Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News, Breaking News Amharic, Ethiopian, Recent Videos, Video, World

ኦሮምያዉ ህዝባዊ እምቢተኝነት እስከ ህዝባዊ ነጻነት (ዶ/ር መራራ ጉዲና በቢ.ቢ.ኤን. )

Published Posted on by | By TZTA News

ኦሮምያዉ ህዝባዊ እምቢተኝነት እስከ ህዝባዊ ነጻነት (ዶ/ር መራራ ጉዲና በቢ.ቢ.ኤን. )

የኦሮምያ ህዝባዊ እምቢተኝነት ቀጥሏል፥ኦሮምያ በሙሉ የሚሳተፍበት ታላቅ ሰልፍ ተጠርቷል • ህወሃትም ንጹኋንን መግደሉን አላቆመም።ህዝቡም መታገሉን አላቆመም።በስተመጫረሻ ቀጥ ብሎ የሚቆመዉ የጨቋኞች ሴራ እንጂ የህዝብ ፍላጎትና ምርጫ አይሆንም። ቢቢኤን ሐምሌ 26/2008 #OromoProtests ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የተሰዉለት የኦሮምያ ህዝባዊ ንቅናቄ እንደቀጠለ ነዉ። የኦሮምያ ህዝብ ድምጹን በሰላማዊ መንገድ የሚያሰማ ቢሆንም ህወሃት የንጹኋን የኦሮምያ ተወላጆችን ደም በጎዳና ላይ እያፈሰሰ ይገኛል። ባለፉት ሐያ አራት ሰዓታት ዉስጥ የአንድ አመት ህጻንን ጨምሮ በርካቶች ሲቆስሉ ቁጥራቸዉ እስከ 13 የሚደርስ ንጹኋን ዜጎች በአጋዚ ጥይት መገደላቸዉን የኦሮምያ ህዝባዊ እምቢተኝነት አንቀሳቃሾች አሳዉቀዋቅል። ህገ ወጥ የሆነዉን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተከትሎ የተቀጣጠለዉ የኦሮምያ ህዛባዊ እምቢተኝነት ባሰበት እንጂ አልበረደም። በግፍ መገደል፣በግፍ መታሰር፣በግፍ መደብደብና መሰደድ የኦሮሚያን ህዝብ የነጻነት ጥማት አናረዉ እንጂ በህዝቡ ላይ ፍርሃትን አልጫነም። «እምቢኝ ለመብቴ! እምቢኝ ለነጻነቴ!» ያሉ የኦሮምያ ተወላጆች በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ስር ባሉ ቦታዎች ላይ አደባባይ ወጥተዉ ተሰለፉ። ድምጻቸዉን አምባገነናዊ መንግስት ይሰማ ዘንድ ጠየቁ።ህገ መንግስት ይከበር ዘንድ አሳሰቡ። የታሰሩ ይፈቱ ዘንድ ጠየቁ።ግፉ መከራዉ ይበቃ ዘንድ አሳሰቡ። ምላሹ ግን የንጹኋንን ደም በኦሮምያ መሬት ላይ ማፍሰስ ሆነ። «እያለን እንደሌለን፣እየተቆጠርን እንዳልተቆጠርን፣ሐብታችን እየተዘረፈ ለቅምጥል የህወሃት ማፍያዎች መሰጠቱ ያበቃል።ድላችን በልጆቻችን የህይወት ዘመን ሳይሆን በኛ የህይወት ዘመን ይፋ ይሆናል» ያሉ የኦሮምያ ተወላጆች እምቢኝ አሻፈረኝ ብለዉ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን አፋፍመዉታል። በምስራቅ ሐረጌ በደዳር ህዝብ ተሰባስቦ ወጥቶ በመሰለፍ ድምጹን አሰምቷል።የምስራቅ ሀረጌዋ ሶቃ ነዋሪዎች ተሰልፈዋል። በምእራብ ሐረጌ ከቆቦ ወደ ድሬዳዋ የሚያመራዉ መንገድ በተቃዉሞ ተዘግቶ እንደነበር የኦሮምያ ህዝባዊ እምቢተኝነት አንቀሳቃሾች አሳዉቀዋል። በደዳር ምስራቅ ሐረጌ ዉስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች መንገድ ላይ ወጥተዉ የትግል ባንዲራን እያዉለበለቡ ድምጻቸዉን አሰምተዋል። በደዳር የአጋዚ ጦር በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈቱም ታዉቋል። በሐረማያ አካባቢ የአራዳ ሀቃ አርሶ አደሮች ያላቸዉን ጽኑ የትግል መንፈስ ለማመላከት ተሰልፈዉ አጋዚን ላሰማራዉ ህወሃት ጠንካራ መልእክታቸዉን አሰምተዋል። ከምስራቅና ከምእራብ ሐረጌ በትግል መንፈስ የማትነጠላዋ ደንበል ባሌ ላይ ሰልፍ ተደርጓል። ተመሳሳይ የሆነ የትግል መንፈስ፤ ተመሳሳይ የሆነ የአላማ መስተጻምር በመላዉ ኦሮምያ ታይቷል። የኦሮሞ ህዝብ የሚያደርጋቸዉ ጥረቶች በሙሉ ሰላማዊና ህገ መንግስታዊ ቢሆኑም እንደ ማፍያ እና አሸባሪ የሚንቀሳቀሰዉ ህወሃት ንጹሃን ዜጎችን መግደሉን መርጧል።ቢቢኤን ከኦሮምያ ህዝባዊ እምቢተኝነት አንቀሳቃሾች ባገኘዉ መረጃ መሰረት ባለፉት ሁለት ቀናት ዉስጥ በአወዳይ 9 ሰዎች በአጋዚ ጥይት ተመተዉ ሲገደሉ ሌሎች 4 ሰዎች በበዴሳ በተመሳሳይ መልኩ በአጋዚ ጥይት ተገድለዋል። ለነጻነት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል ። ባለፈዉ እሁድ በጎንደር ዉስጥ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የጎደር ህዝብ በኦሮምያ ጎዳኖች ላይ የሚፈሰዉ የኦሮሞ ወገኖቻችን ደም የኛም ደም ነዉ ሲል አጋርነቱን አሳይቷል። ለአመታት በእስር ሲንገላቱ ቆይተዉ ከተፈቱ በኋላ በድጋሚ የታስሩትን በኦሮምያ ህዝብ ዘንድ እጅጉን በመብት ተሟጋችነታቸው የሚታወቁት አቶ በቀለ ገርባ መታሰርን የጎንደር ህዝብ አዉግዟል። የጎንደርን ሰልፍ ተከትሎ ሰልፍ ያደረጉ የአወዳይና የበዴሳ ነዋሪዎች በአጋዚ ጥይት ተመተዉ እንዲሞቱ መደረጋቸዉ ከፍተኛ ቁጭትን ፈጥሯል። ህዝቡ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ የተነሳ ይመስላል። የፍርሃት ካብ ተደርምሷል። የኦሮምያ ህዝባዊ እንቢተኝነት አንቀሳቃሾች በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚደርሰዉን መከራና ስቃይ ለማዉገዝ አምባገነናዊዉን መንግስት በሰላማዊ መንገድ እናስጠነቅቃለን በማለት ታላቅ አገር አቀፍ ሰልፍ በመላዉ ኦሮምያ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 30/2008 ጠርተዋል። ሰልፉ በኦሮምያ ዉስጥ ያሉ የምንኛዉንም እምነት ተከታዮችና ብሔር ብሔረሰቦች ያካተተ መሆኑን የኦሮምያ ህዝባዊ እምቢተኝነት አንቀሳቃሾች ለቢቢኤን ገልጸዋል። የቅዳሜዉ ሰልፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦሮምያ ተዋላጆችና በኦሮምያ ዉስጥ የሚኖሩ ዜጎች የሚሳተፉበት በመሆኑ በአገሪቷ ዉስጥ ወሳኝ የሆነ ለዉጥ ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ህዝባዊ እምቢተኝነት አንቀሳቃሾች አሳዉቀዋል። በሰልፉ ላይ የህወሃት ደህንነቶች ችግር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ህዝባዊ እምቢተኝነት አንቀሳቃሾች ገልጸዋል።ሰልፉ በሁሉም የኦሮምያ ወረዳዎችና ከተሞች እንደሚካሔድ ያሳወቁት አዘጋጆች ሰልፉ ሰላማዊ ብቻ እንደሚሆን አሳዉቀዋል። የጦር መሳሪያ ወደ ስልፉ ይዞ መምጣት አይቻልም፣መንገድ አይዘጋም፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ሰራተኖች ላይ ጫና አይደረግም፣ በንብረትና በይዞታ ላይ ጥቃት አይፈጸምም በማለት የሰልፉ አዘጋጆች አሳዉቀዋል። በስልፉ ላይ ለመሳተፍ የሚመጣዉ ሁላ ተረጋግቶ መሔድ አለበት፣መቸኮልና መሮጥ አስፈላጊ አይደለም፣ በትላልቅ ከተሞች ህዝብ ሊሰባሰብባቸዉ የሚችልባቸዉ ቦታዎች ታዉቀዉና ተለይተዉ ለህዝቡ መረጃ ሊደርስ ይገባል በማለት አዘጋጆቹ አሳዉቀዋል። ለሐያ አመስት አመታት ኢትዮጵያን በአምባገናዊነት ሲገዛ የቆየዉ ህውሃት መራሹ መንግስት የማያዉቀዉ አይነት ተቃዉሞ እየገጠመዉ ነዉ። የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገዉ ተቃዉሞ የኦሮሞ ህዝብ ብሶትና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ቢሆንም አገሪቷ ዉስጥ በገሃድ የሚታየዉ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መብቴ ይከበርልኝ ጥያቄና በህገ መንግስት የተረጋገጠዉ የእምነት ነጻነት አለመከበር በዚሁ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ አካል እንደሚሆንም ቢቢአኤን ለማወቅ ችሏል።ህዝቡ በመልካዓ ምድራዊ አቀማምመጥ የተራራቀ ቢሆንም በደም የተሳሳረ በአላማ የተቀናጀ መሆኑን የቅዳሜዉ የኦሮምያ ሰልፍ ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል። የቅዳሜዉን ስልፍ እንቀላቀልና የድሉን ጉዞ እናፍጥነዉ የሚሉ ጥሪዎች እየቀረቡ ነዉ። በመጪዉ ቅዳሜ የኢትዮጵያ ጎዳኖች በሙሉ ወደ ድል ደጃፍ ያመራሉ።ህዝበ በድል ደጃፍ ላይ ሲጓዝ አብረን መጓዝ አለብን። የድሉን ጎዳና ለ አመታት ጠርገናል። አሁን ከኛ የሚጠበቀዉ ብቸኛው መዉጫችን ወደ ሆነዉ ድላችን ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር በመሆን አብረን መነሳት ነዉ። ጎንደር በድል ጎዳና በቁርጠኝነት ተሟል።ባህርዳር በድል ጎዳና ላይ ሊጓዝ መሰናዶዉን እያጠናቀቀ ነዉ። መላዉ ኦሮምያ ላይ ያሉ ጎዳናዎች በሙሉ ወደ ድል ደጃፍ የሚያመሩ ይሆናሉ። የኦሮምያዉና የባህርዳሩን የድል ጉዞ በመቀላቀል ከወደ ድል ደጃፍ እንድረስ። ጨቋኞች በመጨረሻ የእድሜ ጣራ ላይ ስለሆኑ የድሉ አካል መሆኑ ግዴታ ነዉና የጀመርነዉን ለመጨረስ እንነሳ። የሚል የትግል ቁርኝት እየተስተዋለ ነዉ። ህዝብ አሸናፊ ነዉ።ጨቋኞች ተሸናፊናቸዉና ማንም የማይበደልባትን፣ማንም የማይጨቆንባትን አዲሲቷን አገራችንን ለመገንባት አብረን እንነሳ የሚል ጥሪ ቀርባል። የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ ሰላሳ፣ ህዝቡ በአንድነት ሲነሳ፣ቀኗ ትሆናለች የጭቋኞች አበሳ የሚል ህዝባዊ ድምጽ ያስተጋባል። ሳዲቅ አህመድ ነኝ ልብ ያለዉ ልብ ይበል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu