Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News, Breaking News Amharic, Canadian, Ethiopian, World

ትዝታ ጋዜጣ ለአቶ ሳሙኤል ያላት ክብር ከፍተኛ ነው።

Published Posted on by | By TZTA News

ትዝታ ጋዜጣ ለአቶ ሳሙኤል ያላት ክብር ከፍተኛ ነው።

Spread the love

የአቶ ሳሙኤል ፈረንጅ የሕይወት ታሪክ በአጭሩ በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ተገልጽዋል። ወደዚያ አልመለስም። የኔ ዋና ትኩረት አቶ ሳሙኤል ወደ ካናዳ ከመጡ በህዋላ በተለይ ከትዝታ ጋዜጣ ጋር ያደርጉትን ታላቅ አስተዋጾ በአጭሩ ለመግለጽ ነው።

አቶ ሳሙኤል ፈረንጂ ታላቅ ክብር የሚሰጣቸው ሰው ነበሩ። ምክንያቱም ከ12 ዓመት በፊት ያልታሰበ በሽታ እጃቸውን እስከያዘው ድረስ በተቻላቸው መጠን ለራሳቸው ዝና፣ ሥልጣን፣ ገንዘብ ሳይሉ በቅንነት ግለሰቦችን ህብረተሰቡን ያገለገሉ በመሆናቸው ነበር።

በቶሮንቶ ከተማ በ1992 ዓ.ም. ሐምሌ ወር የመጀምሪያው መጽሔታንን “ኢትዮጵያን ላይፍ” በሚጀመርበት ጊዜ ነበር የተዋወቅነው፤ እናም በማማከር፣ ጽሁፎችን፣ ግጥሞችን፣ የተለያዩ የትምህርት ሰጪ ሃሳቦችን በመጻፍ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተው፣ በ1996 ዓ.ም. የትዝታ መጽሄት መታተም ከጀመረበት አንስቶ ከዚያም በ1998 ዓ.ም. የመጽሔት ህትመት ወደ ጋዜጣ ሕትመት ከተቀየረ በህዋላ ያለማቅዋረጥ ይሀ ነው የማይባል ቅዋሚ አገልግሎታቸውንና መስዋእትነታቸውን የሳዩበት፣ የገለጹበት መሆኑን ከጻፉት መረጃ ባሻገር ደግሞ የትዝታ ጋዜጣ አማኝነትዋን ትገልፃለች።

አቶ ሳሙኤል ከመኝታቸው በጣም በጠዋት ይነሱና የሚጽፉት ካለ ይጽፉና ወደ እኛ ስልክ በመደወል ጋዜጠኛ እኮ አይተኛም! የሚሉንና የሞራል ድጋፍ የሚሰጡን፣ እንዲሁም የተለያዩ ሃሳቦችን በመጠቆም ይህቺ ጋዜጣችን የምታድግበትንና ከድሆሽ በእግርዋ የምትራመድበትን መሰላሎች በርትተን መዘርጋት እንዳለብንና ለኮሞኒቲያችን ዋና ትንፋሽ ነው እያሉ ጠዋት ማታ ቅስቀሳ የሚያደርጉልን ነበሩ።

አቶ ሳሙኤል ፍጹም ኢትዮጵያዊና ለሃገራቸውና ለወገናቸው ደህንነት ዘለአለም ተቆርቅዋሪ፣ በየጊዜው መሻሻልን የሚያሰላሰሉ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።

አቶ ሳሙኤል ፍጹም የገንዘብ ፍቅር የማያሸንፋቸው፣ ይህን ለራሴ የማይሉና በዚህ በኩል እንጠቀማቸው፣ እንርዳቸው፣ እንድርስላቸው፣ እናድርግላቸው እንጂ ባንጻሩ እኔን እርዱኝ፣ እኔን ጥቀሙኝ የሚባል ነገረ እርሳቸው ጋር ፍጹም አልነበረም። ለራሳቸውም ግድ የሌላቸው ነገር ግን ለኮሚኒቲ፣ ለወጣቶች ክበብ ኢትዮጵያውያንን በሚመለከት ሁሉ የሚረዱና የማይደክሙ ጠንካራ ሰው ነበሩ።

አቶ ሳሙኤል ባህሪያቸው በራሳቸው የሚተማመኑ፣ የራሳቸው መንገድ ያላቸው፣ ከፍተኛ የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመሳል፣ የመፍጠር ችሎታቸው የላቀ ሲሆን ለምሳሌ ያህል የተለያዩ የአማርኛ ሆነ የእንግሊዘኛ ጽሑፎችን አንብቦ ተረድቶ ኢዲት በማድረግ ፈጣን ሲሆኑ እውቀጣቸው የማይነጥፍ ምንጭ ነበር።

አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ በአንድ ወቅት ለልእልት ድያና (In Memoriam) በሚል አርእስት የደረሱት የእንግሊዘኛ ቅዋንቅዋ የሃዘን እንጉርጉሮ በሰሜን አሜሪካ የግጥም ውድድር ሽልማት ማግኘታቸውን በትዝታ ጋዜጣ መውጣቱ ይታወሳል።

ስለሆነም ስለዚህ ሽልማት እንዴት እንዳገኙ ጠይቀናቸው ሲመልሱ፤ “እርግጥ ለውድድር በራስ መተማመን ይጠይቃል። ማሸነፍ ደግሞ ደስታን ያጎናጽፋል። እኔ ደቂቅ የእናት ቅዋንቅዋዬ ባልሆነ እንግሊዘኛ ተወዳድሬ ሳሸንፍ ድሉ ለእኔ ደቂቁ ሰው ሳይሆን ሙሉ ክብሩ ከልጅነት ጅምሮ የማደንቃቸውና የማከብራቸው ክቡር አቶ ከበደ ሚካኤልና የግጥም ፍቅር በውስጤ ለፈጠሩት ታላቁ መምህሬ አቶ ለገሠ በሱፈቃድ ናቸው።” ብለው አውስተውናል።

በመቀጠልም ባጭሩ ከዚህ በፊት ሌላ ሽልማት መሸለማቸውን ጠይቀናቸው እርሳቸውም ሲመልሱ፣ ቀድም ብየ በሙያዬ የአክልሆማ ገቨርነርና የስቴት ምክር ቤት የአክልሆማ የክብር ዜግነት ሰጥቶኛል። በረዥም ዘመን አገልግሎቴ ከተለያዩ አስራ ሰባት የዓለም መሪዎች አስራ ሰባት የክብር ሊሻኖች ከመሸለሜ ሌላ በ1970 ዓ.ም. (እ.ኢ.አ.) የኢጣሊያ ሪፓብሊክ የ”ኮሜንዳቶሬ ዴላ ሪፓብሊክ ማእረግ ተቀብያለሁ። እንደዚሁም “TIME” የተባለው የአለም አቀፍ መጽሔት “የአመቱ ታላላቅ ሰዎች” ብሎ ስለመረጣቸው አራት መሪዎች ለመጽሄት ከተላኩት ሺህዎቹ ያንባብያን ደብዳቤዎች መካከል ተመርጠው በመጽሄት የJanuary 17, 1994 እትም ሲወጣ ከርሱ መካከል የኔ ጽሑፍ “የምርጥ ምርጥ” ተብሎ በአንደኝነት በጉልህ ታትሞ ወጥትዋል።” ብለው አጫውተውናል። ስለሆነም የርሳቸው አስተዋጽኦ መልካም ሥራ፣ ቅንነትና ሽልማት የሚያኮራን ለትዝታ ጋዜጣ የምናዘጋጀው ብቻ ሳይሆን ለመላው ዜጋዎችና ወገኖች ነው ብለን እናምናለን።

አቶ ሳሙኤል ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በተለይ የኢትዮጵያን ታሪክ በተመለከተ ብዙ ጽሑፎችን ለትዝታ ጋዜጣ አቅርበዋል። ለምሳሌ ያህል ጠቅለል ባለ ሁኔታ ብንመለከት፦

የአፄ ቴዎድሮስ ጀግንነትን፣ የአፄ ሚኒልክን አስተዋይነትን፣ የአፄ ሃይለስላሴ ብልህነትን፣ የደርግ

ን የኢህድግን ሁኔታዎች በተለያየ መልኩ ቁልጭ አድርገው ጽፈዋል፣ ተችተዋል፣ተንትነዋል፣ አስተምረዋል። በተለይም የአድዋና የማይጨው ጦርነቶች በተመለከተ ብዙ ዘክረዋል።

የአገራችንን የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና ሃይማኖት በይበልጥ ጠልቀው ስለተረዱ በተለያየ መልኩ በጋዜጣ አስፍረዋል።

ስለ ተለያዩ ግለሰቦች፣ ባለሙያዎች፣ ምሁሮች፣ ባለሥልጣኖች ብዙ ጽፈዋል፣ ተችተዋል፣ አሳውቀዋል፣ አጋልጠዋል።

የስደት ዓለም ምን እንደሆነ በባህል ላይ ያለው ተጸኖ የሚያስከትለውን ውጤት አሳውቀዋል። አስተምረዋል።

በእንግሊዘኛ ቅዋንቅዋም ስሑፎችን፣ ግጥሞችን፣ ታሪኮችን ለማሳወቅ ጥረዋል።

ቀልድና ጨዋታ በተመለከተ እንደዚሁ በግጥም፣ በቅኔ አንባብያንን አዝናንተዋል።

ቀደም ያሉ ትንቢት ተናጋሪ ባለታሪኮች የጻፉትን ጽሑፍ ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር በማያያዝና በማገናዘብ ዘክረዋል።

በዚህ በካናዳ ያሉ ወጣቶች የሃገራቸውን ባህል እንዳይረሱ እንዲሰባሰቡ በግጥም፣ ሥንጽሑፍ ከባዕድ አገር መጥፎ ጸባዮች አግዋጉል ልምዶች እንዳይቀስሙና እንዳይገቡ ብዙ ጽፈዋል አስረድተዋል።

በመጨረሻም የትዝታ አዘጋጅ ለአቶ ሳሙኤል ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው በጣም በማዘን ለቤተሰብና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

አመሰግናለሁ

የትዝታ ጋዜጣ አዘጋጅ                                                                                                                    ተሾመ ወልደአማኑኤል                                                                                                       https::/www.tzta.ca


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu