Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Contact

የግዕዝ ፊደል እውነታዎች፣ ቅርሶችና ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶክተር አበራ ሞላ

Published Posted on by | By TZTA News
Spread the love

Image may contain: 1 person, smiling, suit
በየሺሀሳብ አበራ
ተለያይተው የተጻፉ ጉዳዮች ተሻሽለውና ተሰባስበው ቀርበዋል። መልካም ንባብ!
ስለ አማርኛ ቋንቋ እውነታዎች
ዶ/ር አበራ ሞላ Dr. Aberra Molla
ባሕር ዳር፣ ሰኔ 06/2008 ዓ.ም. የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት (አብመድ)
፩. ከምዕራብ አፍሪቃው ሀውሳና ከምስራቅ አፍሪቃው ስዋህሊ ቀጥሎ የአፍሪቃ ትልቁ
ቋንቋ ነው።
፪. ከሰሜቲክ የቋንቋ ቤተሰቦች በስፋት በመነገር ያለም ሁለተኛ ቋንቋ ነው።
፫. ከ85.6 ሚሊየን በላይ ተናጋሪ አለው።
፬. ከ 1272 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ የመንግሥት ቋንቋ ነው።
፭. ከአፍሪቃ ብቸኛው ባለፊደል ቋንቋ ሲሆን፣ ፊደላቱን ከወንድሙ ከግዕዝ ተውሷል።
የላንቃ ድምፆችንም ራሱ ፈጥሯል። (ሸ፣ጨ፣ዠ፣ቸ፣ጀ፣ኘ)
፮. የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ ሲሆን የአሜሪካ መንግስትም አማርኛ በአሜሪካ የስራ ቋንቋ
እንዲሆን ፈቅዷል።
፯. ከ 1981 ጀምሮ አማርኛ በዶክተር አበራ ሞላ አማካኝነት እስከ ሙሉ ፊደላቱ
የኮምፒዩተር ቋንቋ ሆኗል።
፰. ከመጋቢት 10/2008 ጀምሮ ደግሞ የጉግል መተርጎሚያ ቋንቋ ሁኗል። አሁን ላይ
በጉግል አማካኝነት አማርኛን ወደ ማንኛውም ቋንቋ መተርጎም ይቻላል።
፱. አማርኛ በአለም ላይ ያሉ ነገሮችን ከ 85 ከመቶው በላይ መግለፅ ይችላል።
በምንጭነት በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋ ላይ የተካሄዱ ጥናቶችን
ተጠቅሜያለሁ።
ለህብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት
አማርኛ ቋንቋ ለሀገር ምን አበረከተ?!
አጋታርከስ፣ ከ 200 እስከ 130 ከክርስቶስ በፊት የኖረ የግሪክ የመልካዓምድር ተመራማሪ
ነው። ከ 60 በላይ የታሪክመፅሀፍትን ፅፏል። አምስቱ መፅሀፍቶቹ ስለሰሜን ኢትዮጵያና
ስለ ቀይ ባህር ያትታሉ። አጋታርከስ፣ በኖረበት ዘመን ከ 130 ዓመታት ከክርስቶስ ልደት
በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦች የሚናገሩት ቋንቋ Camara – ካማራ ይባላል
ይላል። ይህ ቋንቋ አማርኛ ቋንቋ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። አለቃ ታየ ገብረማርያም፣
የአማርኛ ቋንቋ ከክርስቶስ ልደት በፊት ይነገር እንደነበር ፅፈዋል። አለቃ ታየ በአፄ
ሚኒሊክ ዘመን የነበሩ የመፅሀፈ ሰዋሰው መፅሀፍ ፃህፊ ናቸው። አለቃ ታየ በጀርመን
ሀገር የግዕዝና የአማርኛ መምህርም ነበሩ። ፕሮፊሰር አፈወርቅ ገብረእየሱስ ደግሞ
በጣሊያን ሀገር የመጀመሪያ የአማርኛ ቋንቋ ፕሮፊሰርና መምህር ናቸው።
በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በቤተአማራ አማርኛ በተለይም ከ 13 መቶ ክፍለዘመን
ጀምሮ ልሳነ ንጉስ እየሆነ መጣ። ቤተአማራ የአሁኑ አማራ ሳይንት አካባቢ ነው።
በተድባበ ማርያም አካባቢ የሚገኙ መረጃዎችም ይሄን ያመለክታሉ። በንጉስ ላሊበላ
ዘመንም በዛግዌ ስልጣኔ አማርኛ የሰራዊቱ ቋንቋ ነበር። ከ 1271 ዓ.ም. ጀምረው አፄ
ይኮኖአምላክ ንጉሰ አምኃራ ብለው ሲነግሱ አማርኛ የበለጠ ተስፋፍቷል። በ 14 ኛው
መቶ ክፍለዘመን የስነፁሁፍ ቋንቋ ሆኗል።
አማርኛ በኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ኑሮ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ተጋሪ የሆነ ቋንቋ ነው።
ወታደሩን ከየብሄሩ አንድ ላይ በማግባባት በጉንደት፣ በጉራዕ፣ በአድዋ፣ በማይጨው፣
በሶማሊያ ቋንቋዊ አስተዋጽኦ አድርጓል። የአፍሪካ ብቸኛው በስነፁሁፍ ሀብት የበለፀገ
ቋንቋም ነው። በ 1900 በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈው ጦቢያ ልቦለድ የመጀመሪያው የአፍሪካ
ልቦለድ ነው። አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ምክንያት የራሳቸው ቋንቋና ባህል የላቸውም።
ለዚህም ነበር እነጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አክሊሉ ሀብተወልድ በ 1950 ዎቹ አማርኛን
የአፍሪካ ህብረት ቋንቋ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት። ከስዋህሊኛ ቀጥሎ በመነገር
የአፍሪካ ሁለተኛው ነባር ቋንቋ የሆነው አማርኛ በተለይ ኢትዮጵያውያን በጋራ
እንድንግባባ በማድረግ የአንድነት ስር ሆኖ ከ 3 ሺ ዘመን በላይ አገልግሏል። በ 1840
ዓ.ም. መፅሀፍ ቅዱስ ከግዕዝ ወደ አማርኛከተመለሰ በኋላ አማርኛ የቤተክርስቲያን
ቋንቋም ሆኖ እያገለገለ ነው። የግዕዝና የራሱን ፊደል ጨምሮ (ሸ፣ ቸ፣ ኘ፣ ዠ፣ ጀ፣ ጨ፣
ቨ፣ በራሱ ስራዓተፅህፈት በማደግም፣ ኢትዮጵያን ቱባ የስራዓተፅህፈት ባለቤት
አድርጓታል። በአማርኛ ቋንቋ የተፃፉት የነንጉስ ሚኒሊክ ደብዳቤዎች በዩኔስኮ
ተመዝግበዋል። ከ 80% በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁለተኛና በመጀመሪያ ቋንቋነት
የሚናገሩት የአማርኛ ቋንቋ፣ ከ 1980 ዓ.ም. ጀምሮ በዶክተር አበራ ሞላ አማካኝነት
የኮምፒዩተር ቋንቋ ሆኗል። ማይክሮሶፍት የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ
ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል። ጉግልም ከ 2008
ዓ.ም. ጀምሮ የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል። አማርኛ ከቴክኖሎጂ ጋር መተዋወቁ፣
ለዕድገቱ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። በቅርብ ጊዜም አማርኛን በአንድ ድምፅ የኮምፒውተር
መተግበርያ ተሰርቷል። ስለዚህ አማርኛን እንደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በቀላሉ ለመፃፍ
ያስችላል። የትምህርት፣ የስነፁሁፍ፣ የሳይንስ ቋንቋ ሆኖ ለሀገር ያገለገለው አማርኛ፣
በዓለም ላይ 95% የሚሆኑ ጉዳዮችን የመግለፅ ቃላዊ ክምችት አለው። በስነ ልሳናዊ
መዋቅር የኩሽቲክ፣ በቃላቱ ደግሞ ከሴሜቲክ የቋንቋ ቤተሰብ የሚመደበው አማርኛ
ከአረብኛ ቀጥሎ በዓለም ብዙ ተናጋሪ ያለው ቋንቋም ነው። ቻይና ቤጂንግ ዩኒቨርስቲ
አማርኛን ማስተማር ከጀመረ አምስት ዓመታት ተቆጥራል። ጀርመን ሀምቡርግ
ዩኒቨርስቲም አማርኛን ከግዕዝ ጋር አጣምሮ ያስተምራል። እነዋሽንግተንና ቶሮንቶ
ዩኒቨርስቲዎችም ግዕዝንና አማርኛን አብረው እያስጠኑ ነው። ስለዚህ አማርኛ የአማራው
ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያኛ ብሎም የዓለምና የአፍሪካ በስነፁሁፍ ሀብቱ የዳበረ ቋንቋ ነው።
የግዕዝ የኮምፒዩተር ገበታ (US Patent No. 9,000,957, 9,733,724)
አማርኛ፣ የስነ-ጽሑፍ ቅርሶች
መብራት በሱስ እንደወደቀ ጎረምሳ ፀባዮ እየተቆራረጠ ካስቸገረህ ዳቦ መጋገሩን ትተህ
ሻማ ነግድ። ከቻልክም ሻማ ፋብሪካ ክፈት። ላምባና ጧፍም አዋጭ ንግድ ነው። የነሀሴ
ዝናብ፣ እያለቀሰ ሲውል አንተ ጥላ ነግድ። ጃኬትና ቦት ጫማም አያከስሩም። ምንግዜም
ትርፍ የሚገኘው ባንዱ መክሰር ነው። ጨለማ ባይፈሩ እነ ቤንጃሚን ፍራካሊን መብራትን
መቼ ይሰሩ ነበር? ይላል በጎ መካሪ!! መካሪ አያጥፋ!! ሞክር እንደ ቴሌ message ከሰለቸህ
አለመዋጥ ይቻላል። ሞክር የችግር መፈወሻ ብቸኛ ክኒን ሳይሆን አማራጭ ማሳያ ነው።
ግን ኤች አይ ቪ ባይኖር ማሌዥያ የኮንዶም ምርቷን ማን ይገዛት ነበር? እነ ማሊያዥያ፣
አሜሪካ በኮንዶም ኢኮኖሚያቸውን ጠግነዋል። የኤች አይ ቪ መድሃኒት መገኘት ለእነዚህ
ሀገራት መርዶ ነው። በእንግሊዛዊው ዶክተር ኮንዶም የተሰራው ኮንዶም ከነዳጅና ከጦር
መሳሪያ በላይ አዋጭ ንግድ ነው። እዚህ በስጦታ ስለሚመጣ ዝም ብሎ የሚታፈስ
ከመሰለህ ተሳስተሃል። በነገራችን ላይ ኤች አይቪን ለሚመስል የእንስሳት ሁኔታ
መቋቋሚያ ዘዴ ከፈጠሩ የዓለማችን ሳይንቲስቶች መካከል ዶክተር አበራ ሞላ አንዱ
ናቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኤችአይቪ ምንነት ገና በ 1981 በአማርኛ ለኢትዮጵያውያን
ያስተማሩ፣ የፃፉ ዶክተርም ናቸው። ኑሯቸውን ለ 42 ዓመታት ያህል በአሜሪካ ያደረጉት
ዶክተር አበራ የአማርኛ ስራዓተ ፅህፈትን ለኮምፒዩተር ያስተዋወቁ ሙህርም ናቸው። ከ
1980 ዓ.ም. በፊት በአማርኛ ደብዳቤ እንኳን በታይፕ ራይተር ለመፃፍ ብዙ ጊዜ ይፈጅ
ነበር። መፅሀፍት ለማሳተማ አሳር ነበር። በዚህም ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ፊደላት
እንዲቀነሱ ወተወቱ። እነደራሲ ሀዲስ አለማየሁ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በአማርኛ
ፊደላት ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ነበሩ። ዶክተር አበራ የአማርኛ ችግር ገዷቸው ከእንስሳት
ዶክተርናቸው ጎን ለጎን ኮምፒዩተርን አሀዱ ብለው አጠኑተማሩ። የልጅነት
ትውስታቸውን ፊደል እስከ ባህሪያቱ ተመልሰው ጠንቅቀው አጠኑ። አጥንተውም፣
አልቀሩም በ 1980 ዓ.ም. ዛሬ የምንገለገልበትን የአማርኛ ስራዓተ ፅህፈትና ፊደል
ለኮምፒዩተር ያስተዋወቁትን አቀረቡ። የግዕዝ ፊደላትን በሙሉ ወደ ኮምፒዩተር
መርሃግብር አስገቡ። ዶክተር አበራ፣ በአፕል የቴክኖሎጂ ኩባንያ ተንቀሳቃሽ ስልክ
የአማርኛ ፕሮግራም እንዲኖር አድርገዋል። አማርኛችን ከፊስቡክ እስከ ጎግል ከዓለም
ግዙፍ ቋንቋዎች ጋር እንዲቀላቀል ሆኗል። የበለጠ ለማሻሻልም እየሰሩ ነው። ተግባር ሰሪ
ሙህራን ዓለምን ይቀይራሉ።
የዛሬ ብላቴናዎች 3 “ዮ”ዎች እንደዚህ ገራሚ ፈጠራ ሳያበረክቱ ይቀራሉ? (ዮፍታሄ:
633፣ ዮሴፍ፣626 ዮናታን: 623) እንዴት ነው ነገሩ ግን “ዮ” ዎች አልተቻሉም!!
በስነፍጥረታዊ የፊደል አመጣጥ ንድፈ ሀሳብ መሰረት “የ” የተባለችው ሆሄ ትርጉሟ
“የማነ እግዚአብሄር ገብረት” የእግዚአብሔር ሀይል ቀኝ አደረገ ማለት ነው። የማነ – ቀኝ
ማለት ነው። ጌታ ሲሰቀል በቀኝና በግራ የማናይና ፀጋማይ ነበሩ። የማናይ በአዲስ ኪዳን
ቀድሞ ከሰው ልጆች መካከል ገነት የገባ እንደሆነ ስነፍጥረቱ ያትታል። “የ” ወርቃማ
ሆሄ ናት። (የግዕዝ፣ ሆሄያት ሙሉ ትርጉም እንዳላቸው ይታወስልኝማ!!)
“የ” ሆሄ የዋዛ አይደለችም። ግን ሆሄ ነው ፊደል ነው የሚባለው? ፊደል (alphabet)
የሆሄያ አሰዳድር ሲሆን፣ ሆሄ (letter) የነጠላ ድምፆች መጠሪያ ነው።
ግዕዝ በመጀመሪያ 22 ፊደላትን ከአርብ እስከ እሁድ ባሉ ፍጥረታት ልክ ፈጠረ። ከዚያ
በኋላ ለንበት (pronunciation) አራት ፊደላትን አከለ (ሰ፣ኃ፣ዐ፣ፀ)። አማርኛ ደግሞ ሰባት
ሆያትን ጨመረና (ቸ፣ኸ፣ዠ፣ሸ፣ኘ፣ጨ፣ቨ) ፊደላችን 33 ደረሱ ። እነዚህን ፊደላት
ሳይቆራርጡ ዶክተር አበራ ከቴክኖሎጂ ጋር እስከ ስራዓተ ነጥባቸው አስቀመጡ። የግዕዝ
ፊደላት ለአማርኛ እንዲመቹ ሆነው የተሰደሩት ከዛሬ 700 ዓመት በፊት በአፄ
ይኮኖአምላክ ዘመን ነው። በዚህን ወቅት አማርኛ የበለጠ ወደ ፁሁፍ ቋንቋነት የተሳበበት
ዘመን ነበርና። ከቅርቡም አለቃ ተስፋ ገብረስላሴ ዘ ብሄረ ቡልጋ ፊደላት ተደርድረው
እንዲወጡ በማድረግ የሀገር ውለታ ውለዋል። “ድንቁርና ይጥፋ፣ ይሄ ነው የኢትዮጵያ
ተስፋ!” የሚለው የዘወትር መፈክራቸው ነበር። (አሁንም አማርኛን የበለጠ ለቴክኖሎጂ
ለማቅረብ ፈረንሳይ ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ጋር በመሆን
ፊደላት ያዘለ የኮምፒዩተር መጫኛ (keyboard) ሰርተዋል።) አማርኛ የዘመን
ክስተቶቻችን ሙሉ ሸብሎ የያዘ ቋንቋ በመሆኑ የቴክኖሎጂና የሳይንስ ቋንቋ ማድረግ
ሊገፋበት የሚገባ ተግባር ነው። ፊደላችንም ቴክኖሎጂን ተላምዶ፣ ለስራዓተፅህፈት ምቹ
ስለሆነ ይቀነስ የሚለው ሀሳብ አሁን ላይ ሚዛን አይደፋም – ዕድሜ ለዶክተር አበራ ሞላ።
ባለፊደል ቋንቋን የታደለችው ኢትዮጵያ፣ በስነ-ጽሑፍ ሀብቷም ትታወቃለች። የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ዘርፍ የሆነው ዮኔስኮ ከኢትዮጵያ
12 የሚደርሱ የስነ-ጽሑፍ ሀብቶችን የዓለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል። መፅሀፈ ታሪከ
ነገስት፣ ፍትሃ ነገስት፣ መፅሀፈ ሄኖክ፣ አፄ ቴዎድሮስና የአፄ ምኒሊክ ወደ እንግሊዝና
ሩሲያ የተላኩ ደብዳቤዎች ወ.ዘ.ተ. በዮኔስኮ ተመዝግበዋል።
ጥንታዊ የብራና ስነ-ጽሑፍን ከስልጣኔዋ ጋር አዋህዳ የተጓዘችው ኢትዮጵያ ፊደሏም
ቴክኖሎጂን እየተላመደ መጥቷል። በተለይም ዶክተር አበራ ሞላ ፊደላትን በ 1980 ዓ.ም.
ከኮምፒዩተር ጋር ካላመዱ በኋላ ከእጅ ስልክ እስከ ጎግል መተርጎሚያ ድረስ ቋንቋችን
ቴክኖሎጂን ተላምዷል። ከ 35 ዓመታት በላይ ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ዶክተር
አበራ ሞላ፣ በኢትዮጵያ ፊደል የኮምፒዩተር አደራደር ከአሜሪካ የፈጠራ ባለቤትነት
መብት አግኝተውበታል። የፈጠራ ባለቤትነት መብቱን የኢትዮጵያ መንግስት
እንዲሰጣቸው እየወተወቱ እንደሆነም በአንድ ወቅት ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል።
ከፊደልና ከቋንቋ በተጨማሪ የራሳችን የዘመን ቀመርም ከዓለም ይለየናል። በጉዳዮ ዙሪያ
ሰፊ ጥናት ያቀረቡት ዶክተር አበራ ሞላ የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ከሮማውያኑ
የጎርጎርስ ቀመር ይለያል። ትክክለኛው የኢትዮጵያ የዘመን ስሌት ነውም ይላሉ።
ሀሳባቸውን ለቫቲካን ቤተክርስቲያን አሰምተው ተቀባይነት አግኝተዋል። የእንግሊዙ
ቴሌግራፍ እንዳስነበበውም፣ የአውሮፓ የዘመን ቀመር እንደገና መጠናት እንዳለበት
የቫቲካን ቤተክርስቲያን ዋቢ አድርጎ ጠቅሷል። የቫቲካን ጳጳሳትም የአውሮፓ የዘመን
ቀመር መቀየር እንዳለበት በመፅሃፋቸው ገልፀዋል።
http://www.ethiomedia.com/assert/4848.html
ባህረ ሀሳብን የመረመሩት ፕሮፊሰር ጌታቸው ሃይሌም፣የዘመን ቀመራችንን
ምክንያታዊነት እና ሳይንሳዊነት አረጋግጠዋል። ይህ ሁሉ ሀሳብ የተገኘው በግዕዝ ከተፃፉ
ሰነዶች ነው። በመሆኑም ግዕዝን መመርመር ከትናንት ተነስቶ ወደ ነገ ለመሻገር
መንደርደሪያ ሆኖ ያገለግላል ይላሉ ዶክተር አበራ ሞላ። ዶክተሩ እንደሚሉት በተለይም
ስራዓተ ፅህፈቱን ለማሻሻል ያበለፀጉትን አዲስ ሶፍትዌር መጠቀም ነገን ለመቅደም
አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራል ይላሉ።
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲም፣ ግዕዝንና ጥንታዊት የኢትዮጵያ ታሪክን መመርመር
የሚያስችል የትምህርት ክፍል ከፍቶ ከወራት በኋላ ማስተማር ይጀምራል። የዚህ
መርሃግብር አስተባባሪ ዶክተር ዳዊት አሞኘ የጥንታዊት ኢትዮጵያን (classical history
of Ethiopia) ታሪክ ከግዕዝ ሰነዶች በመፈተሽ የሀገሪቱን ትክክለኛ የታሪክ፣ የፍልስፍና
እና የልዩ ልዩ ሀገረሰባዊ ሀብቶችን ለማጥናት ታሳቢ ተደርጓል። መርሃግብሩም በሁለተኛ
ዲግሪ የሚሰጥ ይሆናል። ባህርዳር ዮኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ተቋም ከፍቶ
የቋንቋውን የስነ-ጽሑፍ ሀብት ለማሳደግም እየሰራ ነው።
የሺሀሳብ አበራ

አማርኛ
ባሕር ዳር 01/2009 ዓ.ም. (አብመድ)
ከምዕራብ አፍሪቃው ሀውሳና ከምስራቅ አፍሪቃው ስዋህሊ ቀጥሎ የአፍሪቃ ትልቁ ቋንቋ
ነው። ከሰሜቲክ የቋንቋ ቤተሰቦች በስፋት በመነገር ከአረበኛ ያለም ሁለተኛ ቋንቋ ነው።
ከ85.6 ሚሊየን በላይ ተናጋሪ አለው ከ 1272 ዓም ጀምሮ የኢትዮጵያ የመንግሥት ቋንቋ
ነው። ከአፍሪቃ ብቸኛው ባለፊደል ቋንቋ ሲሆን፣ ብዙ ፊደላቱን ከወንድሙ ከግዕዝ
ተውሷል። (ግዕዝ የአማርኛ አባት አይደለም። ሁለቱ ቋንቋዎች በሰዋሰው መዋቅር እና
በስነ ልሳን ትንታኔ ልዩነት አላቸው። እንዲያውም አማርኛ በቋንቋ መዋቅሩ ከሴሜቲክ
ቋንቋዎች ይልቅ ወደ ኩሽቲክ ቋንቋዎች የቀረበ ነው።) የላንቃ ድምፆችንም ራሱ
ፈጥሯል። (ሸ፣ጨ፣ዠ፣ቸ፣ጀ፣ኘ) 80 ከመቶው ኢትዮጵያውያን በአፍ መፍቻ አሊያም
በሁለተኛ ቋንቋነት ይናገሩታል። ከአፄ ቴወድሮስ መነሳት ጀምሮ በስፋት ወደ ፁሁፍ
ቋንቋነት አድጓል። አሁን ላይ የአማራ፣ የጋምቤላ፣ የቢሻንጉል ጉምዝ፣ የደቡብ ክልል፣
የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድሮች የስራ ቋንቋ ነው። የኢትዮጵያም የስራ
ቋንቋ ሲሆን፣ አማርኛ በአሜሪካ መንግሥትሞ ባንዳንድ ግዛቶች የስራ ቋንቋ
እንዲሆን ፈቅዷል። በአሜሪካ ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተናጋሪዎችም አሉት።
ለአብነት በ2016 የአሜሪካ ምርጫ አማርኛ በሚኒሶታ ግዛት የምርጫ ካርድ በአማርኛ
ቋንቋ ተዘጋጅቷል። ከ 1980 ጀምሮ አማርኛ በዶክተር አበራ ሞላ አማካኝነት እስከ ሙሉ
ፊደላቱ የኮምፒዩተር ቋንቋ ሁኗል። ከመጋቢት 10 2008 ጀምሮ ደግሞ የጉግል
መተርጎሚያ ቋንቋ ሁኗል። አሁን ላይ በጉግል አማካኝነት አማርኛን ወደ ማንኛውም ቋንቋ
መተርጎም ይቻላል። ፌስቡክም አማርኛን መጠቀሚያ ቋንቋ ዝርዝር ውስጥ
አስገብቶታል። (ከፌስቡካችሁ ታች ላይ አረጋግጡ። ፌስቡክ መተግበሪያን በአማርኛ
ማድረግም ይቻላል።) አማርኛ በአለም ላይ ያሉ ነገሮችን ከ 95 ከመቶው በላይ መግለፅ
ይችላል። አማርኛ የተገኘው ከአማራው ነገድ ቢሆንም፣አማራ ከአማርኛ ቀድሞ ኑሯል።
አማራው አማርኛን በዕድሜ ይበልጠዋል። አማራው አማርኛን ፈጠረ እንጂ አማርኛ
አማራን አልፈጠረም።
በምንጭነት፣
– በባህርዳር ዮኒቨርስቲ በተለያዩ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋ ላይ የተካሄዱ ጥናቶችን።
– የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ – መፅሀፍ
– ዲያቆን ዳንኤል ክብረት – ጥናት
የአማርኛ ውልደትና ዕድገት ስስ ዳሰሳ ፩
አማርኛ ቋንቋ ላይ ከተሰሩ ጥናቶች መካከል በ 1983 የወጣው የአሜሪካዊው የስነ ልሳን
ሊህቅ (elite) የቤንደር ጥናት ሰፊ ሀተታ ይዟል። ቤንደር በ 4 ኛው መቶ ክፍለዘመን
ከሰሜን ጫፍ ወደ አማራ (አሁን ወሎ) የመጡ ወታደሮች ከአማራው (ከአማርኛ
ተናጋሪው) ጋር ተዋህደው በተለይ በ 9 ነኛው መቶ ክፍለዘመን አማርኛ እየተስፋፋ
መጣ። ቤንደር አማርኛ ከ 4 ኛው መቶ ክፍለዘመን ቀድሞ ይነገር ነበር የሚል ፍንጭ
ሰጥቷል። አለቃ ታየ ገብረማርያም ግን አማርኛ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት መነገር
የጀመረ ቋንቋ ነው ይላሉ። አብነትም ሽ፣ች፣ጅ፣ጭ፣ዥ፣ኝ ወዘተ አይነት የላንቃ ድምፆች
ሊይዝ የቻለው ከሴማውያን ቋንቋዎች ስለሚቀድም ነው። በእነዚህ ድምፆች የሚጠሩ
ስያሜዎችም በወቅቱ እንደነበሩ ፅፏል። አጋታርከስ የተባለው የግሪክ ታሪክ ከታቢ
በሰሜን ኢትዮጵያ ጫፍ፣ በአፍሪካ ቀንድ በኩል ከክርስቶስ ልደት በፊት ካራአማራ
የሚባል ቋንቋ እንደነበር ፅፏል። ይሄን ቋንቋ ብዙዎች የዛሬው አማርኛ ነው ይሉታል።
ምንጭ አድርገውም ይጠቀሙበታል።
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በ 2001 ዓ.ም. የአማራ ህዝብ ባህል ና ቋንቋ ብሎ
ሙህራን አስጠንቶ ባሳተመው መፅሃፉ በ 1270 ዓ.ም. በሸዋ፣ በወሎ – አማርኛ ግዛቱን
አስፍቶ ስለነበር አፄ ይኮኖአምላክ ልሳነ ንጉስ አደረጉት። በእርግጥ ግዕዝ ከ 10 ኛው መቶ
ክፍለዘመን በኋላ የአንደበት ቋንቋነቱን ለአማርኛ አስረክቦ፣ የፁሁፍ ቋንቋ ብቻ ሆኗል።
የዛጉዌ ወታደሮች ቋንቋ አማርኛ ሲሆን፣ አፄ ላሊበላ አማርኛን ልሳነ ንጉስ አድርገውት
እንደነበር ይርጋ እጅጉ የተባለ የስነ ልሳን ተንታኝ ታሪካዊ ምንጮችን ጠቅሶ ፅፏል።
ቤንደር እና ባየ አማርኛን ከ 13 ኛው መቶ ክፍለዘመን ቀድሞ የአገውና የአማራ
አርሶአደሮች መናገር ይችሉ ስለነበር አማርኛ ለኢትዮጵያ አንድነት መቆሙን በ 13 ኛው
መቶ ክፍለዘመን አወጀ። ኩፐር የተባለው አውሮፓዊ በዛጉዌ ወቅት አማርኛ ከአገወኛ
ጋር በህዝቡ ይነገር ነበር። ስለዚህ የአማርኛ መሰረት ህዝቡ እንጂ ቤተመንግስቱ አይደለም
ይላል። ባየ ይማም ለአማርኛ መስፋፋት የህዝቡ መስተጋብር አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆን
ጠቅሰው፣አማርኛ ከአማራው ነገድ መነገር ቢጀምርም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ቋንቋዎች
አየሰጠም እየተቀበለም ያደገ ቋንቋ ነው ይላሉ። አማርኛ በሁሉም የሀገሪቱ ጠርዝ ባደረገው
መስፋፋትም የሴምና የኩሽ የቋንቋ ባህሪያትን ዘንቆ ይዟል።
የአማርኛ ቋንቋ ፁሁፋዊ ዕድገትበ 14 ኛው እና በ 15 ኛው መቶ ክፍለዘመን የሸዋ
ነገስታት የውዳሴ ግጥም ቀርቧል። በ1690 ለመጀመሪያ ጊዜ የአማርኛ ላቲን መዝገበ
ቃላት በጆን ሩዶልፍ እንደተዘጋጀም ባህሩ ዘርጋው በመዝገበ ቃላት መፅሃፋቸው
ጠቁመዋል። እንግሊዘኛ ላቲን መዝገበ ቃላት በ 1606 ዓ.ም. ነው። አማርኛ
የቤተመንግስትና የህዝብ ቋንቋ ከሆነ ብዙ መቶ ዓመቶችን ቢደፍንም የሸዋ ነገስታት
ለፁሁፍ ግዕዝን መርጠዋል። ነገር ግን የፖርቹጋል የሀይማኖት ሰባኪዎች አብዛኛውን
ህዝቡ በሚችለው በአማርኛ ቋንቋ አየፃፉ ማሰራጨት ሲጀምሩ በ 17 መቶ ክፍለዘመን
ጀምሮ መፅሃፍት ሁሉ ወደ አማርኛ መመለስ ጀመሩ። ለአብነት ከ 400 ዓመታት በፊት
የተፃፉ የአማርኛ መፅሃፍት ሀይማኖተ አበው፣ መፅሀፈ ንሰሃ፣ መፅሃፈ ቀንዲል ወዘተ።
በ 17 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን “የአባጊዮርጊስ ድርሰት በአምሃርኛ” የሚል ግጥምም
ተፅፏል። መፅሃፍ ቅዱስም በ 1840 ዓ.ም. አካባቢ ወደ አማርኛ ሲመለስ አማርኛ
እየፈረጠመ ሄደ። አፄ ቴወድሮስም ብሄራዊ ቋንቋ ሲያደርጉት፣እነ አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያ
በአማርኛ የፍልስፍና መፅሃፍ አከታትለው ፃፉ። አፄ ዮሀንስም አማርኛን ብሄራዊ ቋንቋ
አድርገው ሾሙት። በእምየ ምኒሊክ የበለጠ ተስፋፍቶ፣ በአፍሪካ ቋንቋ የተፃፈው
የመጀመሪያው ልቦለድ “ጦቢያ” በፕሮፊሰር አፈወርቅ ገብረእየሱስ በ 1900 በሮሞ ተፅፎ
ወጣ። ጣሊያንም ከሮም ሆና አማርኛን ማስተማር ጀመረች። (አማርኛን በመደበኛ ደረጃ
ማስተማር የጀመረች ለቅኝ ግዛት እንዲመቻት ጣሊያን ናት።)
ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝን የመሳሰሉት ተራማጅ ፃህፍትም የአማርኛን ስነፁሁፍ በ
1916 መፅሐፍ ፅፈውበታል። ፊታውራሪ ተክለሃዋሪያት ተክለማርያምም ፋቡላ የእንስሳት
ኮሚዲን በ 1913 ዓ.ም. ፅፈው 3000 ቅጂ አሳትመዋል። 300 በአንድ ቀን ተሽጧል-
ዶክተር አንተነህ አወቀ (የአማርኛ ስነፁሁፍ አጭር ቅኝት) ለአማርኛ መስፋፋት
ከክርስትና ሀይማኖት በተጨማሪ እስልምናም ሚናው የጎላ ነበር። በ 15 ኛው መቶ
ክፍለዘመን የሸዋው የጎዜ መስጊድ፣ የጥሩሲና ፣የዶዶታ፣ የቆምበር የመቃብር
ቦታ…ወዘተ በአማራ ክልል ያሉ ቀደምት የእስልምና እምነት መዳረሻዎች ናቸው። በዚህ
ምክንያትም አማርኛ በሀይማኖት አስተምሮውም ሊስፋፋ ችሏል – ዋጋው ሀይሉ (የአማራ
ህዝቦች ባህልና ቋንቋ ገፅ 25)። በወሎ ጠቅላይ ግዛት ተወልደው ያደጉት ሼህ ጦልህ በ
1865 ዓ.ም. አካባቢ መንፈሳዊ ትምህርትና ህግ የሚል የእስልምና መፅሃፍ አሳትመዋል።
በዚህ ዘመን፣ የነብየ መሃመድን ታሪክ በብራናና በአማርኛ ቋንቋ ከመፃፋቸው ባሻገር፣
ሼክ ጦልህ ቁራዓንንም ሙሉ በሙሉ ወደ አማርኛ መልሰዋል። (ሁሴን አህመድን ጠቅሶ
የስነ ልሳን ተንታኙ ይርጋ እጅጉ እንዳጠናው) – የአማራ ህዝብ ባህልና ቋንቋ ከሚለው
መፅሀፍ በገፅ 190 ሰፍሯል።
ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶክተር አበራ ሞላ እና የኢትዮጵያ ፊደል
ከየሺሀሳብ አበራ
አማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
መስከረም ጠብቶ አደዩ ሲፈነዳ፣ ከሚመጡ የመስከረም ትዝታዎች አንዱ ወደ ተማሪ ቤት
ማዝገም ነው። ለምን መስከረም ግን ሁሌ እንደ ወር ህፃን ይጠባል? ጡት አይተውም
እንዴ ብሎ የሞገተ ማን ነበር? መስከረምማ ገና እንቡጥ ነው። ህፃን መስከረም እንጂ
አሮጌ መስከረም የለም። መስከረም ተስፋን፣ ምኞትን፣ ሀሳብን ጠብቶ ያድጋል። የሀሳብ
እንገር ይመገባል። የአማርኛ ቋንቋ በቅኔ የተዘነቀ በመሆኑ መጥባት ለመስከረም መንጋት
ነው። ሌሎች ወራቶች ጨለማ ነበሩ ባይ አይጠፋም። ጥርጣሬ፣ ተጠራጥሮም መጠየቅ
የፍልስፍና መጀመሪያው ምዕራፍ ነው ብለዋል አንደበተ ርቱዑው ፈላስፋ የኛው ዶክተር
ዳኛቸው አሰፋ። አማርኛ ቃላት አማራጭ አላቸው። ባማራጭ ውስጥ ፍልስፍና ይፈሳል።
የኛ ፍልስፍና ቅኔ ነው።
አማርኛን በኮኒቲከት ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ማስተማር ጀምራለች። በአሜሪካ የአማርኛ
ቋንቋ ፕሮጀክት አስተባባሪው ፕሮፊሰር አማኑኤል አናግስቶ አማርኛን ለማስተማር 4.3
ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደተመደበ የዩኒቨርሲቲው ድረገፅ አስነብቧል። አሜሪካ
በምድሯ ከ 500 ሺ በላይ ተናጋሪ ላለው ቋንቋ ለተጨማሪ የስራ ቋንቋነት ታጫለች።
አማርኛ ከ 10 ዓመት በፊት ታጭቶ በተለያዩ ግዛቶች የስራ ቋንቋ ከሆነ ቆይቷል። ዕድሜ
ለዲያስፖራዎቻችን አያ!!! እስራኤልም አማርኛን በስራ ቋንቋነት ልትጠቀምበት ጥናቷን
ጨርሳለች። መስከረም ሊጠባ አካባቢ ከአደይ አበባው እኩል የተስፋ ገብረስላሴ የፊደል
ሰራዊት ከተማውን በቁጥጥር ስር ያውለዋል። በተለያዩ ከተሞች እንደቃኘሁት
የመስከረምን መባት አስመልክቶ ፊደላት ለልጆች እንደ ታጠበ ሸማ ተሰጥተዋል። ተስፋ
ገብረ ስላሴ ዘብሄረ ቡልጋ ..ቆይ እዚህ ፍሬም እንጨብጥማ። ቡልጋ የዛኔ ብሄር ነበረች?
አፈወርቅ ገብረእየሱስ ዘብሄረ ዘጌ ከጣና ተሻርካ የተቀመጠችው ዘጌም በወቅቱ ብሄር
ነበረች? ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ ምነው ልዩነቱ? ትርጉሙ ላይ ብዙ ስምምነት የለም።
በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ከርሞ እልል ያለች ሀሳብ ይዥ እመጣለሁ። ከርሞ ስላችሁ ከሰዓታት
በኋላ ማለቴ ነው። አሁን የምፅፍበት ሰዓት አምና፣ አሮጌው ዓመት ሊባል እኮ ነው።
ሁሉም ያልፋል፣ ለሁሉም ጊዜ አለው ይላል ጠቢቡ ሰለሞን። ግን የኛው ከበደ ሚካኤል
ጠቢቡ ሰለሞንን ሁሉም ካለፈ፣ ለሁሉም ጊዜ ካለው ሞት ራሱ መቸ ያልፋል? ሞት
የሚሞትበት ጊዜ መቼ ነው? ሲል ይጠይቃል። ሰለሞኑን አንደበቱን ሞት ስለያዘው ለከበደ
ሚካኤል ምላሹን አላቀረበም።
ተስፋ ገብረስላሴ ፊደላትን በወረቀት ላይ በመሰደር የሚታከላቸው የለም። ከሸዋ መንደር
ሳልወጣ ዶክተር አበራ ሞላን ሳልጠቅስ ባልፍ የምኒሊክ መንፈስ ይወቅሰኛል። ዶክተር
አበራ ሞላ የተስፋ ገብረስላሴ የፊደል ሰራዊት ወደ ኮምፒዩተር ያዘመቱ የፊደል ጀኔራል
ናቸው። ዶክተሩ፣የዘመን መቁጠሪያችንን እና ሌሎች እንግዳ ጉዳዮቻችንን ወደ
ኮምፒዩተር መንደር ያለምንም መሸራረፍ አስፍረውልናል።
ዶክተር አበራ ሞላ የግዕዝ ፊደላት በኢትዮጵያ ይመዝገቡ ሲሉም 30 ዓመታት
አልፈዋል። አሜሪካ ምኗ ሞኝ ሆነና!! የፊደላትን የኮምፒዩተር አጠቃቀም በተመለከተ
ለዶክተር አበራ የፈጠራ ባለቤትነት መብት ሰጠች። ድሮም አሜሪካ ለዶክተር አክሊሉ
ገጽ 12 የ 12
ለማም የእንዶድን የብልሃርዚያ ቁጥጥርን በተመለከተ የፈጠራ ባለቤትነት መብት የሰጠች
አሜሪካ ናት። የጤፍ እንጀራ አዘገጃጀት በተመለከተ የፈጠራ ባለቤትነቱ መብት ሰጭ
አሜሪካ ናት።
ዩኒቨርስቲዎቻችን እንኳን ቢያንስ የክብር ዶክትሬት መስጠት ነበረባቸው። ለማንም
እያፈሱ ከሚሰጡ ለህክምናው ዓለም ፈርጥና የፊደል የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ፈጣሪና
አስተዋዋቂ ለሆኑት ለዶክተር አበራ የክብር ዶክትሬት ቢቸሯቸው ስራቸውን ለመረከብ
መንገድ ይጠርጋል።
አዲሱ ዓመት የአሮጌው ዓመት ባለዕዳ እንደሆነ ውስጤ ቢረዳም፣ ለአባባል ያህል ግን
አዲሱ ዓመት አዲስ ይሁንልን!!!
ግዕዝኤዲት አማርኛ የአይፎን ቁስ
https://itunes.apple.com/us/app/geezedit-amharic/id935624754?mt=8
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
September 12, 2017
https://archive.is/LWaLI

ስለ አማርኛ ቋንቋ እውነታዎች- ከምዕራብ አፍሪቃው ሀውሳ እና ከምስራቅ አፍሪቃው ስዋህሊ ቀጥሎ የአፍሪቃ ትልቁ ቋንቋ ነው፡፡- ከሰሜቲክ የቋንቋ ቤተሰቦች በስፋት በመነገር ያለም ሁለተኛ…

Posted by Buna Media – ቡና ሚዲያ on Monday, June 27, 2016

https://z-1-lookaside.fbsbx.com/Addistube1/posts/1162884043791196:0
http://freetyping.geezedit.com/ ነፃ መክተቢያ
http://ethiopianamericanforum.com/index.php?option=com_content&view=article&id=671%3Adecemb
er-30-2013
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB_%E1%88%9E%E1%88%8


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu