Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Breaking News

15

Published Posted on by | By TZTA News

15

Spread the love

Thehay                                                                                                             ወ/ሮ ፀሐይ አድማሱ                                                                                                           የኢትዮጵያ ማህበ በቶሮንቶና አካባቢው ምክትል ፕሬዘዳንት

ሴፕቴምበር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶ አዘጋጅነት በክርስቲና በክርስቲና ብሉር በሚገኘው መናፈሻ ከቶሮንቶና አካባቢው እንዲሁም ከሃሚልተን፣ ከኪችነር፣ ከጎልፍ፣ ከኦታዋ፣ ከመሳሰሉት አካባቢዎች በመምጣት የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2006 ዓ.ም. እና 15ኛው የኢትዮጵያ ቀን ምክንያት በማድረግ በደመቀ ሁኔታ አክብሮ ውሏል። በዚህ እለት ጥሪ የተደረገላቸው ከካናዳ ፓርላማ አባል፣ የኦንቴሪዮ የፖሊስ አዛዥ እንዲሁም የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች እንግዶች ኢትዮጵያውያን በክብር ተገኝተዋል።


ምንም እንኳን ዝናቡ ከጠዋት ጀምሮ ሌሊቱንም ጭምር ቢዘንብም ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ቀንና አዲስ አመት ተሰብስቦ ለማክበር የከለከላቸው ምንም ነገር አልነበረም። ከሰአት በኋላም ዝናቡ እያባራ በመምጣቱ የመድረኩ አስተዋዋቂ ዶክተር ዮሃንስ ወደ መድረኩ በመዝለቅ ለዛ የተሞላበት አዝናኝና ተደናቂ ንግግር የከፈቱ እርሳቸው ነበሩ። በመቀጠልም እንኳን ደህና መጣችሁ፣ ለ15ኛው የኢትዮጵያ ቀንና እንዲሁም ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ በማለት ለሕዝቡ ምኞታቸውን ገልፀዋል። በመቀጠልም በመድረኩ ላይ የነበሩትን የልዩ ልዩ የእስልምናና የክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎችን አስተዋውቀዋል። እያንዳንዳቸው ለተሰበሰበው ሕዝብ በየተራ በመጋበዝ ንግግር አድርገዋል። በመጀመሪያም በቅደም ተከተል የሃይማኖት አባቶች እንደሚያምኑበት ለሕዝቡ ቡራኬ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ቀን እያደገ እየለመለም እንዲሄድ ምኞታቸውን ገልጸዋል፣ ለ2006 ዓ.ም. አዲሱ አመትና እንቁጣሽም እንኳን አደረሳችሁ መጪው ዓዲስ አመትም የሰላም፣ የደስታ የፍቅር እንዲሆን አምላክም ይህን እንድፈጽም ተማጽነዋል።


በመለጠቅም ሕፃናት ሴቶች ምን አልባት ባልሳሳት በ5-7 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወደ መድረኩ ብቅ በማለት የፋሽን ሾው አሳይተዋል። እነኚህ እምቦቃቅላ በተለያዩ በኢትዮጵያ ባህል አለባበስ ያንጸባርቁ ተራ በተራ ወደ መድረኩ ሲወጡ ተመልካቹ ደስታውን በእልልታ፣ በጩኸትና በማድነቅ ነበር የተቀበላቸው። እጅግም በጣም በጣም ድንቅ ነበሩ። የእነሱን ምስል ለማስቀረት ተመልካቹ ቪዲይውንና ካሜራውን እያስተካከል ግፊያውና ትንቅንቁ ሌላ ነበር። እነኚህ ሕጻናት የተለያዩ ብሔረሰቦች ልብስ ለብሰው በፈገግታ በእስክስታ ፋሽን ሾው ሲያሳዩ ኢትዮጵያን ወክለው የሚታዩ ነበሩ፣ ተምልካቹም በመደንቅ በከፍተኛ ደረጃ ደስታውን፣ በጩኸት፣ በጭብጨባ እደጉ ተመንደጉ በማለት አድናቆቱን ገልጾላቸዋል።

ከዚያም በመቀጠል የኢትዮጵያ ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ፀሐይ አድማሱ ከዚህ በሚከተለው ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። “በቶሮንቶና አካባቢው እንዲሁም በአጋጣሚ ከቶሮንቶ ርቃችህ በምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ለኢትዮ-ካናዳውያን ቀንና ለአዲሱ የኢትዮጵያውያን አመት በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

ይህ በየአመቱ በጉጉትና በናፍቆት እየተጠበቀ የምናከብረው በዓል፣ አንድነታችንን የምንገልጽበት ፍቅራችንንና አኩሪ ባህላችንን ለትውልድ የምናስተላልፍበት፣ ለካናዳውያንና ለሌላው ዜጋ የምናሳይበትና የምንጋራው በመሆኑ በየጊዜው በዓይነትም ሆነ በቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ልንኮራበትና ልንጠብቀው የሚገባን የበዓል ቀን ነው።

የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶና አካባቢው ከሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች በተጨማሪ ህብረተሰቡን በማገናኘት፣ ታሪካችንንና ባህላችንን በመጠበቅና በማስተላለፍ ለቶሮንቶና አካባቢው ኢትዮ-ካናዳውያን መሰብሰቢያና መኩሪያ በመሆን በበጎ ፈቃደኝነት በቦርድ አባሎች እንዲሁም በጽሕፈት ቤቱ ሰራተኞች ጥረት የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።


ከጥቂት ወራቶች በፊት በቦርዱና ፈቃደኛ በሆኑ የኮሚኒቲ አባሎች ትብብርና እርዳታ፣ በማህበሩ ውስጥ ተፈጥረው የነበሩትን ቅሬታዎች የመከፋፈል ችግር በውይይት ለመፍታት እንዲቻል ወራቶችን በፈጀ መሰናዶ፣ በሜይ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደው የአንድ ሙሉ ቀን የውይይት መድረክ በማህበራችን ሰላም እንዲሰፍን መከባበርና መደማመጥ ያሳየና ያስቻለ በጣም የተሳካ መልካም ጅማሮ የወደፊት የማህበሩን እድገትና እንቅስቃሴ አቅጣጫ የሚያሳይ መልካም እርምጃ በመሆኑ ለስኬት ከጅማሮው እስከ ፍጻሜው የተባበሩንን ሁሉ እጅግ ላመሰግን እወዳለሁ።
የኢትዮያ ማህበር በቶሮንቶ አካባቢው ከፌድራል፣ ከኦንቴርዮና ከሲቲው እንዲሁም የተለያዩ ፕሮግራሞች ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሚገኝ ፈንድ ስራውን ሲያከናውን ከጎኑ ደግሞ ለብዙ አመታት በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ ካናዳውያን በበጎ ፈቃደኝነት ገንዘባቸውን እውቀታቸውን ጉልበታቸውንና ጊዜአቸውን መሰዋት እያደረጉ ያለውን አራያነት ከፍተኛ ግምት ልንሰጠውና ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸውል እላለሁ።

ይህን የበጎ ፈቃደኝነት ስራ እንደ አኩሪ ባህል በመጠበቅ ለወጣቱ ትውልድ ለልጆቻችን እያበረታታን እኛን ለመተካት እንዲችሉ መንገር ማስተማርና ማበረታታት ይገባናል። ከኛ የተሻለ አስተሳሰብና እውቀት እየገበዩ ያሉት ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት ይህን መሃበር ከፍተኛ ደረጃ ልያደርሱት ይችላሉ፤ ታሪክና ባህላችንን ተረክበው እንዲጓዙ ለማድረግ ዛሬ ካልጣርን ዛሬ ካልደከምን ቀጣይነቱ ያጠራጥራል ወላጆች ይህን ጥሪ እንደምትቀበሉ ተስፋ አደርጋለሁ።

ይህ የዘንድሮ በአል እንዲከበር የደከሙትን የበአል አዘጋጅ ኮሚቴ አባላትን የገንዘብ አስተዋጽዎ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ በሙያቸው አስተዋጽዎ ላደረጉ ባለሙያዎች፣ በበአሉ የተካፈሉ የንግድ ድርጅቶችን፣ የሃይማኖት ተቋማትንና አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንዲሁም ሌት ተቀን የደከሙትን የቦርድ አባሎች ከልብ አመሰግናለሁ።
ለማህበራችን እንቅስቃሴ የበጀት ድጋፍ ለሚያደርጉልን የመንግስትና የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች በጣም አመሰግናለሁ። በዚህ በዓል መከበር ከመጀመሪያ ጀምሮ የተለያዩ ፈቃደኞችን በመስጠትና በመተባበርና የቶሮንቶ ከትማ ማዘጋጃ ቤት ላደረገልን ሁሉ ምስጋናዬና አቀርባለሁ።

በመጨረሻም አዲሱ የኢትዮጵያውያን 2006 ዓመተ ምህረት የሰላም የፍቅር የብልጽግና ዘመን እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ። መልካም በዓል። በማለትንግግራቸውን ፈጽመዋል። በማያያዝም አጠር ያል መለልዕት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ዘክረዋል።
የካናዳ የፓርላማ አባል የኤን ዲ.ፕ. ተወካይና የኦንታሪዮ የፖሊስ አዛች ለሕዝቡ ንግግር አድርገዋል። በተለይ የፓርላማው ተወካይ ለኢትዮጵያ ማህበር ም/ፕሬዝዳንት የማስታወሻ ስጦታ አድርገዋል።

በመቀጠልም የአቶ ነጋዬ ሺበሺ ለማህበሩ ባደረጉት ከፍተኛ አስተዋፆኦ በነበራቸው የመግባብት ችሎታ እንዲሁም ትሁትና ሰውን አክባሪ በመድረኩ ላይ በትልቁ ምስላቸውን ለሕዝቡ ቀርቧል። በልጆቸቸው ስለ ሳቸውያላቸውን ደግነት ለሕዝቡ ዘክረዋል። በዚህ እለት ሁሉም ሕዝብ ሃዘኑን ለቤተሰቡ አቅርቧል። የሶስት ደቂቃ ፀሎት ተደርጓል። እኛም ለቤተሰቡ መፅናናት ይስጣቸው እንላለን።

በመቀጠልም ከመድረኩ ዝቅ ብለን ስንሄድ ሁለት ታላላቅ ቡድኖች የእግር ኳስ ጨዋታ ነበራቸው እንርሱም፣ በቶሮንቶ የታወቀው ቡድን የማሪያም ቡድንና ከሃሚልተን ተወክሎ የመጣው ቡድን ነበር።

ሁለቱም ጥሩ መፎካከር አድርገው የሃሚልተን ቡድን በማሸነፉ የዋንጫ ሸልማት ተበርክቶላቸዋል። ለቶሮንቶ ቡድን የሜዳሊያ ሽልማት ተደርጓል። የዚህ አይነት የእግር ኳስ ጨዋታ ቢበረታታና ቀደም ብሎ ተጀምሮ ሌሎችንም ቡድኖች ጨምሮ ቢካሄድ መልካም ነው እንላለን።

ሌላው ድንቅ የሆነው በዚሁ ፓርክ ከመድረኩ ባሻገር በጣም ትናንሽ ድንኳኖች ተተክሎ በዚያ የመጣው ሕዝብ ሲጎበኛቸው መታየቱ ነው። እነኚ የተለያዩ ድንኳኖች የተለያዩ ሙያትኞችን የያዝ ሲሆን የኢትዮጵያን ቀን ለማከበር የሚመጣውን ሕዝብ የሚያስተነግዱ ልዩ ልዩ ቢዝነስና እንዲሁም ያልሆኑትንም ያቅፋል። በቢዝነስ አንጻር ስንመለከት እንሹራንስ፣ ሕግ፣ ሪል ኢስቴት፣ የመሳሰሉት ሲኖሩ፣ በሌላ መንገድ የተለያዩ ሬስቶራንቶች የአገር ባህልና እንዲሁም ሳንድዊች ሌላም ጭምር የሚያቀርቡ፣ የአገር ልብስ፣ ቲ ሸርት፣ የእንጨት ስራ ውጤት፣ የቴለፎን ካርድ ሽያጭ፣ ቡና ማቅመስና የተቆለውን ሆነ ጥሬውን መሸጥ ሌላም ሌላም ነበሩ፣ እንዲሁም የተለያዩ እምነት ያላቸው ክርስቲያኑ ሆነ ሙስሊሙ በየድንኳናቸው ሆነው ሕዝቡን ሲያስተናግዱ ታይተዋል። በኢትዮጵያ ማህበር የተዘጋጅ በኢትዮጵያ የታውቁ በታሪክ፣ በነገሥታት መሪዎች ሌሎችንም እንዲሁም በሰዕል መልክ በማቅረብ ለሕዝቡ ቀርቦ በኤግዝቢሽን መልክ ታይቷል።ቢራ መጠጣት የሚፈልገው ለራሱ ክልል ተበጅቶለት እየተዝናና ተስተናግዷል። ፖሊስ ጠባቂ ቢኖረው በጨዋንት በመከባበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነቱን አስመስክሯል። በዚህ እለት በብዙ ሺህ ሕዝብ እንደፍላጎቱ አስተናግደዋል። አብዛኛዎችን እንደጠየቅናቸው በዝግጅቱ እንደረኩ ነግረውናል።

በመናፈሻው ሜዳ ላይ ሲታይ ሌላው ጥሩ ጎኑ ተለያይቶና ተጠፋፍቶ የነበርው መገናኛ መሆኑ ነው። እኔ እንኳን ብዙ የማውቃቸውን አግንቼ ሰላምታ ተለዋጬአለሁ፣ ቆም ብዬም አውግቻለሁ። ሌላውም እንዲሁ እየተገናኘ በግሩፕ በግሩፕ በመሆን ሲወያይ ማየቱ ይህ በአመት አንድ ቀን የሚከበርው የኢትዮጵያ ቀን በቂ ስላልሆነ ለሚቀጥለው አመት ሁለት ቀን ቢሆን ጥሩ ነበር በማለት አስተያት የሰጡም አሉ። ስለሆነም ማህበሩ ይህንን በጎ አስተሳሰብ ቢቀጥልበት መልካም ነው ነው።

እንደገና ወደ መድረኩ ስንቀርብ የተለያዩ ሙዚቃዎች ውዝዋዜዎች ቀርበዋል። በአሁኑ ጊዜ ዝናው እየጨመረ ታውቂነትን ተጎናጽፎ የሚገኘው በወ/ሮ ሱዚ የሚመራው ስብሰብ በሉ የተባለው ድርጅታቸው ወጣቶችን በተለያዩ ብሔረሰብ ውዝዋዜ የተካኑትን በሃገራዊ ሙዚቃ ትጅበው በማቅረብ ወጣቱን ልጁም ሳይቀር ጎልማሳውም እስክታውን እንዲሁም አዛውንቱ በመቀመጫው ላይ እንዲወዛወዝን እንዲደሰት አድርገዋል።

እጅግ የሚደነቁና አስደሳች ነው በማለት አስተያየታቸውን አንድ ተመልካች ሃሳባቸውን ለግሰዋል። የተለያዩ ብሄረሰቦች ውዝዋዜ ድምፃዊ ዘፋኞችም ወደ መድረኩ በመምጣት ሕዝቡን አስደአስተዋል። በእውንቱ የተሰበስበው ሕዝብ ከመብዛቱ ያን ያህል ደስታውና ጭፈራው ኢትዮጵያዊቱን አስመስክሯል። አንድም ኳ ሳይል በሰላም ዝግጅቱ አብቅቷል።

ስለሆነ ከዚህ ሁኔታ በመነሳት ለሚመጣው 16ኛው የኢትዮጵያ ቀንና እንዲሁም በኢትዮጵያ አዲሱ አመት አከባበር ሁለት ቀን ቢሆን መልካም ነው በማለት አንድ ግለሰብ አስተያይታቸውን ለግሰዋል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu