Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Ethiopian

‹‹ ዘጠኝ ሞት መጣ ቢለው አንዱን ግባ አለው!!! ›› ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

Published Posted on by | By TZTA News
Spread the love


ሶሎሜ!!!
‹‹ሊያባሉንና ሊያጫርሱን ለተዘጋጁት የቀን ጅቦች ዕድል ልንሰጣቸው አይገባም!!!›› ዶክተር አብይ አህመድ
የዓየር ኃይል የጦር አይሮፕላኖች ከውቅሮ ብሸፍቱ ይመለሱ! የኢትዮጵያ ታንኮች አዳማ ይመለሱ! የጦር መሣሪያ ግምዣ ቤት ቤቱ ይመለስ!
አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ ከሱማሌ ክልል ተፈናቅለዋል!!! ግማሽ ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ከተለያዮ ክልሎች ተፈናቅለዋል!!! በደቡብ ክልል 450 ሽህ ጌዲዬ ህዝብ ተፈናቅለዋል!!! የወያኔ መንግሥት የከፋፍለህ ግዛ ዘመን አብቅቶል!!! የወያኔ የኮንትሮባንድ ንግድ ሲባል ህዝብ አይፈናቀልም!!! ኤርትራን ያስገነጠለ፣ የባህር በር ሃገሪቱን ያሳጣ፣ ባድሜን አሳልፎ የሸጠ የወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያዊ ትግራይ ወጣቶች ትግል ይገረሰሳል!!! በቃ ፍየል ሲሰባ፣ ሾተል ይልሳል!!! ሰው ታሞ እንጅ፣ ፈርቶ አይሞትም! የተፃፈልንን እኖራለን!!!

{I} የዘውግ ፌዴራሊዝም በኢትዩጵያ፣ ግብር ከፋዩ ህዝብ፣ ለወያኔ/ኢህአዴግ የፌዴራልና ክልሎች መንግሥታት የዘር ፖለቲካኞች ደሞዝ ይከፍላል!!!

• የግንቦት 20 በዓል፣ የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ግንቦት ሃያ በዓል፣ለህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሃት) በዓል፣ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ለብአዴን) በዓል፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለኦሕዴድ) በዓል፣ የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) በዓል፣ ለሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለሶዴድ) በዓል፣ ለአፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አዴድ) በዓል፣ ቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ለቤህነን) በዓል፣ ለጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ለጋሕነን) በዓል፣ ለሃረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሃዴድ) በዓል እየተባለ በየአመቱ የሚወጣው የበዓል ወጪ በግብር ከፋዩ ዜጋ ላይ የተጫነ ዕዳ በመሆኑ ሊቆም ይገባዋል እንላለን፡፡ የዘር ፌዴራሊዝም ውጤቱ ዳንኪራ እንጅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አላስገኘም፡፡

• የብሄር ብሄረስብቦች በዓል፣ ጋምቤላ ክልል፣ወይዘሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ በጋምቤላ በተካሄደው የ10ኛው የብሄር ብሄረስብቦች በዓል ለ200 ስዎች ለበሉት 12 ሚሊዩን ብር እንዲከፍል ተጠይቆል፣ ክልሉ 346 ሚሊዩን ብር ከበጀቱ በመቀነስ እየከፈለ መሆኑ አስታውቆል፡፡ በ2009 ዓ/ም በጀት ዓመት 200 ሚሊን ብርእንዲሁም በ2010 ዓ/ም 146 ሚሊዮን ብር ለፌዴራል መንግስት ከፍለዋል፡፡ ለጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት ህክምና አንድ ሚሊዮን ብር ክልሉ ሠጥቶል፡፡ ከግብር ከፋዮ ህዝብ የተዘረፈ ኃብት ነው፡፡

• ሱማሌ ክልል፣ ሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኤሊ የክልሉን ባጀት ለትግራይ ተፈናቃዬች 10 ሚሊዮን ብር፣ ለመለስ ዜናዊ ልጅ 1.5 ሚሊን ብር፣ ለክንፈ ልጅ 1.5 ሚሊዮን ብር፣ ከግብር ከፋዮ ህዝብ የተዘረፈ ገንዘብ ነው፡፡

• አፋር ክልል፣ በተካሄደው የብሄር ብሄረስብቦች በዓል፣ ክልሉ 500 ሚሊዩን ብር ከበጀቱ ለወያኔ/ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ብዙ ሥራዎች በመስጠት ሲያዘርፍ ክልሉ እዳውን እየከፈለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከግብር ከፋዮ ህዝብ የተዘረፈ ኃብት ነው፡፡

• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሃረሪ፣ ደቡብ ክልሎች ተመሳሳይ የብሄር ብሄረስብቦች በዓል በሦስት እስከ አምስት መቶ ሚሊዩን ብር ወጪ እንዲከፍል ተጠይቆል፣ ክልሉ 500 ሚሊዩን ብር እየከፈለ መሆኑ አስታውቆል፡፡ የብሄር ብሄረስብቦች በዓል በደመቀ ሁኔታ ለመከወን ለስብሰባ ተሳታፊዎች ድግስ፣ ቲሸርት፣ ኮፍያ፣ ባንዲራ፣ የሚወጣ የግብር ከፋዩ ዜጋ ላብና ደም በመሆኑ ሊቆም ይገባዋል፡፡
የዘውግ ፌዴራሊዝም በኢትዩጵያ፣ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የዘውግ ፌዴራሊዝም ማኒፊስቶ (የወያኔ ህገ መንግስት)በ1983ዓ/ም በቆንቆ፣ላይ ተመስርቶ ለሃያ ሰባት አመታት በህዝብ ላይ የተጫነበት የኢኮኖሚ፣ጆግራፊ፣ የባህል፣ የስነልቦና፣ወዘተ ልዩነቶች ፈጥሮ በማለፉ በዘር ላይ በተመሰረተ ክፍፍል ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ከቀያቸው ተሰደዋል፣ ብዙ ኢስብዓዊ ድርጊቶች ተፈፅመዋል፡፡ ዛሬም በወያኔ የተቀበረ የጊዜ ቦንብ እየፈነዳ ይገኛል፡፡ በሶማሌ ክልል አንድ ሚሊዩን ህዝብ ተፈናቅለሎል፣ ከኦሮሞም ክልል ሶማሌዎች በመቶ ሽህ ተፈናቅለዋል፡፡ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አማራዎች መጤ ተብው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ፣ በኦሮያም አማራዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በደቡብ ክልል በጌዲዮና በኦሞ ክልል ጉጂ ዞኖች መካከል ግጭት ታስቅሶ በሺዎች ተፈናቅለዋል እንዲሁም በጉራጌ ዞን በጉራጌና ቀቤና ማህበረሰቦች ግጭት ተከስቶል፣ በሲዳማና ወላይታ ህዝብ መኃል ግጭት ተከስቶል፡፡ በትግራይና አማራ ክልሎች በወልቃይት ጠገዴ ግዛት ውዝግብ ቀጥሎል፣ በአማራና አፋር ክልል ግጭቶች ይስተዋላሉ፣ በሃረሪ ክልል የኦሮሞ፣ሱማሎና አማራ ህዝብ የታፈነ ብሶት መፈንዳቱ አይቀሬ ሆኖል፡፡ በኢትዮጵያ የሃገር ግንባታ የነገሥታት ታሪክ አስተዳደር ‹‹ሃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው!!!›› በሚል ቃል ኪዳን የተሳሰረና ህዝቡ በሁሉም የሃገሪቱ ግዛቶች ንብረት አፍርቶና ሠርቶ ይኖርበት የነበረ ወርቃማ ዘመን ያሳለፈ ህዝብ ነው፡፡ ›› የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከሰውነት ጥያቄ ወደ የማንነት ጥያቄ ተሸጋገሩ፡፡

Ethnicity and restructuring of the state in Ethiopia (Berhanu Gutema Balcha1)
‹‹Ethnicity has been a key criterion in restructuring the Ethiopian state in federal lines. The cases of dissolved ethno-federal arrangements such as that of the USSR, Yugoslavia and zechoslovakia resonated pessimism about the feasibility of federalism based on ethno linguistic lines. In contrast, some relatively successful ethno-linguistic federal arrangements like those of India and Switzerland have shown the feasibility of ethnic federalism in divided societies. Both, critiques and advocates of ethnic federalism have their justifications. Advocates hold that ethnic federalism could {1} reduce groups’ disparity, {2} promote accommodation and self-rule, {3} encourage ethnic harmony through co-existence and {4} reduce secession or disintegration tendencies (Lijphart 1977 and 2002, Gurr and Harff 1994; Hameso 1997; Kimenyi 1997; Clapham 2001; O’Leary 2002; Osaghae 2006; Kymlicka 2006).
In contrast, critiques argue that ethnic federalism could {1}institutionalise ethnic discrimination, {2}obstruct individual citizens rights, {3}strengthen centrifugal forces, {4} introduce zero-sum ethnic competition and {5}generate dangerous reactions like ethnic cleansing, expulsion and disintegration (Lipset 1963; Nordlinger 1972; Ake 1996; Fleiner 2000; Nyong’o 2002; Egwe 2003; Mamdani 2005).››

የማንነት ጥያቄ በኢትዩጵያ፣በኦሮሚያ ክልል ዛይ፣በአማራ ክልል ቅማንት፣ በትግራይ ክልል ራያና ወልቃይት፣ በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል ወለኔና ኮንሶን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ብሄር ብሄረሰቦች የንግድ መታወቂያ፣ የማንነት ጥያቄዎች መጨመር ዋናው ምክንያት የሚገኘው የፌዴራል መንግሥት የገንዘብ የበጀት ጥቅም ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑና በዛም ለብዙ የዘር አባላቶች የሥራ ዕድል የማግኘትና የደሞዝ ገቢ ምንጭ ዕድል ስለሚፈጥር የፊዴራል መንግሥት በሚያከፋፍለው በጀት የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት መንገድ፣ ትምህርት ቤት ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያ የመሳሰሉትን በመገንባት ስለሚያስችል ለዚህ ለመብቃት መታገል የግድና የህልውና ጥያቄ ይሆናል፡፡
‹‹ A double process occurred at the same time: the ethnicization of the political culture and the politicization of ethnic identity as the primary vehicle for claims and entitlements to economic resources and political power. The civic basis for politics was displaced by the legalization of ethnic ideology, the creation of ethnic based political organizations, the creation of ethnic-designated regional states and the division of the country’s territory along ethnic lines. This new social arrangement is called ethnic federalism. Ethnic federalism was promulgated into a fundamental constitutional law above and beyond any customary law in 1995 (Mammo and Papadopoulos, 2004: 9).››
የማንነት ጥያቄዎች የመጨመር እንድምታ፣
{1} ለክልልና ለፌዴራል መንግስታት የማንነት ጥያቄዎች ከአገሪቱ ከሁሉም አቅጣጫዎች እየጎረፉ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹ በክልል ደረጃ መፍትሄ አግኝተዋል ቢባልም፣ ሌሎች ግን በይግባኝ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበዋል፡፡ ወለኔ፣ ዛይ፣ ኮንሶ፣ ራያና ወልቃይት በክልል ደረጃ የመጨረሻ ውሳኔ ገና ያላገኙ ናቸው፡፡ እንደ ቅማንት፣ መንጃና ኮንቶማ ያሉት ደግሞ በምክር ቤቱ በይግባኝ ከታዩት የሚካተቱ ናቸው፡፡ ለአንዳንድ ምሁራን በክልል ደረጃም ሆነ ለፌዴራል መንግስቱ ለማንነት ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሾች ወጥነት የሚጎላቸው ናቸው፡፡
{2} በሽግግሩ መንግስት ወቅት 63 ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለራሳቸው እውቅና ሰጥተው ነበር፡፡ ሕገ-መንግስቱ በ1987 ዓ/ም ሲፀድቅ 67 ደርሰው ነበር፡፡ በወቅቱ በደቡብ ክልል የነበረው ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቁጥር 46 የነበረ ሲሆን፣አሁን 56 ደርሶል፡፡ ነገር ግን እነዚህ አዳዲስ ብሄሮች ማንነታቸውን እንዴት እንዳገኙ መረጃ የለም፡፡
{3} የማንነት ጥያቄዎች በአብዛኛው ለአዲስ ማንነት እውቅና በመጠየቅ፣ አዲስ አስተዳደር በመጠየቅ፣ ፍትሀዊ የሆነ የሃብትና የሥልጣን ክፍፍል በመጠየቅና በመሳሰለው ሊገለፅ ይችላል፡፡ የማንነት ጥያቄዎች በዋናነት የእውቅና ጉዳይ ነው፡፡ አንድ አካል እውቅና ሳይሰጠው መብት አይኖረውም፡፡ እውቅና ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡
{1} በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {1.1} የስልጤ የማንነት ጥያቄ በደቡብ ክልላዊ መንግስት፣ የስልጤ ህዝብ በደቡብ ክልል ውስጥ ተከልሎ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ ስልጤዎች ከጉራጌ የተለየ ማንነት ስላለን ተነጥለን ራሳችንን በራሳችን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን ሲሉ ጥያቄዎች ለደቡብ ክልል አቀረቡ፡፡ የስልጤ ጉዳይ በ1992 ዓ/ም በደቡብ ክልል ውድቅ ሆኖ በይግባኝ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀረበ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የስልጤ ማህበረሰብ በማንነቱ ላይ በመጋቢት ወር 1993 ዓ/ም በህዝበ ውሳኔው ውጤት ስልጤ ከጉራጌ ተለይቶ የራሱ ዞን ለማቆቆም በቅቶል፡፡{1.2} መንጃና ኮንቶማ የማንነት ጥያቄ {1.3} ኮንሶ የማንነት ጥያቄ {1.4} የቁጪ የማንነት ጥያቄ {1.5} የሲዳማ የማንነት ጥያቄ {1.6} የወላይታና {1.7} የጌዲኦ የማንነት ጥያቄ በደቡብ ክልላዊ መንግስት ይገኛሉ፡፡
{2} በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {2.1} የቅማንት የማንነት ጥያቄ በአማራ ክልላዊ መንግስት፣ የቅማንት ህዝብ በአማራ ክልል ውስጥ ተከልሎ የኖረ ህዝብ ነው፡፡የቅማንት ህዝብ በአማራ ክልል ከአማራ የተለየ ማንነት ስላለን ተነጥለን ራሳችንን በራሳችን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን ሲሉ ጥያቄዎች ለአማራ ክልል አቀረቡ፡፡ የቅማንት ጉዳይ በ1992 ዓ/ም በአማራ ክልል ውድቅ ሆኖ በይግባኝ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደቀረበ፣ በአማራ ክልል ምክር ቤት ጉዳዩን ዳግም ለማየት ተስማማ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመመካከር በመጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ/ም ለቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር እውቅና ሰጥቶል፡፡{2.2} የአርጎባ፣የአገው ህዝቦች፣ ምዕራብ አዊ የብሄረሰብ ዞኖች፣ የማንነት ጥያቄ በአማራ ክልላዊ መንግስት ይገኛሉ፡፡
{3} በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {3.1} የራያና ቆቦ፣ በወልቃይት የአማራ የማንነት ጥያቄ በትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ የአፋር የማንነት ጥያቄ በትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ በደሜ፣ኢሮፕ፣ ጥያቄ በኤርትራ መንግሥትና በትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ የወሰን ድንበር ግጭት ተከስቶል፡፡
{4} በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {4.1} የሲቲ ዞን የማንነት ጥያቄ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት፣በሶማልያና ኦሮምያ የድንበር ግጭት ተከስቶል፡፡
{5} በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣{5.1} የኑዌር የማንነት ጥያቄ በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት
{6} በኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {6.1} የዛይ የማንነት ጥያቄ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስት
የዘውግ/የብሄርና ብሄረሰቦች የማያባራ ግጭቶች፣ በኢትዩጵያ ዘጠኝ ክልላዊ መንግስቶች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰት የማያባራ የድንበር ግጭት ምክንያት አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በጦርነት ቁም ስቅላቸውን እያዩ በምግብ እራሳቸውን እንዴት አድርገው ሊችሉ ይችላሉ? የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ስልጣን ከጨበጠ ከግንቦት 1983 ዓ/ም ጀምሮ በዘውግ ላይ በተመሰረተ የውሸት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ፌዴራልላዊ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ አገዛዝ መዋቅር በመተግበር በሃገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ የዘውግ/የብሄርና ብሄረሰቦች የማያባራ ግጭቶች የዕለት ተለት ክስተት ሆኖል፡፡ በስልጤና በጉራጌ፣ በደቡብ ዋጋጎዳ የቆንቆ ግጭት፣ በሸኮና በመጀንገር ግጭት፣ በአኝዋክና ኑዌር ግጭት፣ በበርታና ጉሙዝ ግጭት፣ በጌዲኦና ጉጂ ግጭት፣ በኦሮሞና በአማራ ግጭት፣ በቦረናና ገሬ ግጭት፣ በአፋርና ኢሳ ግጭት፣ በኦሮሞና በሱማሌ ግጭት፣ በትግራይና በአማራ ግጭት ወዘተ በተከሰቱ የድንበር ግጭት ምክንያት አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የግብርና ሥራቸውን መስራት ባለመቻላቸው ተደጋጋሚ ድርቅና ርሃብ በሃገሪቱ ተከስቶል፡፡ የህወሓት መንግስት ድርቅና ርሃብ በመሬቱ ላይ በመዝራት በዜጎች ርሃብና ችጋር ላይ በመነገድ የህዝቡን አንጡራ ሃብት ተቀራምቶል፡፡
What is the cause of such bloodshed? Is it an ‘ethnic’ conflict? A’resource conflict’? A’ conflict of identities’ of ‘cultures’ of ‘values’? It is all these and much more.” (Markakis 2003:446)

Pastoral conflicts have struck Ethiopia in different forms for centuries, and are thus not a new phenomenon. However, during the past two decades the country has experienced an increase in the frequency and intensity of violent inter-ethnic conflicts, resulting in far more casualties and derived humanitarian crisis (Markakis 2003; Abdulahi 2005; Unruh 2005; Hagmann and Mulugeta 2008). Conflict the causes and dynamics of conflicts in Ethiopia are changing due to a number of factors, including environmental degradation, shrinking grazing lands, climate change and political instability (Meier et al. 2007; Abdulahi 2005; Hagmann and Mulugeta 2008). However, although inter-ethnic conflicts were apparent prior to 1991, such conflicts became more evident after the then newly incumbent EPRDF government introduced a new policy of ethnic federalism, reconfiguring the state structure into a federation based on ethno-linguistic differences (Debelo 2012; Milas and Latif 2000; Tache and Oba 2009; Abbink 2006). Journal of Law and Conflict Resolution Vol. 4(4), pp. 62-69, April 2012/ Available online at http://www.academicjournals.org/JLCR DOI: 10.5897/JLCR11.045 ISSN 2006-9804 ©2012 Academic Journals

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (2008-2012እኢአ)፣ በአምስት አመታት ውስጥ የአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢ፣አንድ ትሪሊዩን ሦስት ቢሊዩን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ህወኃት /ኢህአዴግ በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ዶሴው ላይ ገልፆል፡፡ በእቅዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 17 በመቶ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶል፡፡ የሁለት ዓመት ተኩል የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መንግሥት በቀጥታ የተበደረው የውጭ ዕዳ ክምችት በዚህ አመት 24.75 ቢሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡የንግድ ሚዛን ጉድለቱ በ2009 ዓ/ም 13 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ አገሪቱ ስታገኝ የነበረው የውጭ ብድር በኢንቨስትመንትና ለኢንቨስትመንቱ በሚያስፈልገው ቁጠባ መካከል የሚታየውን ልዩነት ለመሸፈን ከፍተኛ ሚና እንደነበረውየገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ አስታውቀዋል፡፡ ከ2004 ዓ/ም እስከ 2007ዓ/ም ድረስ ከታክስ ይገኝ የነበረው 15.2 በመቶ የነበረ ሲሆን ከ2008ዓ/ም እስከ 2009ዓ/ም 10.3 በመቶ ብቻ ማደግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በ2009ዓ/ም ታቅዶ ከነበረው የታክስ ገቢ 39 ቢሊዮን ብር መሰብስብ እንዳልተቻለ፣ በ2010ዓ/ም ታቅዶ ከነበረው የታክስ ገቢ 199 ቢሊዮን ብር ደግሞ 50 ቢሊዮን ብር እንደማይሰበሰብ ከወዲሁ መታወቁን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የተለያዮ ፕሮጀክቶች ወደ በ2011 ዓ/ም እንዲሸጋገሩ መንግሥት መገደዱን፣ ይህ ሁኔታም በመንግሥት ላይ የበጀት ጫና መፍጠሩን ገልፀዋል፡፡

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ህገ መንግሥት መሠረት የፊዴራል መንግስት ለክልል መንግሥታት መደበኛው ባጀትና የክልሎች ድጎማ በብዙ ቢሊዮን ብር የሚቆጠር በጀት ለክልሉ የመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ ለክልሎች ሹማምንትና ካድሬዎች መኪና፣ ቤት፣ መሬት ወዘተ ጥቅማ ጥቅሞች ለማግኘት ቀበሌዎች ወደ ወረዳ፣አውራጃ፣ ዞን፣ ልዩ ዞንና ወደ ክልል መንግሥትነት ማደግ ይፈልጋሉ፡፡‹‹The case of Waag Himra demonstrates the advantages of ‘special’ zone status, and thus provides a useful preface to the consideration of cases in the SNNPNRS where populations have raised claims for similarly separate and autonomous zones. In 1998/99 the zone had a capital budget of 7,974,000 EB and recurrent budget of 18,278,000, in respect of a population projected to be around 316,500 at the time262. Resulting per capita budget figures are significantly higher than those applying in other areas. In particular, the capital budget, which has funded the extensive construction of zone office buildings, a large hospital, and highly visible housing for civil servants, has fuelled a dramatic growth in Sekota town during the 1990s. In addition to the generous allocation of resources to the ‘special’ zone by the Amhara259››በዚህ የጥቅም ግጭት ይነሳል፣ ክልሎቹ እዚህ ግባ የማይባል ግብር እየሰበሰቡ፣ ከፌዴራል መንግስት የሚሠፈርላቸው በጀት ይባላሉ፡፡ በኢትዮጵያ 2000 ሽህ ከፍተኛ ግብር ከፋዬች በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ አዋሳ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር ወዘተ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞችና ገበሬዎች ብቻ ግብር ከፋዬች ናቸው፡፡ ከነዚህ የሚሠበሰበው የግብር ከፋዩ ህዝብ ላብና ደም ለእነዚህ የክልል ሹማምንትና ካድሬዎች ወጪ ይውላል፡፡ የክልል ሹማምንት የሙያ ክህሎትና የትምህርት ደረጃ ብቃት መመዘኛ የማያሞሉ ምላስ አደር የፖለቲካ ካድሬዎች በህዝቡ ጫንቃ ላይ ተቀምተው ህዝቡን ሲዘርፉ 27 አመታት ተቆጥሮል፡፡ በየቦታው የሚነሳ የማንነት ጥያቄ ማጠንጠኛው ወደ ክልል መንግሥትነት ብናድግ ከፍተኛ በጀት እናገኛለን በሚል የፖለቲካ ካድሬዎች ቅስቀሳ የተነሳ ነው፡፡ ለዚህ ነው በህገ-መንግስቱ የተቀመጠው በቆንቆ ላይ የተመሠረተ የክልሎች አከላል ግጭቶችን በየአካባቢው የሚጭረው፡፡ በደቡብ ክልል የሲዳማ፣ ወላይታና የጉራጌ ህዝብ ከ ከ3 አስከ 4 ሚሊዩን ህዝብ እያለን ለምን ክልል አንሆንም ጥያቄ ተቀስቅሶል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪና፣ ቤኒሻንጉል ክልል ህዝብ ከሃያ ሽህ እስከ 200 ሽህ ብቻ ሆነው እኛ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር እያለን ለምን ክልላዊ መንግስት አንባልም የሚል የማንነት ጥያቄ ህገ-መንግስቱ የሰጠን የእኩልነታና የፍትህ ጥያቄ ይከበር እያሉ ነው፡፡ የወያኔ ህገ-መንግሥት ሃገሪቱ ልትወጣው ወደማትችልበት የማያባራ ጦርነት ከመግባታችን በፊት ህገ-መንግሥቱ በአፋጥኝ መቀየር ግድ ይላል፡፡

‹‹Of all the national regional units established under ethnic federalism, the smallest, Harar NRS with its ‘national’ population of 9,374 Hararis242 out of a total regional population of 131,139243, is an undoubted constitutional oddity. Whilst the arrangements for its representation at federal level are the same as those relating to other federated states244, Harar NRS is governed under a highly idiosyncratic internal arrangement, which artificially maintains a disproportionate ‘balance of power’ between the small Harari community, and the much larger Amhara and Oromo populations living outside the walled city but within the boundary of the state245. This arrangement, which effectively marks a departure from the principle of equal and universal suffrage in which Ethiopia’s constitutional arrangements are otherwise embedded, is officially justified with reference to the unique historical and religious significance of the holy city of Harar, and, in the view of a Harari historian and linguist, the importance of the history, heritage, and ‘cultural rights of minorities’:››

ምንጭ

{1} The post 1991 ‘inter-ethnic’ conflicts in Ethiopia: An investigation (Lubo Teferi) Department of Law, Adama Science and Technology University, Adama, Oromia State, Ethiopia. E-mail: mailto:luboteferi@gmail.com. 12 March, 2012

{2} Journal of Law and Conflict Resolution Vol. 4(4), pp. 62-69, April 2012/ Available online at http://www.academicjournals.org/JLCR DOI: 10.5897/JLCR11.045 ISSN 2006-9804 ©2012 Academic Journals


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu