Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Ethiopian

በቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባለቤት-ሳባ

Published Posted on by | By TZTA News

በቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባለቤት-ሳባ

Spread the love

ከውስጥ አዋቂ ለዘ-ሐበሻ የተላከ መረጃ

በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረው መፈረካከስ ያሰጋቸው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ወደ ውጭ ማሸሹን ተያይዘውታል:: በሙስና እስር ስጋት ውስጥ ያሉት አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሐዬ ልጆች አሜሪካ ገብተዋል:: በሃገር ቤት የቀጠለው እርስ በ እርስ የሕወሓቶች መበላላት ጉዳዩ እስኪረጋጋ እዚህ ይቆያሉ:: ካልተረጋጉም እዚህ ያፈሩትን ንብረት ይዘው ይቀጥላሉ::

ከአባይ ጸሐዬ ልጆች መካከል አንዷ ቢቢ አንዷ ናት:: በአዲስ አበባ የ7 ህንጻዎች ባለቤት ናት:: በ እናት ከምትገናኛትና ለአባይ ጸሐዬ የ እንጀራ ልጅ ሳባ ጋር አብረው ዱባይ ቆይተው ሳባ ወደ ቻይና እንዲሁም ባቢ ከ12ቱ እህት ወንድሞቿ ጋር አሜሪካ ትገኛለች::(ዱባይ ውስጥ ስለነበረውና ስላለው ጉዳይ ወደፊት ሰፋ ያለ መረጃ ይቀርባል)

ትናንት በዘገባዎች ላይ ሳባ የአባይ ጸሐዬ ልጅ ተብላ ከተለጠፈች በኋላ የሥርዓቱ ሰዎች “ሳባ የአባይ ልጅ አይደለችም” ለማለት ቃትቷቸው ነበር:: የእንጀራ አባት እንደ አባት ካልተቆጠረ አዎ አባቷ ላይሆን ይችላል:: ግን የአባይ ጸሐዬ ልጅ እህት ናት:: ለዚህም ነው ስለዚህች ወጣት ሚሊየነር ነገሮችን መረጃዎችን እንድንፈለፍል ያደረገን::

ሳራ ከሞላ አስገዶምና ከጓደኞቹ ጋር በመሸታ ቤት

ሳባ ወዛመይ የተሰኘው የዳዊት ነጋ የሙዚቃ ክሊፕ ትግራይ ውስጥ የሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ተቀርጿል:: በክሊፑ ላይም ተውናለች:: በጓደኞቿ ዘንድ “የወርቅ ዘር” በሚል የምትታማው ሳባ ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነትን ካሸነፈ በኋላ ሳቢና የተሰኘው የሳባ ሬስቶራንት በቻይና የተሰኘ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ቻይና ውስጥ ተከፍቶላታል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብትና ንብረት በየመሸታ ቤቱ አርቲስቶችን በመጋበዝ ይበተናል::

ቻይና በርካታ የሕወሃት ባለስልጣናት ልጆች እንደሚማሩ ይታወቃል:: በዚሁ ቻይና ውስጥ አምባሳደር ሲሾም እንኳ የሚሾመው ከሕወሓት ተመርጦ ነው:: በቻይና የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ይመላለሳሉ:: ይህ ሬስቶራንት ነጋዴዎች የሚሰለሉበት እንደሆነ የሚናገሩት የውስጥ ምንጮች ከኢምባሲው ጋር ብዙ የሚሰራቸው ምስጢራዊ ጉዳዮች እንዳሉ ምንጮቹ ይናገራሉ:: አብዛኞቹም የሚሰሩት ምስጢራዊ ነገሮች እናንተ አንባቢዎች የምትገምቱት ዓይነት ነው::

ሳባ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጋር ግንኙነት አላት:: በሃገር ቤት አርቲስቶችን ባገኘች ቁጥርም በየመሸታ ቤቱ ጋባዥ እርሷ ናት:: ዱባይ በነበረችበት ወቅትም ተዋቂ ሰዎች እዚያ ሲመጡ ተቀባይና ሃገር አሳይ በመሆን ጀርባቸው ምን እንዳለ የምታጠናው እርሷ ነበረች እየተባለ በሰፊው መረጃዎች ይነገሩባታል::

ሳባ መቀሌ በነበረችበት ወቅት

ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገባው የትህዴን መሪ ሞላ አስገዶም ጋርም በተደጋጋሚ በየመሸታ ቤቱ መታየቷን የሚናገሩት ምንጮቹ ፎቶዎችን አስደግፈው ልከዋል:: ከሞላ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እስከምን ድረስ እንደሆነ የሚታወቅ ባይሆንም ሆኖም ግን አብረው በብዛት ታይተዋል::

ሳባ ዛሬ በስሟ ቻይና ውስጥ ሬስቶራንቱን ተከፍቶላት እየሰራች ነው:: የወደፊቱ የሕወሓት መሪዎች መኖሪያ በምትባለው ቻይና እንዲህ ያለው ሬስቶራንት መከፈቱ ጥቅሙ ለሕወሓት ሰዎች ሳይታለም የተፈታ ነው::

ቻይና ለንግድ የሚሄዱ ከሕወሓት ጋር ንክኪ የሌላቸው ነጋዴዎች ሊያስቡበት የሚገባውን ጉዳይ እዚህ ጋር ጠቆም አድርገናል:


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu