Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic

( )

Published Posted on by | By TZTA News
Spread the love

 ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ
ጎልጉል:- ታዋቂ የሚባሉት የኪነት ባለሙያዎች በአብዛኛው የህዝብ አንደበት ከመሆን ይልቅ “አጫፋሪነትን” መርጠዋል በሚል በሚዘለፉበት ወቅት ላይ ከየአቅጣጫው ምስጋና፣ ውዳሴና አድንቆት የሚዘንብበት ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ።
በካሊፎርኒያ ግዛት የሳን ሆዜ ከተማ (City of San Jose) በኢትዮጵያና በኤርትራ ወዳጆች ፎረም ስም ቴዲ አፍሮን የሸለመው ፌብሩዋሪ 15 ቀን 2013 ነው። የምስጋና ሽልማት /Commendation Award/ የተሰጠው ቴዲ አፍሮ ስለተሰጠው ሽልማት የቀረበው ምክንያት “ራሱን ለሰላምና ለመፈቃቀር አግልግሎት አሳልፎ ሰተ በጣም ተደናቂና ታዋቀቂ የሙዚቃ ሰው” በሚል ሙገሳ መሆኑን የቴዲ አፍሮ የፌስቡክ ገጽ ጠቁሞዋል።
ቴዲ አፍሮ በኤርትራ አዲስ ትውልድ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው የጥበብ ሰው ነው። አርቆ በማስተዋልና ጊዜና ወቅት ጠብቆ አነጋጋሪ ስራ በማቅረብ ለጥበቡ የተፈጠረ ሰው መሆኑንን በተደጋጋሚ አሳየው ቴዲ በፑንት ላንድ ሞት ሊፈረድበት የነበረውን የትግራይ ተወላጅ ከመንግስት ቀድሞ በመቶ ሺዎች በመክፈል ነፍስ ያተረፈ የዘመኑ ድንቅ ሰው ነው። ቴዲ አስተዋዩን መሪ አጤ ሚኒልክን ከተኙበት ቀስቅሶ ታሪካቸውን በማደስም በኩል የሰራው ስራ “ጥቁር ሰው” የሚለውን አሻራ ለተተኪው ትውልድ እንዲቀመጥለት አድርጓል

በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር                                                                                                        
      ጎልጉል;- የአገራቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል፤ የአገራቸውን የወደፊት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ … ሁኔታ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የውጪ ፖሊሲ ዕቅድ በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት ለምክርቤቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኦባማ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡ አፍሪካና ቻይናም የንግግራቸውን ሙሉ ቀልብ የሳቡ ነበሩ ባይባልም  ሳይጠቀሱ አልታለፉም፡፡ በተለይ ስለአፍሪካ እንዲህ ብለዋል፤-;- የአገራቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል፤ የአገራቸውን የወደፊት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ … ሁኔታ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የውጪ ፖሊሲ ዕቅድ በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት ለምክርቤቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኦባማ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡ አፍሪካና ቻይናም የንግግራቸውን ሙሉ ቀልብ የሳቡ ነበሩ ባይባልም  ሳይጠቀሱ አልታለፉም፡፡ በተለይ ስለአፍሪካ እንዲህ ብለዋል፤-
        ‹‹… የተለያዩ አፍቃሪ የአልቃይዳ ወኪሎችና አክራሪዎች ከአረብ ምድር እስከ አፍሪካ ብቅ እያሉ መጥተዋል፤ እነዚህ ቡድኖች ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ እንደዚያው እያደገ መጥቷል፡፡ ይህንን አደጋ ለመቋቋምም በአስር ሺዎች የሚጠጉ ልጆቻችንን በመላክም ሆነ አገራትን መቆጣጠር አያስፈልገንም፡፡ ይልቁንም እንደ የመን፤ ሊቢያ እና ሶማሊያ ያሉት አገሮች የራሳቸውን ደኅንነት እንዲያጠናክሩ እንረዳቸዋለን፤ በማሊ እያደረግን እንዳለነው አሸባሪዎችን እየተዋጉ ያሉትን ወዳጆቻችንንም እንደግፋለን፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ባለን አቅም ሁሉ በአሜሪካውያን ላይ አደጋ ሊጥሉ በሚችሉ አሸባሪዎች ላይ ቀጥተኛ እርምጃ እንወስዳለን፡፡››        ‹‹… የተለያዩ አፍቃሪ የአልቃይዳ ወኪሎችና አክራሪዎች ከአረብ ምድር እስከ አፍሪካ ብቅ እያሉ መጥተዋል፤ እነዚህ ቡድኖች ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ እንደዚያው እያደገ መጥቷል፡፡ ይህንን አደጋ ለመቋቋምም በአስር ሺዎች የሚጠጉ ልጆቻችንን በመላክም ሆነ አገራትን መቆጣጠር አያስፈልገንም፡፡ ይልቁንም እንደ የመን፤ ሊቢያ እና ሶማሊያ ያሉት አገሮች የራሳቸውን ደኅንነት እንዲያጠናክሩ እንረዳቸዋለን፤ በማሊ እያደረግን እንዳለነው አሸባሪዎችን እየተዋጉ ያሉትን ወዳጆቻችንንም እንደግፋለን፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ባለን አቅም ሁሉ በአሜሪካውያን ላይ አደጋ ሊጥሉ በሚችሉ አሸባሪዎች ላይ ቀጥተኛ እርምጃ እንወስዳለን፡፡››

የካናዳ ኩባንያ በደቡብ ኦሞ ነዳጅ ፍለጋ እንዲያካሂድ ተጨማሪ መሬት ተሰጠውየካናዳ ኩባንያ በደቡብ ኦሞ ነዳጅ ፍለጋ እንዲያካሂድ ተጨማሪ መሬት ተሰጠው                                                                                      የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም                                                                                      የካቲት ፩፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
     ኢሳት ዜና:-ካናዲያን ኤክስፕሎረር አፍሪካን ኦይል የተሰኘው ኩባንያ አዲስ መሬት የተሰጠው በምስራቅ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው። ኤክስፕሎረር አፍሪካ በደቡብ ኦሞ የነዳጅ ፍለጋ በማካሄድ ላይ ካለው ቱሎው ኦይል ጋር በሸርክና የሚሰራ ድርጅት ነው።     ኢሳት ዜና:-ካናዲያን ኤክስፕሎረር አፍሪካን ኦይል የተሰኘው ኩባንያ አዲስ መሬት የተሰጠው በምስራቅ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው። ኤክስፕሎረር አፍሪካ በደቡብ ኦሞ የነዳጅ ፍለጋ በማካሄድ ላይ ካለው ቱሎው ኦይል ጋር በሸርክና የሚሰራ ድርጅት ነው።
     ቱሎው ኦይል በደቡብ ኦሞ የሚያካሂደው አሰሳ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ይናገራል። ድርጅቱ ተሳክቶለት ነዳጅ ማውጣት ከጀመረ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል።     ቱሎው ኦይል በደቡብ ኦሞ የሚያካሂደው አሰሳ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ይናገራል። ድርጅቱ ተሳክቶለት ነዳጅ ማውጣት ከጀመረ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል።
     ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ድርሻ ከ10 በመቶ የማይበልጥ ቢሆንም በአገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ ሙስና ግምት ውስጥ ሲገባ፣ ህዝቡ ከነዳጁ ሀብት ብዙም ተጠቃሚ ይሆናል ተብሎ እንደማይታሰብ ተንታኞች ይናገራሉ።
     በደቡብ ኦሞ ዞን የአንድነት ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው በአካባቢያቸው ነዳጅ መገኘቱን የኩባንያዎቹ ባለስልጣናት በተለያዩ መንገዶች እየገለጡ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን እስካሁን ይፋ ለማድረግ አልፈቀደም። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት በአካባቢው ነዳጅ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።

ፓትሪያርክ ለማሾም የሚደረገ ው የምረጡኝ ዘመቻ ቀጥሏል
የካቲት ፩፮ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
     ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ የፓትሪያርክ የምርጫ ቅስቀሳ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች ገለጹ። ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገብ የቆየውን የፓትሪያርክ የምርጫ ቅስቀሳ፣ ፓትሪያርክ ይሆናሉ ተብሎ ባለፈው ሳምንት በተሰራጨው ዘገባ ላይ ስማቸው የተነሳው አቡነ ሳሙኤል አረጋግጠዋል።
አቡነ ሳሙኤል ለአዲስ አድማስ በሰጡት አጭር ቃለምልልስ እንደገለጡት በምርጫው ዙሪያ የተለያዩ ቡድኖች ተፈጥረው የምርጫ ቅስቀሳ እያካሄዱ መሆኑን አጋልጠዋል። አቡነ ሳሙኤል ” በየብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ፣ በእኔም ቤት ሳይቀር እየዞሩ እገሌን ካልመረጣችሁ፣ ካላስመረጣችሁ የሚሉ አካላት እንዳሉ ግልጽ ነው” ያሉት አቡነ ሳሙኤል ፣ “ስልጣን ባለው አካል መንፈሳዊ ስልጣንን ለመያዝ የሚደረገው ሽር ጉድ ሁሉ በፍትህ መንፈሳዊ፣ በቀኖና ቤተክርስቲያን የተወገዘ መሆኑን” በመግለጽ ድርጊቱን አውግዘዋል። እንዲህ ሆኖ የሚሾመው አባትም ቢሆን ሲመቱ ስጋዊ ሹመት ይሆንና በነፍስም በስጋም ያጎድለዋል፣ ያለጊዜውም ሊያስቀስፍ ይችላል በማለት አስጠንቅቀዋል። በመሆኑም ይላሉ አቡነ ሳሙኤል ” በምርጫው የሚሳተፉ ካህናትና መእምናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ማሰብ መወሰንና መቆም ይገባቸዋል።”
     አቡነ ሳሙኤል ባለፈው ሳምንት ” ፓትሪያርክ ሆነው ለመመረጥ ቅስቀሳ ጀምረዋል” የሚለውን የሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባ አስተባብለዋል። ” ምረጡኝ ብየ አላልኩም፣ ምረጡኝ ብየ አላውቅም” ያሉት አቡነ ሳሙኤል፣ ይህንን የሚያስወሩት በምርጫው ዙሪያ የተደራጁ ቡድኖች ናቸው” ብለዋል። አቡነ ሳሙኤል ” ፓትሪያርክነት የአባትነት፣ የቡራኬ ስልጣን ነው፤ ለእኔ አገልጋይነት ይሻለኛል፤ አገልጋይ መሆን ነው እንጅ፣ አዛዥ፣ ገዢ፣ አሳሪ፣ አሳሳሪ መሆን አይደለም” በማለት ተናግረዋል።
     አቡነ ሳሙአል ፓትሪያርክነት በ ” አዛዥነት፣ በገዢነት፣ በአሳሪና አሳሳሪነት የተመለከቱበት መንገድ ለውዝግብ ሳይዳርጋቸው እንደማይቀር ይታመናል።
     አቡነ ሳሙኤል ቀጣዩ ፓትሪያርክ ይሆናሉ ተብሎ ከተገመተ በሁዋላ በእጩነት አለመቅረባቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ እየተፈጸመ ያለውን ሴራ እንደሚያሳይ ዘጋቢያችን ገልጿል። የአቡነ ሳሙኤል ንግግር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤትክርስቲያን የገባችበት የዝቅጠት ደረጃ ያሳያል ያለው ዘጋቢያችን፣ የእርስ በርስ መጣላለፍ፣ የስም ማጥፋት፣ ለገዢው ፓርቲ ሎሌ ሆኖ መቅረብ፣ መንፈሳዊነትን ረስቶ ለስጋ ማደር፣ ጥቅምን ማሳደድ፣ ዘረኝነት እና ንግድ” የቤተክርስቲያኑዋ መገለጫ እየሆኑ ነው ብሎአል።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያሪክ፤ መሠረተ ቢስ መረጃዎችን በማስተላለፍ ህዝቡን ለማደናገር ይሠራሉ በማለት ክስ የመሠረተባቸው አራት ጋዜጠኞች ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ፡፡
     በስልክ ከፖሊስ በደረሳቸው ጥሪ መሠረት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቀርበው የተከሳሽነት ቃላቸውን የሰጡት፤ የ “ሎሚ” መጽሔት፣ የ “ሊያ” መጽሔት፣ የ“አርሂቡ” መጽሔት እና የ “የኛ ፕሬስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጆች ናቸው።እንደ አዲስ አድማስ ዘገባ፤ጋዜጠኞቹ ፎቶግራፍ እና አሻራቸው ተወስዶ በዋስ ተለቀዋል፡፡ የ“ሎሚ”፣ የ “ሊያ” እና የ “አርሂቡ” መጽሔት ዋና አዘጋጆች ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ለፖሊስ ቃል የሰጡ ሲሆን፤ የ “የኛ ፕሬስ” ዋና አዘጋጅ ደግሞ ሃሙስ የካቲት 14/ ቀን ቃሉን ሰጥቷል፡፡
     የየኛ ፕሬስ ጋዜጣ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ስዩም ለአድማስ እንደገለፁት፤ ዋ“ሲኖዶስ ተከፋፍሏል” እና “ስደተኛው ሲኖዶስ መግለጫ አወጣ” በሚሉ ርዕሶች በጋዜጣው ላይ በወጡ ዘገባዎች በዋና አዘጋጁ በካሳሁን ወልደዮሐንስ ላይ ክስ ቀርቦበታል፡፡
     የ“አርሂቡ” መጽሔት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሣሁን ተስፋዬ በበኩላቸው፤ በመጽሔቱ የታህሳስ ወር እትም ቁጥር 40 ላይ “አቡነ ማቲዎስና አቡነ ሣሙኤል ተፋጠዋል” በሚል ባወጣው ዘገባ ክስ ቀርቦባቸዋል። በክሱ ዙሪያ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አበራ የተከሳሽነት ቃሉን ሰጥቷል።
     የ“ሎሚ” መጽሔት ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ እንዳሉት ደግሞ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ የሆነችው ወ/ት ብዙአየሁ ጥላሁን በሶስት ርዕሰ ጉዳዮች ለቀረበባት ክስ ማክሰኞ ዕለት ቃሏን ከሠጠች በኋላ -እርሳቸው የመኪናቸውን ሊብሬ አስይዘው በዋስ አስለቅቀዋታል።ዋና አዘጋጇ “መንግሥት በሃይማኖት፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም” የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ፣ ህዝብ- በመንግስትና በቤተክርስቲያን አመኔታ እንዳይኖረው የሚያደርግና ህዝብን ለአመጽና ለሁከት የሚያነሳሳ ጽሑፍ አትማ አሠራጭታለች “ የሚሉ ክሶች የቀረቡባት ሲሆን ለሁሉም ክሶች ቃሏን መስጠቷን አቶ ግዛው ገልፀዋል፡፡
     የ“ሊያ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መላኩ አማረ በበኩላቸው፤ ስለ ጉዳዩ ዋና አዘጋጇ ብዙም የምታውቀው ስለሌለ እሣቸው የተከሳሽነቱን ቃል እንደሰጡና በክስ ዝርዝር መግለጫው ላይም ከሳሽ ሆነው የቀረቡት አቡነ ናትናኤል መሆናቸውን ተናግረዋል።
     መጽሔቱ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀጣይ እጣ ፈንታ ምንድነው?” በሚል በቁጥር 19 እትሙ ባቀረበው ዘገባ ክስ እንደቀረበባቸውም አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡
     ጋዜጠኞችን በመክሰስ፣በማሰር፣በማዋከብና በማሳደድ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱትና የፕሬስ ጠላቶች ከሚባሉት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ እንደሆነች ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ኮሚቴ(ሲፒጄ) በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu