት ቦታ ተፈናቀሉ?
– ገና ስንቶች ይሙቱ?
– ስንቶች ይፈናቀሉ?
– አንገፍግፎን በቃ!! ለማለት፤ ስንትና ምን ዓይነት የሥልጣን ወንጀል በአገራችንና በዜጎቻችን ላይ ይፈጸም?!
መቋጫ
አንዱ ባሊ ሲገነጠል: በሌላው ላይ ተንጠልጠል ፤ እንዲሉ፤
እነዛው የትሊንቶቹ ፤ ህወሓት ጠፍጥፎ የፈጠራቸው፤ ኢህዲግ ተብዬ አባላት፤ የህዝባችን አሳሪዎች፤ ገራፊዎች፤ ገዲዮችና የአገር ሃብት ዘራፊ ሌቦች፤ ” የቀን ጅቦች ” ዛሬም ከያለበት ተጠራርተው፤ ኮታቸውን በመገልበጥ፤ እንደለመዱት፤ የቀረችውን የአገር ሃብት ሊዘርፉና፤ የዜጎችን መብት ሊደፈጥጡ፤ በድህነት ያደቃቋቸው ወገኖቻችንን መልሰው ሊግጡና፤ በብድር እስከ አንገቷ ያሰጠሟት አገራችንን፤ ከነ አካቴው ደፍቀው ለማስመጥ፤ በዕዳ ባቆራመዳት አገራችን ላይ ዳግም በለፀጋዎች ለመሆን፤ ” የብልጽግና ፓርቲ” እየተባባሉ ይሞዳሞዳሉ ::
ወደ 10 ሚሉዮን የሚጠጉ ወገኖቻችን በቅርብ ጊዜ ለረሃብና ለበሽታ እንደሚጋለጡ፤ ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅት ሰጪ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ፤ እነሱ በአገር ሃብት ስርቆትና ዘረፋ: ስለበለጸጋ ብቻ፤ ብልጽግና ሳይኖር ስለ ብልጽግና፤ ሠላም ሳይኖር: ስለ ሠላም፤ ዜጎች በሚከፍለት ግብር ወጪ፤ በሚተዲደሩ የዜና ማሰራጫዎች፤ በደሃ ወገኖቻችንን ላይ ጠዋትና ማታ፤ ያናፋሉ::
ዴንቄም ሠላም !! ዴንቄም ብልጽግና !! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
እግዚአብሔር፤ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !! ኅዳር 21 ቀን 1012 ዓ.ም (December 01/2019)
Most Popular
Archives
- December 2019
- November 2019
- January 2019
- December 2018
- November 2018
- October 2018
- September 2018
- August 2018
- July 2018
- June 2018
- May 2018
- April 2018
- March 2018
- February 2018
- January 2018
- December 2017
- November 2017
- October 2017
- September 2017
- August 2017
- July 2017
- June 2017
- May 2017
- April 2017
- March 2017
- February 2017
- January 2017
- December 2016
- November 2016
- October 2016
- September 2016
- August 2016
- July 2016
- June 2016
- May 2016
- April 2016
- March 2016
- February 2016
- January 2016
- December 2015
- November 2015
- October 2015
- September 2015
- August 2015
- July 2015
- June 2015
- May 2015
- April 2015
- March 2015
- February 2015
- January 2015
- December 2014
- November 2014
- October 2014
- September 2014
- August 2014
- July 2014
- June 2014
- May 2014
- April 2014
- March 2014
- February 2014
- January 2014
- December 2013
- November 2013
- October 2013
- September 2013
- August 2013
- July 2013
- June 2013
- May 2013
- April 2013
- March 2013
- February 2013
- January 2013
- December 2012
- November 2012
- October 2012
Archives
Categories
Events
- -
- 01/22/2013 - January 2013 TZTA Publication
- 01/18/2013 - TZTA Launches New Website