Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic, Ethiopian

ዶ/ር አብይ የታገሱዋቸው የሕወሓት ጄኔራሎችና የቀድሞ ባለስልጣናት ለውጡን ለመቀልበስ የጦርነት ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል

Published Posted on by | By TZTA News

ዶ/ር አብይ የታገሱዋቸው የሕወሓት ጄኔራሎችና የቀድሞ ባለስልጣናት ለውጡን ለመቀልበስ የጦርነት ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል

Spread the love

መነበብ ያለበት! ትህነግ በዶክተር አብይ (አትንኩት) ላይ

ጋዳፊ ውርደት ሲጠራው እንዲህ እንደነዚህ የቀን ጅቦች የሚያደርገውን አሰጥቶት ነበር።ለውጡ እንዳይቀለበስ ብቻ ሳይሆን 27 ዓመት ባጠፉት ሕይወትና በዘረፉት ሀብት ያልተጠየቁ ይህን ባያደርጉ አይገርምም። ዶ/ር አብይና የለውጡ ደጋፊዎች የዚህን የአገር ሀብት ዘርፎ ጠያቂ ያጣውን የዚህን “ጄኔራል” ተክለብርሃን ፉከራ ከትግርኛ ቃለ መጠይቁ ክፍል አንድ ተተርጉሞ ቀርቧል።ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ማስታወሻ ጋር እነሆ፦

የቀድሞው የዶክተር አብይ (በባህርዳር ወጣቶች ስም መሰረት አትንኩት) አለቃ ጀኔራል ተክለብርሃን፣ “ይህ ጠላት ኃይል ነው” ይለዋል አብይን! “ንጉስ ሆኗል” ይላል! ጀኔራል ተክለ ብርሃን በአንድ ወቅት አብይን ከመስርያ ቤት “አባርሮት” ነበር።

#Brook-Abegaz Aba- Bona ገፅ ላይ

የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ዋና ኃላፊ የነበረው ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ከድምፂ ወያኔ ራዲዮ ጋር ያደረገው እጅግ አስደንጋጭ ቃለ መጠይቅ (ከትግረኛ ወደ አማርኛ ቃል በቃል በKedir Endris የተተረጎመ)
————————————————–
ቃለ መጠይቁ 1 ሠዓት ከ42 ደቂቃ የወሰደ ሲሆን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ለአገራችን ደህንነት በተለይ ደግሞ ለጠሚ ዐብይ ደህንነት እጅግ አስፈላጊ መረጃ ነው በማለት ከ25ኛ ደቂቃ 29 ሴኮንድ ጀምሮ ያለውን ብቻ ቆርጠን ነው የምናቀርብላችሁ። ሙሉውን ቃለ ምልልስ በድምጽ ከአስተያየት መስጫው ታገኛላችሁ።
.
ከቃለ ምልልሱ እንደምንረዳው
—————————————
☞ ጠሚ ዓብይ ሰይፍ ተመዞበታልና እራሱን በጥብቅ እንዲጠብቅ አሳስቡት።
.
☞ ሙስሊምና ክርስቲያኑም ለማባላት ያቀዱት ሴራ ስላለ ሕዝቡ ራሱን ይጠብቅ። ማንኛውንም ሃይማኖት ሰበብ አድርገው ሽብር የሚቀሰቅሱ ሰዎችን ሊመክት ይገባል። ሙስሊሙ ወገናችንን የቁማር ካርታ ሊመዙበት ስላሰቡ ህዝበ ሙስሊሙ በጥብቅ ይስብበት።
.
☞ በአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሶማሊ፣ ሃረሪና ደቡብ ክልል ለመሳብ ያሰቡት የቁማር ካርድም ስላለ ጥብቅ ክትትል ይደረግ።
.
አሁን ወደ ሰጠው ቃለ መጠይቅ እንለፍ።
————————————————-
ጋዜጠኛ (ወንዱ): አሁን ባለው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታዎቸ አስመልክተን ሰፊ ጊዜ ወስደን በትኩረት ልናወራ ነው። ኢህአዴግ ለሁለት አመት ያህል ያደረገውን የተሓድሶ ግምገማ ተከትሎ አሁን ኢህአዴግ ያደረገው የአመራርና የተለያዩ ለውጦች አሉ። እ ለውጡ እንደተጀመረ ነው አንተም ከኢንፎርሜሽን መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ የወጣኸውና እና ስለ ኢንሳ የሚባለው ድርጅት እንደምሰማውና እኔም እንዳነበብኩት ከሆነ ድርጅቱ በጣም የሚያስፈራና ከፍተኛ አቅም ያለው ድርጅታችን ነው የሚባለው። እስኪ ስለ ኢንሳ አሁን ያለበትም ደረጃና ሁኔታ ጨምረህ ብታዋራን? ኢንሳ ማለት ምን አይነት አቅም ያለው ድርጅት ነው?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: ኢንሳ በአማርኛ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ
(ኢመደኤ) ተብሎ የሚታወቀው ነው። ኢንሳ ማለት የኢንፎርሜሽን አውታረ መረብ ደህንነት የሚጠብቅ ተቋም ነው። ስለዝህ ኢንፎርሜሽኑ አለ፤ ኢንፎርሜሽኑ ፍሰት የሚደረግበት መረጃ የምትለዋወጥበት የኢንፍርሜሽን አውታረ መረብ ደግሞ አለ። ደህንነት ማለት ደግሞ የኢንፎርሜሽኑና የአውታረ መረቡ ደህንነት ማለት ነው። እና ኢንሳ ማለት የኢንፍርሜሽኑና አውታረ መረቡ ደህንነት የሚጠብቅ ድርጅት ማለት ነው። የዚህ ድርጅት መነሻው ከመከላከያ ነው። መነስሃው ከመከላከያ ነው ማለት ቀደም ብየ ሳወራችሁ እንደቀየሁት [ለ25 ደቂቃ ደርግን በመረጃ እንዴት እንደጣሉት ሲደነፋበት የነበረ ነው] በህወሓት ብረታዊ ትግል ጊዜ በተፈጠረው አቅም መነሻ ተደርጎ የተጀመረ ተቋም ነው። በህወሓት ብረታዊ ትግል ጊዜ የመረጃ ቴክኒካዊ መረጃ የሚባል ድርጅት ነበረን በመከላከያው። አሁንም አለ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ትልቅ ድርሻ የነበረው ነው።በብረታዊ ትግላችን ጊዜ ከነበረን ትልቅ አቅም ተነስቶ ነው ከመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ በተገኙ 38 ኢንጅነሮች ነው የተቋቋመው። ሁላች ሁም እንደምታውቁት ኢንሳ በሚቋቋምበት ጊዜ ዋና እንትን የነበረው እየተስፋፉ የነበሩ ትልልቅና ሰፋፊ የሚባሉ ፕሮጀችቶች ነበሩ። ከቴሌሙኒኬሽን መስፋፋት ጋር ተያይዞ ያለው የኢንተርኔት፣ የኔትዎርክና የሞባይል ሁሉ ፕሮግራም የማስፋፋት ፕሮግራም ማለት ነው። ስለዚህ ከ1997 የፈረንጅ አቆጣጠር ጀምሮ ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አለማቀፋዊ መተሳሰር ተፈጠረ። ከዝህ ቀጥሎ ደግሞ ሃይል ማስፋፋት ተጀመረ። የኤሌክትሪክ ሃይል መሰረተ-ልማት የሃይል ምንጩን ጨምሮ የሃይል መረቡ በኮምፒተር ነው የሚታዘዘው። ቀጥሎ የመጣው አሁን ያለው ደግሞ የባቡር ነው። የአየር መንገዱን ጨምሮ ሁሉም የአውታረ-መረብ ግንኙነት ስርአት አላቸው። እና የአገሪቱ ሁሉም መሰረታዊ ልማት የሚባሉት መሰረታቸው ኮምፒተር መሰረት ያደረገ የኢንፎርሜሽን ልውውጥ ስርአት ነው። በዚህ ስርአት መሰረት ነው ቁጥጥር የሚደረግባቸው ማለት ነው። ከዚህ በዘለለ ደግሞ የመንግስት ድርጅቶች automate የሚደረጉበት ሁኔታም አለ። የአሰራር ስርአታቸው ወደ automation የሚገቡበት ሁኔታ አለ። ባጠቃላይ ግን ኢንሳ ማለት የአገሪቱ የኢንፎርሜሽንና መረጃ አውታረ-መረብ ኮምፒተር መሰረት ያደረጉ ሁሉ ከጥቃት የሚከላከል ማለት ነው። ምክን ያቱም እዚህ ላይ ሁልጊዜ ጥቃት አለ። ኢንፎርሜሽን ለመውሰድ ብቻ ሳይሆን አገልግሎት ለማቋረጥም። ዋላ የኤሌክትሪክ ሃይል ላይም ከምንጩና ከመተላለፊያው ስርአቱ ላይ ለዚህ የሚቆጣጠር ኮምፒተር ላይ ጥቃት ብታደርግበት የኤለክትሪክ አገልግሎት የሚባለው ያቆማል ማለት ነው። የውሃም የቴለኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችም እንደዛው። ስለዝህ እነዚህ ከተለያዩ ጥቃቶች መካላከል ማለት ነው። እኛ ጥቃት/ደህንነት የምንለው በጣም ሚስጥራዊ የምንላቸውን መረጃዎችን እንዳይወሰድ መከላከል ብቻ አድርጎ የሚወስድ ካለ ይህ የድሮ አስተሳሰብ ነው። አሁን ትልቁ የደህንነት ጉዳይ አገልግሎት ማቋረጥን ነው። ከዛ ደግሞ የተሳሳት መረጃ መስጠትም ደግሞ አለ።
.
ጋዜጠኛው (ወንዱ): በመሃል ሲስተሙን ወስደው?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: አዎ ሲስተሙን ወስደው የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን ይሰጣሉ። ከዛ ደግሞ ለምሳሌ የባንክ ኢንፎርሜሽን ፍሰት ስለምታውቁት ሁሉም ሰው ስለሚያውቀው በባንክ ውስጥ ያለች 100 ብር 100 ሚሊየን አድርገህ ልትቀይራት ትችላለህ። ቁጥሩን ወይም እንትኑን በመቀየር ማለት ነው። የባንኩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ሰብረህ ሃክ አደርገህ ብትገባ [በመሃል እሱም ጋዜጠኞቹም ይስቃሉ] የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ። መስረቅም ትችላለህ። መስረቅ ይቻላል ብቻ ሳይሆን ስርቆት አለ። ወደ ሌላ ባንክ አካውንት ማስተላለፍም አለ ማለት ነው። ወይ ደግሞ አንድ ሚሊዮን የነበረ ብር ወደ 10 ብር መቀየርም ትችላለህ።ይህም የኢንፎርሜሽኑ ተአማኒነት ማለት ነው። ስለዝህ እነዚህን ሁሉ ለመከላከል የተቋቋመ ድርጅት ነው ኢንሳ ማለት። ስለዝህ የምርምር አቅም አለ። ከዛ ደግሞ ይህን ለመከላከል የቴክኖሎጅ ልማት ፈጠራም አቅም ያስፈልግሃል ማለት ነው። ያለውን ቴክኖሎጂ መረዳት መኮረጅ እንዳለ ሁኖ የራስህ ጥበብና ቴክኖሎጂ መፍጠር ያስፈልጋል። ስለዚህ እነዚህ አገልግሎትና ምርምርና ማበልፀግን የሚሰጥ ድርጅት ነው ማለት ነው። ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ ታዋቂና ተወዳዳሪ መሆን አለበት። ማወቁ አይደለም ዋናው ቁም ነገር። ይህንን የምታደርግ ከሆነ የደረሰብህ ጥቃት መነሻው ከአዲስ አበባ ወይ ከኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም። ዋናው ተጋላጭነት የሚፈጥረው አደጋ ከውስጥህ የሚነሳው ነው። ሁልጊዜ ለጠላት ተጋላጭ የምትሆነው ከውስጥህ ባለው ነው። ምን የሚባል አባባል አለ መሰለህ? በግለሰብ ደረጃ ብታየውም የግልሰቡ ዋና ጠላት ራሱ ነው። የዛ ሰው የራሱ አስተሳሰብ፣ ስነ ልቦናና አእምሮ ተጋላጭነት ይፈጥረበታል ማለት ነው። ይህንን ግንዛቤ ውስጥ ከተን ስንሰራ ቆይተናል ውስጤታማም ነበርን።
.
ጋዜጠኛ (ሴቷ): አሁን ያለንበት ሁኔታ በብዙ ወገኖች በልዩ ሁኔታ ደግሞ ኢሊት በሚባሉ በነቁ ወገኖቻችን እየተባለ ያለው አሁን ባገራችን ያሉ ሁኔታዎች ለመገመቱ የሚያስቸግር፣ በመደናገር ውስጥ ነው ያለነው ብሎ ነው የሚያስብ። መደናገር ማለት አንደኛው ወገን ጥሩ ነው ያለነው ብሎ የሚያስብ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ወዴት ነው የምንሄደው ብሎ በስጋትና በፍርሃት ግማሹ እስከመገንጠል ብንወስን ያስኬደን ይሆን ወይ ሌላው ደግሞ ትናንትና ወደነበርንበት እየተመለስን ይሆን ወይ ብቻ በብዙ መልኩ እየተገለጡ ያሉ ክስተቶች አሉ። ስለዚህ አንተ ደግሞ ባለው ሁኔታ ጠቅላላ አመለካከትህ ከመግለጥ በዘለለ አሁን ወዳለው ወደ እውነታው የተጠጋ ሓሳብ አለህ ብየ አምንሃለሁ። ስለዝህ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነን ያለነው? አገር አቀፍ ሁኔታችን ምንድን ነው የሚመስለው?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: አሁን ያለንበት ሁኔታ? በርግጥ የፓርቲ አባል አይደለሁም አልነበርኩም። እኔ ከመካላከያ ነኝ። ግን ፖለቲካው በሁሉ አለ። ስለሚያሳስበን በደምብ ሁልጊዜ እንከታተለዋለን። ስለዚህ አገር አቀፍ ሁኔታው በቅርበት ስንከታተለው ነበር። እና አሁን ያሉ ሁኔታዎች አስቀያሚ ናቸው። ወደድንም ጠላንም እንደ እሬት የሚመረንን እውነት የምንቀበልበት አስገዳጅ ሁኔታዎች ላይ ነው ያለነው። ይህችኛዋ ነች አንደኛዋ ቃል። እሬት እሬት እየጣመን እውነት እንድንቀበል የሚያስገድደን ሁኔታ ላይ ነው ያለነው። ይህ ሁሉ ጥልቅ ተሓድሶ ወዘተ ወዘተ እየተባለ ተመጥቶ በመጨረሻ የመጣው ውጤት ግን የአንድ ሌሊት ውጤት ብቻ አይደለም። በሂደት የተፈጠረ መበስበስም አለ። ስለዝ ህ እየበሰበሰ መጥቶ የመጨረሻ ደረጃው የደረሰበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። አሁን ባጭሩ ኢህ አዴግ የሚባል ግንባር ነበር። ግንባር ነበር በኢንግሊዝኛው coalition የሚሉት ማለት ነው። ፓርቲ አይደለም ግንባር ነው። ሰዎች ፓርቲ ይሉታል ፓርቲ አይደለም።
.
ጋዜጠኛው (ወንዱ): የፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት ነው?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: አዎ የድርጅቶች ስምምነት ማህበር ልትለው ትችላለህ። ባጭሩ ለማስቀመጥ አሁን እሱ ባለፉት ብዙ አመታት እየተሸረሸረ መጣና አሁን ድርጅቱ ራሱን በልቶ ጨርሶ ለዛ በትግራይ ህዝብ ደምና በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የመጣን ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ወደ መብላት የገባበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። ስልዝህ አሁን ያ ወያኔያዊ ያልሆነ ሃይል ነው የበላይነት አግኝቶ ያለው። ቀደም ብየ እንደገለጥኩላችሁ ይህ ያጭር ጊዜ ስራ አይደለም። ከግለሰብ ጋር የሚገናኝ አይደለም። ከግልሰው ጋር ትስስር የለውም። ያለው ሁኔታ ከአብይ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ሳይሆን እናይ በመሰረቱ ማየት ያለብን እንደጠላት ሃይል አድርገን ነው። እንደጠላት ሃይል አድርገን ካልወሰድነው እንዴት አምርረን እንደምንወጋውም ግልፅ ሊሆንልን አይችልም። ስለዝህ ሄዶ ሄዶ ከኢህአዴግ ውስጥ ተነስቶ እየበሰበሰ ራሱን እየበላ የኢህአዴግም ፕሮግራም ጭምር እየበላ በልቶ በልቶ ከጨረሰ ብሁዋላ በመጨረሻ በስልጣን ላይ የወጣው ሃይል ከኢህአዴግ ፕሮግራም ጋር የሚገናኝ ትንሽ የኢህአዴግ ሽታ እንኩዋን የለውም። ለእኔ ይህ የጠላት ሃይል ነው። እንደጠላት ሃይል እንውሰደው። አሁን የኢህአዴግ ሽታ የለውም ማለት ይህ ሃይል ህዝባዊ ሽታ ያለው አይደለም ማለት ነው። ከህዝባዊነት የወጣ ስላልሆነ ሄዶ ሄዶም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ለፌደራላዊ ስርአታችን ሊያጠፋ የሚችል አካሄድ እየሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ሁላችንም እንደምናውቀው ስልጣን ከህዝብ ነው። ስልጣን ከህዝብ የምርጫ ድምፅ ነው የሚገኘው። ያን የህዝብ ድምፅ መሰረት አድርጎ ደግሞ የሚሰራ ስርአት ይኖራል። ባጭሩ አሁን ያለው ግን የግለሰው ፍፁም የስልጣን ገዥነትና አንበርካኪነት ነው ያለው። የመንግስታችንን ስርአት ትርጉም ወደሌለው ደረጃ አውርዶታል። ኢህአዴግ አሁን ጠፍቷል። ትርጉም ወደሌለው ደረጃ አው የወረደው። ግንባሩም፣ ምክር ቤቱም ፓርላማዉም ትርጉም ወደሌለው ደረጃ ወርዷል። ፌደረሽን ምክር ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ነገር ምልክት ወደሆነበት ደረጃ ወርዷል። ስለዚህ አሁን ሄዶ ሄዶ የንጉሰ ነገስት አገዛዝ ተመስርቷል ማለት ነው። በቃልም እየሰማን ነው። ንጉሰ ነገስት የሚል።
.
ጋዜጠኛ (ሴቷ): ሰባተኛ ንጉሰ ነገስት ያለውን?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: አዎ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ፣ ሰባተኛው ንጉስ የሚሉ። ይህ ወዴት እንደሚሄድ የሚያሳየን ነው። ስለዝህ የግለሰቡ የስልጣን ፍፁም ገዥነትና አንበርካኪነት ነው የመጣው። ፍፁም የግለሰቡ የስልጣን ፍቱም ገዥነት ወደፊት ባህርይው ምንድን ነው የሚሆነው። አሁን በተሎ ካላስቆምነው፣ በፍጥነት ካላስተካከልነው በመሰረቱ ህዝባዊ ሊሆን አይችልም። ህዝባዊነት ማለት በህዝብ ውሳኔ የሚያምን ማለት ነው። አሁን ካጭር ጊዜ በፊት እንኩዋን የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ህዝብ ሳይወያይበት ነው ብቻውን የወሰነው። የሚገርመው በሰኔ 16 የጠራው ስብሰባ እንኩዋን ድል አምጥቻለሁና ስሙኝ ኑ ደግፉኝ ነው ያለው። ህዝብን ለማነሳሳት ተብሎ ደግፉኝ ነው የሚለው (ተበሳጭቱዋል)። ደግፉኝ? ንጉሰ ነገስት ስለሆነ ሊደገፍ ማለት ነው። ከዚያ ባለፈ እነዛ የተሸጡ ድርጅቶችም፣ ሊሸጡ የታሰቡትንም ምንም አይነት አመክኞ የሌለው ነው። አሁን የዶላር እጥረት ስላለን ምናምን። አሁን የዶላር እጥረት አገር በመሸጥ አይፈታም። መሰረታዊው መፍትሔ አገር በማልማት ነው። አገርን ለማልማት ደግሞ ስራ መስራት ያስፈልጋል። የተፈጠረ ሃብትን መሸጥ ቀላል ነው። ማንም ደላላ የሚያደርገው ነው። ለደላላ ሃብት መፍጠር ነው የሚከብደው። አሁን የተሸጡት ወይ ሊሸጡ የታሰቡ ወይ ሌላ ሼር ሊገባባቸው የተባሉት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ በ27 አመት አንዳንዶቹ ደግሞ ከዛ በፊት ቀደም ብሎ ያፈራቸው ሃብቶቹ ናቸው። ስለዝህ ሃብት ለማፍራት የሚጠይቀው ጥረት በአንድ ለሊት ልታጠፋው ትችላለህ። ለማጥፋት ማለት ነው። ስለዝህ በዝህ ጉዳይ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያገባዋል። ይህ ስራ ሲሰራ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊማከርበት ይገባል ማለት ነው። የህግ የበላይነትም ጠፍቷል። በግለሰቡ ውሳኔ ወንጀለኞች፣ በሃይል መንግስትን ለመገልበጥ የሞከሩ ወንጀለኞች፣ ሰው የገደሉ ወንጀለኞች ተፈተዋል። አሁን ደግሞ ምን እያየን ነው? በአለም በአሜሪካ ጉልበት ተረግጠው በአሜሪካ ቁጥጥር ስር ከገቡት እንደነ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ያሉ አገሮች ውጭ FBI ሌላ አገር ገብቶ አያውቅም። FBI ደግሞ ለምርመራ መጥቷል እየተባለ ነው።
.
ጋዜጠኛው (ወንዱ): ይህን ጉዳይ ከደህንነት አንፃር እስኪ እንየው?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: እ ደህንነት ማለት ሉአላዊነት ነው። የአገር ሉአላዊነት ነው። እኛ FBI ይሁን ከ FBI በላይ አቅም በኢትዮጵያ የተገነባ አቅም አለን። ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ እርዳታ ጠይቃ አታውቅም። ስለዝህ በራስህ አቅም የማትተማመን ከሆንክ ሞተሃል ማለት ነው። ጥገኛ ነህ ማለት ነው። ጥገኛ ሎሌ ነህ ማለት ነው።
.
ጋዜጠኛው (ወንዱ): ታድያ ይህን ምን ያመጣው ነው ትላለህ? በአቅማችን አለመተማመን ያመጣው ነው ወይስ አቅም የለንም ማለት ነው? ምን ማለት ነው?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: ቀደም ብየ ነገርኩህ። ይህ ሃይል በአገሪቱ አቅም የሚያምን አይደለም። በአገሪቱ አቅም የተሞረከዘ አይደለም። ህዝብ ነው ያገር አቅም ማለት። ህዝብ የፈጠራቸው ድርጅቶች ናቸው ያገር አቅም። ስለዝህ በነዚህ የማይተማመን ከሆነ ጥገኛ ነው ማለት ነው። ነገ ጧትምኮ መከላከያም አያስፈልገንም ሊባል ይችላል። በ እነ ኢራቅና በአፍጋኒስታን ዘመተው black water የሚባሉ አሉ የአሜሪካ ሲቪል ሆነው የመከላከያ ስራ የሚሰሩ። አሜሪካኖች outsourcing ነው የሚሉዋቸው። በሶማሊያም ገብተው ነበር። ከእንግዲህ ብሁዋላ እነሱ ወደ ኢትዮጵያ የማይገቡበት ምክንያት አይኖርም።
.
ጋዜጠኛ (ሴቷ): እና ይህ የሚያሳየው አሁን ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ገብቶ ያለው ቅድም ስትገልጠው እንደነበር በሰኔ ፩፮ የተፈፀመ የቦንብ ጥቃት ነበር። ያ የቦንብ ጥቃት ማን ለማን ነበር ሊያጠቃ አስቦ ነው የነበረው ሊመረመር ነው ተብሎ ነበር መጀመሪያ ብሁዋላ ግን የፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር ሲገልፅ እንደሰማነው ደግሞ ለእነዛ በቁጥጥር ስር ውለው ተይዘው ያሉ ሰዎች ጭምር ሊመረምራቸው ነው። ፈረንጆቹ የተያዙትን ሃበሾች ማንን ልታጠቁ አስባችሁ ነበር ብሎስ ሊመረምራቸው ነው። ጥቃቱ የተፈፀመበት ሁኔታን ማቴሪያሉን ጨምሮ አስመልክቶ ቦንቡን መመርመር አንድ ጉዳይ ነው። ለእነዛ ሰዎች ለእነዛ ሃበሻ ሰዎች ግን ቅድም ስትለው ከነበረው ጋር እንድታያይዘው ስለፈልኩ ነው እኔ በቋንቋየ በትግርኛ መናገር እየቻልኩይ ትግርኛ የሚናገር ሰው ሊመረምረኝ እየቻለ ስለላም ከሆነ በመሰለል ሊያውቀኝ እየቻለ ፈረንጅ ግን ለማን ነበር ልታጠቂ አስበሽ የነበረው ብሎ እንዲመረምረኝ ማድረግ በመሰረቱ አግባብነት አለው ወይ? በመሰረቱ አስተሳሰቡ በራሱ ጤነኛ ነው ወይ? ለእኔ ብዙም ግልፅ አልሆነልኝም። እኔ እንደሚመስለኝ ያን ቦንብ ለመመርመር አቅም እንኩዋ ቢያንሰን ቦንቡን ለሰሩት ሰጥተን ይቺን እስኪ መርምሩዋት ብንላቸው እነሱ ስለሰሩት ችግር ላይኖረው ይችላል። የእኛ የራሳችን ቋንቋ የሚናገረውን ጥቃቱ ለምሳሌ እኔ ወይ ሌላ ሰው እንኩዋን ፈፅሞት ቢሆን በፈለገው መለኪያና በፈለገው ሲስተም ሊመረምረኝ እየቻለ ፈረንጅ እንዲመረምረኝ ማድረግ አግባብነቱ ምንድን ነው። የህግ አባብነትስ ያለው ነው ወይ?
.
ጀነራል ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ: ጠብቁ ይቀጥላል………..

Source: Satenaw


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu