Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic, Ethiopian, World

በአሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ቀድሞ ጠፊውና አጥፊው ማን ይሆን?

Published Posted on by | By TZTA News

በአሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ቀድሞ ጠፊውና አጥፊው ማን ይሆን?

Spread the love

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በትናንትናው የመንግስታቱ ድርጅት 72ኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ አጋሮቻንና ህልውናዋን ለመከላከል “ሰሜን ኮሪያን እንዳለ ከማውደም በስተቀር ሌላ አማራጭ የላትም” ያሉ ሲሆን በማግስቱ ዛሬ ፒዮንጊያንግ በአጸፋ መልስ “አሜሪካ ቅንጣት ታህል የትንኮሳ እንቅስቃሴን ካደረገች ሰሜን ኮሪያ በቀድሞ ማጥቃት እርምጃ በኒውክሌር ቦምብ ቀድሜ ከምድረ ገጽ አጠፋታለሁ” ስትል ፈጣን መልስ የሰጠች ሲሆን መከላከያዋንም በተጠንቀቅ በማቆም የማጠናከሪያ ትእዛዝን አስተላልፋለች።

በአሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ሲካሄድ የነበረው የቃላት ጦርነት ለዓመታት የዘለቀ ቢሆንም የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ነገር ፒዮንጊያንግ ከሳምንታት በፊት ለስድስተኛ ግዜ በተሳካ ሁኔታ የሞከረችው የሃይድሮጂን ኒውክሌር ቦምብ ቴክኖሎጂ ከ1950ጀምሮ የህልውናዪ ጠላት ካለቻት አሜሪካ ጋር በኒውክሌር ውጊያ “አጠፋሻለሁ” የለም “እኔ አጠፋታለሁ”በሚል መገታተር ደረጃ በመድረሳ የሁለቱን ሀገራት በአንክሮና በጥልቀት እንድንከታተል አድርጎናል።

ሰሜን ኮሪያ ኢራቅ ወይም ሊቢያ አይደለችም አንዳችም ህዝብ ጨራሽ መሳሪያ ሳይኖራቸው በአሜሪካን ላይ የዛቻ ዶፍ ሲያዘንቡ ከርመውና በእውነተኛው የፍልሚያ ቀን አንዳችም ከባድ የጦር መሳሪያ በማጣት ወደ ትቢያነት እንደተለወጡት ገዢዎች በባዶ እጃ የምትደነፋ ሀገር ያልሆነች ሲሆን የታጠቀችው የኒውክሌር ቴክኖሎጂም በአሜሪካን ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ [ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሃላ ማለት ነው]የሀገሪቱ መሪ የኒውክሌር መሳሪያን በመጠቀም ፒዮንጊያንግን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ በማለት በተ.መ.ድ ፊት ቀርቦ እንዲናገር አድርጎታል።

በትናንትናው የተ.መ.ድ 72ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሀገራቸው በሰሜን ኮሪያ፣ኢራን፣ቭንዙዌላ፣ኪዩባና ሶሪያ ላይ የሚያራምዱትን ፖሊስ ይፋ ባደረጉበት ንግግራቸው ዙሪያ የተጠናቀረው ልዩ ዘገባ እንደሚከተለው ቀርባል።

***የትራምፕ አሜሪካ ትቅደም መፈክር አሜሪካዊያኑን እና ዓለምን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ-

በትናንትናው ንግግራቸው ትራምፕ የዋሺንግተንን ባለ አስር ነጥብ የተ.መ.ድ ማሻሺያ ሰነድን ይፋ ያደረጉበት ሲሆን ሰነፍዱ የድርጅቱን አገልግሎት፣ሃላፊነትና ተግባር ላለፉት ስድስት ዓስርተ ዓመታት ሲያደርጋቸው ከነበሩት ተግባራቶቹ ይበልጥ አሻሽሎና አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ተብሎ በፕሬዚዳንቱ የተገለጸና የ128ሀገራትን ፊርማ ያገኘ ቢሆንም ራሺያ፣ቻይና፣ብራዚል፣ደቡብ አፍሪካና ሌሎች ሀገሮች ግን አዲሱ የማሻሻያ ሰነድ ተ.መ.ድን ከዛሬው በባሰ ሁኔታ የአሜሪካን መጠቀሚያ የሚያደርግ በመሆኑ አንቀበልም በማለት ያልፈረሙ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ያልተቀበሉትን ወደ ገሀነብ የሚገቡ ብለዋቸዋል።

ተ.መ.ድ የአሜሪካንን ጥቅም አራማጅና አስጠባቂ ነው እየተባለ በከፍተኛ ትችት እየተተቸ ባለበት ሂደት የአሜሪካን ትቅደም ፍልስፍናን አራማጁ ትራምፕ “ያ-በቂዪ አይደለም” በሚል እምነት ድርጅቱን ይበልጥ የሀገራቸውን ጥቅም በማስጠበቅ መልኩ እንዲሻሻል ያረቀቁት ሰነድ የአሜሪካንን ብቸኛ ልእለ ሃይልነትን በጽኑ እየተቀናቀኑና ብሎም ሃያልነቱን ለመጋራት ከፍተኛ ዓላማና ትግል እያደረጉ ያሉትን ራሺያን እና ቻይናን በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ድርጅቱን ከአሜሪካን መዳፍ ለመታደግ እንዲታገሉ አድርጋቸዋል ሲሉ ተንታኞች የሚናገሩ ሲሆን ውጤቱም የተ.መ.ድ መሰንጠቅና ብሎም መፍረስን ያስከትላል ሲሉ ይናገራሉ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በስድስቱ ሃያላን ሀገራት [አሜሪካ፣ራሺያ፣ቻይና፣እንግሊዝ፣ፈረንሳይና ጀርመን]እና ኢራን መካከል የተካሄደውን የኒውክሌር ስምምነት ለማፍረስ ገና በምረጡኝ ዘመቻቸው ላይ እያሉ ሲዝቱ የነበረ ቢሆንም በትናትናው ንግግራቸው “እጅግ አሳፋሪና አሜሪካ የማትቀበለው”በማለት ስምምነቱን ለማፍረስ ዛሬም እያለሙ እንዳሉ ይፋ ያደረጉ ሲሆን በድርድሩ ውስጥ ተሳታፊ ካልሆነችው እስራኤል በስተቀር አምስቱም አደራዳሪ ሃያላን ሀገራት የዋሽንግተንን አዲስ አቃም በመሪዎቻቸው በኩል እንደማይቀበሉና እንደማይደግፉ ይፋ አድርገዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ ለክልላዊ የበላይነት እየተካሄደ ባለው ውስብስብ ግን እጅግ ደም አፋሳሽ ጦርነት የሞስኮ አጋር የሆነችው ኢራን በሶሪያ፣በኢራቅ፣በየመን እና በሊባኖስ እስከ ሚዴቴራኒያን ባህር ያዘረጋችው ተጽእኖ ፈጣሪ ሃይል ለአጋሮቻቸው እስራኤልና ሳኡዲ ዓረቢያ እጅግ የሚያሰጋ በመሆኑ የኢራን ኒውክሌር ስምምነትን እሰርዛለሁ በማለት ቴህራንን በቀጠናው የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታቆም ሊደራደሩበት የቀረበ ስልት ነው ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ።

ሆኖም በሁለቱም አቅጣጫ ማለትም የኒውክሌር ስምምነቱን በማፍረስም ሆነ የቴህራንን በክልሉ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለማቆም መስማማትን ከኢራን እሺታን ከአምስቱ ሃያላን ደግሞ ድጋፍን ስለማያስገኝላቸው ከሁለት አንዱን በተናጥል ሃይል በመጠቀም እርምጃ ይወስዱ ይሆናል ተብሎ የሚታመን ሲሆን የሚከፍሉት ዋጋ ግን ከባድ ነው ሲሉ ዲፕሎማቶች ይናገራሉ።

**የዋሽንግተን እና ፒዮንጊያንግ ፍጥጫ-የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ምርጫ

ስድስተኛው የኒውክሌር ሙከራ ውጤታማነት ስሜን ኮሪያ የኒውክሌር መሳሪያ ቴክኖሎጂን የታጠቀች ሀገር በማድረግ ወደ ማህበሩ አባልነት እንድትገባ ቢያደርጋትም የዋሽንግተን ስር የሰደደ የጠላትነት አቃም፣ጥላቻና ፒዮንጊያንግን እንደ የኒውክሌር ባለቤት አድርጎ የመቀበል ፍላጎት ጭራሹኑ አለመኖር ለስድስት ዓድርተ ዓመታት የቆየውን ፍጥጫ ወደ ለየለት ጦርነት ደረጃ ሳያደርስ አይቀርም ተብሎ ተገምታል።

የ33ዓመቱ ወጣትና ቁርጠኛ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ አን ሀገሩን እና ህዝቡን ለዓመታት ከታፈኑበት ማእቀብና ከዓለም መገለል በማንኛውም መስዋእትነት ሰብሮ ለመውጣት መወሰን በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ በስተቀር ሁሉም ወደ ሃላ ይቅር[የአሜሪካ ትቅደም ፍልስፍና ውጤት ማለት ነው]የጸና አቃም ሁሉቱንም ሃይሎች ሳይፈልጉ ወደ ሁሉን አቀፍ ጦርነት ደረጃ ሊያደርሳቸው ይችላል ተብሎ ይገመታል።
የዓለማችን ልእለ ሃያል ሀገር መሪ በመሆን አንድን ሀገር ሙሉ በሙሉ ከማጥፋት በስተቀር ምንም የተሻለ አማራጭ የለንም በማለት የመጀመርያው የሆኑት ትራምፕ ፒዮንጊያንግ ለዛቻቸው [ a pre-emptive strike if they show “any slight sign of provocation] አንዳች የትንኮሳ ምልክትን ካሳዩን በቀድሞ ማጥቃት በኒውክሌር መሳሪያችን አሜሪካንን ሙሉ በሙሉ ወደ ትቢያነት እንለውጣለን ስትል እጅግ መረርና ተከታታይነት ያለው ዛቻ ሰንዝራለች።
የሰሜን ኮሪያ ስድስተኛው የህይድሮጂን ኒውክሌር ቦምብ ቴክኖሎጂ ከሌላኛው የኒውክሌር ቦምብ የረቀቀና የተለየ እንደሆነ ሳይቲስቶች እያብራሩ ሲሆን መስረታዊ ልዩነቶቹም የሃይድሮጂን ኒውክሌር ቦምብ ቴክኖሎጂ በተፈለገ መጠን እና በአህጉር ተሻጋሪ ባላስቲክ ሚሳዪል አናት [እንደ አረር]በመጫን ያለተካሽ ተዋጊ አይሮፕላን የትኛውንም የዓለም ክፍል ማጥቃት መቻሉ ሲሆን ሰሜን ኮሪያ ቀደም ሲል ባመረተቻቸው አህጉር ተሻጋሪ ባለስቲክ ሚሳዪሎቻ አማካይነት አሜሪካንን መደብደብ እንደሚያስችላት ተገልጻል።

ፒዮንጊያንግ ባለፈው ሳምንት በስኬት የሞከረችው የሃይድሮጂን ኒውክሌር ቦምብ አሜሪካ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለቂያ ላይ በጃፓን ሂሮሺማ ከጣለችውና ከ80ሺህ በላይ ሰዎችን ከፈጀው አቶሚክ ቦምብ 10እጥፍ እንደሚበልጥ ሳይቲስቶች ተናግረዋል።
ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው እንደሚሉት በመጥፋት ደረጃ ሰሜን ኮሪያዊያን የዘመናት ጠላታቸውን አሜሪካን አጥፍተው ቢጠፉ የሚቆጩ አይመስሉም።ትራምፕ እንዳሉት ባለሮኬቱ ኪም በአጥፍቶ መጥፋት ዓላማ ላይ ያለ መሪና ሕዝብ የመሆኑ ትክክለኛነት ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ከእውነት የራቀ እንዳልሆነ መረዳት የሚቻል ሲሆን አሜሪካ ግን ፒዮንጊያንግን ያለምንም ክፍያ እንደ ጃፓን፣ኢራቅ ምንም ሳትሆን [የፐርል ሃርበሩ ጥቃት ከኒውክሌር ጥቃት ጋር ሲነጻጸር ውድመቱ አንሶ እናየወለን]የምታጠፋት ሀገር ሳትሆን የዓለም ሃያልነታን ስፍራ በሚያስገርም ሁኔታ የምታጣበት ጦርነት እንደሚሆን ለመተንበይ ጠንቃይነትን መላበስ አይጠይቅም።

ሁለቱ ሃያላን የሰሜን ኮሪያ ጎረቤቶች ራሺያና ቻይና በአካባቢያቸው የኒውክሌር ጥፋት እንዲከሰት እንደማይፈቅዱ ደጋግመው አቃማቸውን ግልጽ ያደረጉ ሲሆን በ1950ዎቹ የኮሪያ ጦርነት ሁሉቱም ሀገሮች ከሰሜን ኮሪያ ጋር ተሰልፈው አሜሪካንን እና ምእራባዊያንን የተዋጉ ሲሆን ቻይና ብቻ ወደ ፒዮንጊያንግ ከላከቻቸው 1ሚሊዮን ወታደሮቻ ውስጥ 400ሺህ ያህሉ መስዋእት እንደሆኑባት ይታወቃል።

ልእለ ሃያልነቱን በአሜሪካን የተነጠቀችውና ዛሬ ለማስመለስ እየታገለች ያለችው ራሺያ ወደ ጦርነቱ የምትገባበት ብዙ አስገዳጅ ክስተቶች በቅድመ ሁኔታ ተጠናቀው ግዜያቸውን እየተጠባበቁ ባለበት ሁኔታ አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ላይ ጦርነት ብትከፍት በእርግጥ ሀገሪቱን ድምጥማጥን ማጥፋት እንደምትችል ቢታወቅም የደቡብ ኮሪያን፣የጃፓንን እና የራሳን ልእለ ሃያልነትን ገብራ በመሆኑ ይህንን ጦርነት ከሁለቱ መሪዎች [ትራምፕ እና ኪም]መካከል ቀድሞ የሚጀምረው እጅግ የመረረውና የአእምሮ መዛባት ያለበት መሪ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ማን ይሆን ከሁለቱ መሪዎች የአእምሮ መዛባት ያለበት?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በሰሜን ኮሪያ ላይ የተ.መ.ድን የሃይል እርምጃ ውሳኔ እነ ራሺያና ቻይና ባሉበት ሊያገኙ ያለመቻላቸው ሁኔታ ውሳኔያቸውን በተናጥል እንዲወስዱ የመገደዳቸው ሂደት ከሰሜን ኮሪያ ጀርባ ያሉትን ራሺያን እና ቻይናን በይፋ በጸረ አሜሪካን ግንባር እንዲሰለፉ ያስገድዳቸዋል-ትራምፕም የአሜሪካንን ትቅደም ፍልስፍና እውን ለማድረግ ከእነዚህ ሁሉ ሃይሎች ጋር ኢኮኖሚያዊ፣ዲፕሎማሲያዊና ብሎም ገሀዳዊ ፍልሚያ እንዲያካሂዱ የሚገደዱ በመሆናቸው እንደ ሂትለር ጀርመንን ሃያል አደርጋለሁ ብሎ እንዳወደመው አሜሪካም የዛሬው ሃይልነታ አልበቃ ብሎኛል ብላ ስትፋልል ያላትን ደረጃ እንዳታጣ መካሪ ሳያስፈልጋት አይቀርም።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu