IN CONVERSATION WITH THE MAKER OF – HOPE

Posted on by   | Reply

IN CONVERSATION WITH THE MAKER OF - HOPE

Solomon Abebe is a resident of Toronto, Canada. He is also the director of a new documentary called - HOPE. The new documentary has been sumbitted for reveiw and potential competition with the prestigious Toronto Film Festival as well as the New York documentary film festival. Solomon A K A.....

Link

 


 አቶ ወሰን ይጥና የኢትዮጵያን ማህበር በቶሮንቶና አክካባቢውፕሬዘዳንት


ለዚህ ቃለ መጠይቅ እንዳደርግ እድሉን ስላገኘሁ አመሰግናለሁ። በቀጥታ ወደ ጥያቄው እሄዳለሁ።

ትዝታ
የኢትዮጵያ ማህበር ለፕሬዘዳንትነት ከተመረጡበት ካለፈው ዲሴምበር ጀምሮ በማህበሩ የተፈጸሙትን ዋና ዋና ክንውኖች ቢገልጹልን?

አቶ ወሰን፦
በጣም አመሰግናለሁ። ምክንያቱም ለማህበሩም ሆነ ለኮሚኒቲው ፈቃደኛ ሆነህ ማህበሩ የት እንደደረሰ ለማሳወቅ በመጣርህ አመሰግናለሁ። እንግዲህ የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶና አካባቢው ፕሬዘዳንት ሆኜ የተመረጥኩት በኦክቶበር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዲሴምበር ድረስ ያለውን ሁኔታ በትዝታ ጋዜጣ ላይ ለመገለጽ ተሞክሯል። ከዚያ በኋላ ያለውን በአብዛኛው በዋናነት መጠቀስ አለበት ብዬ የማምነው ቀደም ሲልም በተከታታይ በጋዜጣው ላይ ውጥቷል።

ፎረም የመወያያ እና የመነጋገሪያ መድረክ እሱን በዋናነት እናይዋለን። ኖቨምበር 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የኮሚኒቲ ምክር (ኮንሰልቴሽን) አካሂደን ነበር። የኮሚኒቲ አባሎች፣ እንዲሁም ወጣቶች የተለያዩ ሰዎች በተገኙበት ይህ ፎረም እንዴት የት ቢዘጋጅ የሚል ጠቋሚ ጥያቄዎችን በማቅረብ በመያዝ ዲሴምበር 1 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የግማሽ ዓመት ስብሰባ፣ አሳቡን እንደገና አንስተን በእለቱ በተገኙት ከማህበሩ አባላት ጋር ተወያይተን፣ ሃሳቡን መቀጠል እንዳለብን ጠንከር ያለ መልዕክት አገኘን። ከዚያም ወሩ የበአላት ወር ስለነበር ከዚያም በጀነዋሪ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደገን ስብሰባ ጠርተን በጣም በርከት ያሉ በቁጥርም፣ በስብጥርም በአመለካክከትም ከሁሉም በኩል ጋብዘን በመጀመሪያው ሳምንት ላይ በቁጥር ብዙ አልነበሩም 6ና 7 ነበሩ። በፌቡራሪ 2013 ዓ.ም. ለዚሁ ጉዳይ ስብሰባ ስንመጣ የአባላት ቁጥር ጭምሮ ከ17 – 18 እየሆነ መጣ። በጥሩ ሁኔታ በመቀጠል አሁን መደበኛ የሆነ ሰኞ ሰኞ ስብሰባ እናደርጋለን። ኮሚተውም በዚህ ተከታታይ ስብሰባ የራሱን መተዳደሪያ አወጣ። በንደዚህ እያልን ነው የቀጠልን ያለነው። ከዚያ በኋላ በተጓዳኝ የተሰሩ ብዙ ሥራዎች አሉ።

ሌላው ማህበሩ ያጋጠመው ችግር ብዙ ፕሮግራሞች ነበሩ በአሁኑ ጊዜ ተዘግተዋል። ይህ የታወቀ ነው። የተወስኑ ፈንዶች እንደገና ማግኘት እንድንችል ሲቲ ኦፍ ቶሮንቶ ሁለት ፈንዶች ለማግኘት፣ እንዲሁም በፌቡራሪ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. እና በፌቡረሪ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁ ፈንድ ለማግኘት ማመልከቻ አስገብተናል። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ ፌቡራሪ 19 ቀን 20113 ዓ.ም. ለኦንቶሪዮ መንግሥት ፈንድ ጥየቃ ማመልከቻ አስገብተናል። ለሰመር ወጣቶችን ለመቅጠር ማመልከቻ አስገብተን እንዲሁ እየተጠባበቅን እንገኛለን።

ሌላው ከዚህ በፊት ምን እንደሆነ ባላውቅም የፕሮፐርቲ ታክስ አለ። እኛ የምንከፍለው ከኪራይ ጋር ነው እሱ ተመላሽ ሊሆን ይችላል። ገንዘቡን በተመለከተ ለሲቲው ሌላ ማመልከቻ ጽፈን እየተጠባበቅን ነው።

ሌላው እንቅስቃሴ በትልቁ ፎረም ላይ ትኩረት እያደርግን ግን በተጓዳኝ መደረግ ያለባቸው ሥራዎች ስላሉ የክራይስስ ወይም የቤተሰብ ወይም የግለሰብ በአጠቃላይ የማህበሩ ቀውሶች በተመለከተ የሚቻለውን ያህል ድጋፍ ለመስጠት እየሞከርን እንገኛለን። ካውንስለር ሠራተኛ ስለሌለን የቦርዱና የኮሚቴው አባላት በማስተባበር የኢንተርቬሽን ሥራ በአይምሮ ሕመም ለሚቸገሩና የተለያየ ችግር ያለባቸውን ለመርዳት ጥረት እያደረግን እንገኛለን። የሠራተኛ ሃይል ስለሌለን በቦርድ ውስጥ የተሻለ ልምድና ቀረቤታ ያላቸውን ሰዎች ሌሎች የኮሚኒቲ አባላት አንድ ላይ በማድረግ እንደስፖርት ግሩፕ ለማድረግ እየሞከርንና እየሰራን እንገኛለን።

ሌላ በተጓዳኝ የሴቶችንና የልጆችን ጉዳይ በተመለከተ በችልድረን ኤይድ ሶሳይቲ ችግር ያለባቸው ቤተሰቦች በትምህርትም፣ ከቤትም ልጆቻቸው የተባረሩባቸውን ቤተሰቦች ለእነዚህን እርዳታ ለማድረግ ደብዳቤ ከመጻፍ ጀምሮ የፖለቲካ ስዎችን ጭምር በማናገር ምን ማድረግ አለብን የሚለውን ነገር ጥረት እየተደረገ ነው። በታላቅ ደረጃ በርከት ያሉ ዝግጅቶችን አሳልፈናል።

በአለፈው ኦክቶበር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የአድዋ በዓልን ከብላክ ሂስትሪ መንዝ ጋር አንድ ላይ በተጓዳኝ አክብረናል። በማርች 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያንና ካናዲያን ሂሪቴጅ መንዝ የቶሮንቶ ሜርና ካውንስለር የሰየመውን በደስታ በመቀበል ከቮሌንቲየር አፕርሼሽን ጋር በማጓደን በማርች 30 2013 ዓ.ም. አዘጋጅተን በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷልሌላው በርከት ያሉ ሥራዎች አሉ። ይኸውም ፓርትነር በተመለከተ ከሌሎች ተመሳሳይ ኮሚኒቲዮች ጋር አብሮ በመሥራት ሁለት ያህል ፕሮጄክቶች አሉን። አንደኛው ጤናማ የሆኑ ልጆችን ለማሳደግ በሚል ፓርትነር ሺፕ አለን። ከሌሎቻ አራት ድርጅቶች ጋር እያካሄድን እንገኛለን። ሥልጠና (ትሬኒግ) እየተሰጣቸው ነው። በዚህ ዎርክ ሾፕ ለሚሳተፉ ሰዎች ከዚህ በፊት የቆየ ሌላ ፓርትነር ሽፕ አለ። ማህበራትን ለማጠናከር ሲሆን እሱም ውስጥ እንዲሁ እንሳተፋለን ማለት ነው።በአሁኑ ጊዜ አምስት ሰራተኞች ሲኖሩን ሁለቱ ቋሚ ሲሆን ሦስቱ የፓርት ታይም ሰራተኞች ናቸው። ከማርች 31 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቀደም ሲል ሲጓተት በመጣው ችግር አንድ ፕሮግራም ተዘግቶብናል። ይህም NACP የሚል ነው። በፕሮግራም ደረጃ የምናካሂደው የሲኒየርስ ፕሮግራም፣ የኤች አይ ቪ ፕሮግራምና የፕሪቬንሽን ፕሮግራም ናቸው።ትዝታ፦ ያጋጠመዎት ችግር ካለ? ምንስ እርምጃ ተወአቶ ወሰንእንግዲህ ብዙ ችግሮች አሉብን። ከአለፈው የቀጠለ የማህበሩ ፋናንሽያል አቅም እየተዳከመ መምጣት ባለው ሁኔታ ላይ ጽ/በቱን በቀጣይነት ማስኬድ ሲሆን ከኪራይ ጀምሮ ሌሎች ተጓዳኝ የሆኑትን መሸፈን አንዱ ቻሌንጅ ነው። ይህ ክማህብሩ ከዚህ በፊት ከነበረው ተቀማጭ ገንዘብ እየተከፈለ ያለ ነው። ይህን ለመርዳት አንዳንድ ሃሳቦች በስራ ላይ ለማዋል እየተሞከረ ነው። ለምሳሌ የአባልነት ክፍያ ማስከፈል ይህ ወጪን እንዲሸፍን ወይም ለመቀነስ ይረዳል።
በቦርዱ ውስጥ የነበሩ ሶስት የክፍት ቦታዎች ኦክቶበር፣ ዲሲምበርና ጀነዋሪ በገዛ ፈቃዳቸው ስለለቀቁ በነዚያ ከፍት ቦታዎች ለመሙላት ጥረት አድርገናል። እነዚህ ሶስቱ የቦርድ አባላት ሊለቁ የቻሉት በቀላሉ በግል ምክንያት ባጭሩ ሊቀጥሉ ባለመቻላቸው ስለገለጹልን ነበር። ለምሳሌ ፕሬዘዳንቱ በፈቃዱ ከቦርድ አባልነት ሲወርድ ያን ቦታ ሊሸፍንና በቀጣይነት እንዲሄድ የሚያደርግ፣ እንዲሁም በሕዝብ ግንኙነት፣ በጸሐፊ የመሳሰሉት ይህ እራሱ እንደ ችግር ከታየ እራሱን ይቻለ ትግል ነው። ምን እርምጃ ተወስዷል ለሚለው እነዚህን ቦታዎ ለመሸፈንና እንዲቃለል ለማድረግ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት እርምጃ ተወስዷል ማለት ነው። ነገሩን በችግር መልክ አላየውም።
ዋና ኮር የሆኑ የማህበሩ ችግር ከዚህ በፊት እንደተገለፀው የማህበሩ አባላት መከፋፈል ነበረ ልበለው። ዛሬ ስናገር የተሻለ ሊሆን ይችላል። በተለያየ ጊዜ በነበረበት ስብሰባ ላይ ያለ መስማማት አንድ አንድ የምልህ ደስ የማይሉ ደረጃ ላይ እንደ ችግር ሆነው አሁን ያንን በማርገብ በመቀራረብ በመነጋገር አብሮ ለመሥራት ወደሚያስኬድ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ከፈንደር ወይም ከሌሎች እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ተቋማት አሁንም ቢሆን በቦርድ ደረጃ በመሃበር ደረጃ ያላንን ችሎታ የተሻለ ለማድረግ ችግሮችን መቅረፍ አለብን። በዚያም ሁኔታ ጥረቶችን እያደረግን ነው ያለነው።

እኔ እንደማየው የማህበረሰቡ ችግር መፍትሄ ለመስጠት እየተሞከረ ነው። ማህበርተኛው ከተቀራረበ አብሮ መሥራት ከቻለ ልዩነታችንንም አውቀን ከሄድን ችግርነቱ ቀርቶ መፍትሄ ይሆናል ማለት ነው።

ትዝታ፦
ባለፈው ቃለ መጠይቅ ሳደርግልዎ የማህበሩ አባላት ቁጥር 215 እንደደረስ አስረድተውኝ ነበረ; አሁን ይህ ቁጥር እንዴት ነው። “ይህን ጥያቄ ለመመለስ በጥናት መደገፍን ይጠይቃል” ብለው ነበር ። የተጀመር ጥናት ካለ ቢነግሩኝ?

አቶ ወሰን፦
215 አባላት ስንል አክቲቭ ማህበረትኛ አንዳንድ ወይም መደበኛ ክፍያቸውን በአለፉት አንድ አመት የከፈሉ እንደ ሪፈረንስ ልንወስደው የምንችልበት ሊኖር ይችላል። ክፍያቸውን አጠናቀው አክቲቭ የምንላቸው ናቸው። አክቲቭ ያልሆኑ ድግሞ ለምሳሌ ሁለት ወይም ሶስት አመት ሳይከፍሉ የቆዩ አሁን ባለው ሁኔታ ቁጥሩ ዝቅ ያለ ነው። አንድ በማህበሩ ውስጥ ያለው እንደችግር ያየነውና መከፋፈልን የፈጠረው በማህበሩ አባላት ላይ ጫና አድርጓል። አዲሱን የአባላት መዋጮ ጉዳይ ቦርዱ ስላወጣ በዚያ ላይም ጥያቄና ቅሬታም ያላቸው አባሎች ስለአሉ፣ የአባላቱ ቁጥር ከ215 አክቲቭ በሚለው ላይ ነው የሚገኘው። ከላይ እንደጠየከኝ ስለ ማህበሩ ቁጥር መቀንስ ወይም ባለበት መሄድ እስካሁን ያደረግነው ጥናት የለም።

ትዝታ፤-
ከላይ የተጠቀስውን ጥያቄ ስጠይቅዎ በአባላት መዋጮ ላይ ተጸእኖ እንደሚያመጣ ስለሚያስገነዝበን ነው። ስለሆነም በዲሴምበር ቃለ ምልልስ ሳደርግልዎ እንደጠቆሙኝ የአባላት መዋጮ በአዲስ መንገድ እንደሚጀመር ነው ይህ ምን ይህል ተግባራዊ ሆነ? ካልሆነስ ምን ሊደረግ ታስቧል? ይህ ትክክል አይደለም ብለው የሚከራከሩ አሉ። እርሶ ምን ይላሉ?

“በኖቬምበር 25 ቀን 2012 መደበኛ የቦርዱ ስብሰባ መተዳደሪያ ደንባችን አንቀጽ 14.7 ለቦረዱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የአባላት ወርሃዊ መዋጮ እንዲሻሻል ወስኖ ይህንንም የቦርዱ ውሳኔ ዲሴምበር 1/2012 በተጠራው የግማሽ ዓመት ጉባዔ ላይ ቀርቦ ማህበራችን የገጠመውን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ችግር ማገዝ እንዲያስችል ከጃንዋሪ 1 ቀን 2013 ጀምሮ የተሻሻለውወርሃዊ ክፍያ ተግባራዊ እንዲሆን አጽድቆታል።”

አቶ ወሰን፦
የአባላቱ ክፍያ ወይም አባላቱን ለመጨመር ጥረት መደረግ ያለበት በቦርዱ ውይይትና በአቅጣጫ ጠቋሚነት ጥናት መደረግ እንዳለበት ሃሳብ ቀርቧል። ጥናት መደረግ አለበት ያልኩት ባለፈው ቃለ መጠይቅ ላይ ያሉኩት በግምት ነው። በአብዛኛው ከ50 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አሉ ለምንድነው ከዚያን ያህል ኢትዮጵያውያን 215 ብቻ አባላት ያሉት ምንድን ነው ችግሩ መጠናት ነው ያልኩት። በበኩሌ ለምን እንዲህ ሆነ ተብሎ መጠናከርና ትኩረት መደረግ አለበት፤ አሁን ግን ለጊዜው ባሉት ማህበርተኞች ማለት ያለውም ማህበርተኛ እየቀነሰ በመሆኑ ለመጠናከር መጀመሪያ ግራውንድ መሠራት አለበት። ቢያንስ 300 አባላት እንኳን እንዲሆን ቁጭ ተብሎ ተወያይቶ ተነጋግሮ አብሮ ለመሥራት መቻል አለበን። እዚያ ላይ ነው ያለው ትኩረትና መሆን ያለበት። ነገር ግን በቀጣይነት ወደፊት ሁለት፣ ሦስትና አራት አመት ውስጥ ለዚህ ጉዳይ ጥናት መደረግ አለብት። ባለፈው ከነበረው ጥያቄ አንዱ ለሚቀጥለው አምስት አመት ማህበሩ የት ይደርሳል የሚል ነበር። አዎ ሥራው ከተሠራ መተባበር ካለ ሕብረት ካለን አብረን የምንሰራ ከሆነ በእርግጥ አንድ ሺህ ይደርሳል ብዬ አስባለሁ።

አሁን ባለንበት ሰዓት አንዳንድ የአባላት ቅሬታ ክፍያው ብዙ ነው። ክፍያውን ማህበሩ ይደግፋል፤ እየደገፈም የተሻለ አማራጮች አሉትየሚለውን በማየት ላይ ነው ያለነው። ስለዚህ ይህንን በቀጥታ ለመመለስ ውጤታማ አያደርገውም። ነገ ተነገ ወዲያ ምን ይሆናል ለሚለው ካለፈው ከጀንዋሪ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ አባልቻችንን ልከናል። አባሎቹ መረጃው አላቸው ብዙ ጊዜ በተለምዶ ክፍያ የሚጠናቀቀው ስብሰባ ሲጠራ ከዚያ 48 ሰዓት በፊት ነው። አሁን ትኩረት አድርገን ሰዎች እንዲከፍሉ ማህበርተኛ እንዲሆኑ ግፊት ያደረግነው ነገር የለም፤ ነገር ግን በኮሚኒቲው ፎረም ሂደቱን በሚያዘጋጁት ጋር ይህ እራሱ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ችግር ሊያመጣ ሰለሚችል በሚለው ላይ ባለንበ ሰዓት ነው። ይህ ጥያቄ የመጣው ተገቢ የሆነውን መልስ ለማግኘት ምናልባት ከዚህ በላይ የጠቀስኩት ቢደረግ ይሻላል በሚል ነው።

ከጀነዋሪ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ይህን አዲሱን የአባአት ወረሃዊ መዋጮ ተግባራዊ አድርገነዋል። በሂደት ግን ጥቆማዎች፣ ቅሬታዎች ስላሉ ነገሩን በአፋጣኝ ግፊት አላደረግነውም አና አሁን ያለው ሁኔታ ከአባላቱ ከኮሚኒቲው ፊድ ባክ ነው። ጥቆማዎች የማግኘት ነው፣ በይበልጥ ለመቀጠል አሁን ያለንበትን ሁኔታም መገንዘብ ያስፈልጋል።

ትዝታ፦
አንድ አንድ ግለሰቦች ሃሳባቸውን እንደሚገለጹት በአንቀጽ 2 በቁጥር 2.1 ላይ በመተዳደሪያ ደንቡ የተገለጸው ተግባራዊ አይደለም። የኢትዮጵያ ማህበር እንዲህ ሊከፋፈል እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ የቻለው የተለያዩ ቡድኖች ተጽእኖ በማድረግ ነው ይላሉ። እርስዎ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለዎ?

ኣቶ ወሰን፦
በዚህ ሁኔታ ግልጽ ያልሆነ ነገር አለ ማለትም አንዳአንድ ጊዜ በመተዳደሪያው ደንብ (በኮንስቲቱሽኑ) አማካይነት አባላቱ በሙሉ መምረጥ መመረጥ በሚቻልበት ሰዓት፣ በተደጋጋሚ እንደልምድ ካለፈው ተጋቦሽ ወይም በትራዲሽን በመጣው ሁኔታ አንድ አንዴ የመተዳደሪያ ደንቡን ሊጋፋ ይቻላል፣ ግን ላለፉት ዓመታት ካለፈው እንደልምድ ወይም ትራዲሽን ሆኖ የመጣው ነገር አለ፣ በዚያ ሁኔታ የቦርድ አባል ሆነው ይገባሉ፣ ሃላፊነት ይወስዳሉ። በዚያ ጊዜ መሆን ያለበት ሁላችንም የምንስማማበት እኔም የማምነው የግል ፖለቲካ ወይንም ሌሎች እምነቶች የአጀንዳ ቆባቸውን አስቀምጠው በመሓበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት መስራት ነው። ይህን ማድረግ የሚችለው እያንዳንዱ የቦርድ አባል መሆን አለበት። በግሩፕ ወይም በሌላ ሁኔታ ሲመጣ ይሰማል፣ ይታወቃል። ለምሳሌ ኤጂ ኤም ላይ በግልጽ የሆነ ክፍፍል ይታይ ነበር። እከሌ የዚህ ፖለቲካ አባል ነው፣ ናት ማለት ባይቻልም ዋና ዋና ማለት ሜጀር የሆኑ ክፍፍሎች ይታዩ ነበር። ያለ መተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለቦርድ አባልነት ሲመረጥና ሲገባ አንድ ቃለ ማህላ የሚሰጠው ከፖለቲካ አመለካከቱ በእምነት አመለክካከቱ ጫና ሳያደርግ ተገቢ (ፌር) በሆነ መንገድ ማህበሩን ሲረዳ ነው። አና አሁን ባለኝ አላፊነት እንደፕሬዘዳትነት ይሄን ነገር እንዲጠበቅ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ሗላ አልልም ማድረግም አለብኝ። በኔ በኩል እየአንዳንዱ የቦርድ አባል ሃላፊነት አለበት፣ አንድ አንድ ስሜቶች ሊታዩ ይችላሉ የለም አለ ለማለት አልችልም።

በኖቬምበር 2012 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ ላይ 13 አባላት በድምፅ ብልጫ ተመርጠው የቦርድ አባል ሆኑ። ይህንን ስራዬ ብሎ የሚከታተለው ያውቀዋል። ከዚያ በኋላ በዲሴምበር 5 ቀን 2012 ዓ.ም. በተደረገው ኮሚቲ ምደባ በዚያ በተወሰኑ ቅሬታዎች ምክንያት አምስት የቦርድ አባላት ሪዛይን አድረገዋል ወይም ከቦርድ አባልነት በፈቃዳቸው ተገልለዋል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ሜይ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በ 8 ቦርድ አባላት ሲስተናገድ ቆየ። በዚያን ጊዜ የመተዳደሪያ ድንቡን መሠረት ትክክል ነበር። አራትና ከአራት በላይ ስብሰባ ተጠርቶ መሟላት አለበት ያ ተደርጎ ፌቡሩዋሪ ላይ ስብሰባ ተጠርቶ አልሆነም። እንደገና ወደ ሜይ ሄደ። አዎ ችግር አለ ኮንስቲቲሽናል አይደለም፤ እንደገና ወደ ሜይ ሄደ በአንድ ወር ጊዜ ስብሰባ መጠራት አለበት የሚል ነበር። ይህ ነገር እልባት ያገኘ ነበር። በማህበረስብ ውስጥ ያለውን ኮንፊውዥን ብዥታ ጠፈቶ እልባት አግኝቷል። አንድ ሁኔታ እኔ መተዳደሪያ ደንቡን ወይም ኮንስቲቲሽን የማስጠበቅ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ በአንዳንድ ሁኔታ ሁልግዜ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። አለማወቅ ሊሆን ይችላል። ስህተትም ሊሆን ይችላል። ለዚህ ሃላፊነት መውሰድ አለብን። እንወስዳልንም። በተደረጉ ስህተት ላይ በውጭ ደግሞ ያሉ የኮሚኒቲ ክሪትካል በጣም አስቸጋር አድርጎ ማስቀመጥ ከኮሚኒቲው ጋር ሊጋጭ ይችላል። ያንን ደግሞ በምተማመን መቻቻል ነው። ወይም ሰፋ ያለ ሰዓት ወስዶ የመማማሪያ፣ በኮንስቲቲሹናል በማተኮር መቻቻል አለብን። የህ ከስህተት ተነስተን ማለት ነው። አንድ ምሳሌ መስጠት የምችለው ብዙ ጊዜ የቦርድ አባላት ውስጥ መግባት ወም መመረጥ የሚችሉት ለአንድ አመት በአባልነት ቀደም ሲል የቆዩ በ48 ሰዓት ውስጥ ክፍያቸውን ያጠናቀቁ የሚል አለ። ብዙ ጊዜ ያንን አናይም። በተለያየ ምክንያት ማህበሩን ብቻ አስቀድሞ ትልቁ አሰራራችን እንደ ትራዲሽን ስለሆነ ለምሳሌ አንድ ስብሰባ በጎደሉ አባላት ላይ አምስት ሰዎች እንዲሟሉ ሲደረግ ሂደቱ ጥሩ አልነበረም። የተወሰኑ አባላት ስብሰባውን ትተው የወጡበት ያ እራሱ ማህበሩን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተበት ጊዜ ነበር። በዚያ ሁኔታ ማህበሩ የመኖሩና ያለመኖሩ ጥያቄ ነበረበት። የምርጫው ሂደት በድምጽ መስጠት ነበር። ትክክል ያልሆነ ነበረ። ዋናው መሆን የነበረብት ግንቦት 27 ከዚያ ስብሰባ ስንወጣ የተሟላ የቦርድ አባል መሆን የነበረበት ካልሆነ ማህበሩ ችግር ነበረበት። ከፈንደሮች ከመተዳደሪያ ደንብ ወይም ኮንስትትሽን አንጻር እንደገና አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ብዙ ጊዜ ትክክለኛ ባልሆነ ሂደት ይሁን የሚል ሁኔታ ይፈጠራል ወይም በተቃራኒው ይህን ተምረን በጋራ ማስተካከል የምንችልበትን መፍጠር አለብን። ባጭሩ ለመመለስ ኮንስቲቲሽኑ ይጠበቃል ውይም ለመጠብቅ በጋር ካለው አውነታ ለምስንገንዘብ ጥረት ይደረጋል። የኔ ሃላፊንት ግን ችግሮች ስህተቶች ይፈጠራሉ ሃላፊነት መውሰድ ካለበት ይወሰዳል ማለት ነው።

ትዝታ፦
ባለፈው ቃለ መጠይቅ ላይ በኢትዮጵያ ማህበር ፎረም እንደተቋቋመና ስራውንም እንደጀመረ ጠቀስ አድርገውልኝ ነበር? ለዚህ ጥቂት ጥያቄዎች ይኖሩኛል።
ሀ) የኢትዮጵያ ማህበር መተዳደሪያ ደንብና ከፎረሙ ሃሳቦች ማንኛው ተፈጻሚነት አለው?
ለ) ፎረሙ እስከአሁን ድረስ ለመሃበሩ ችግር ማቃለያ የሚሆን ምን አከናውንውኗል?
ሐ) ፎረሙ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች ሃሳቦች ፈቃደኛና ዝግጅዎች ናቸውን?

አቶ ወስን፦
ሀ) ይህ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያ ማህበርን ተገዢ ወይም ጎቨርን የሚያደርገው መተዳደሪያ ደንቡ ወይም ኮንስቲቲሽኑ ነው። ፎረሙ በኮንስቲቲሽኑ ሥር ሆኖ የማያሳውቅ አሁን ያሉ ችግሮችን ሁኔታውን አገናዝቦ መፍትሄና ጠቋሚ ሃሳብ የሚሰጥ የተከፋፈለውና የራቀውን አባልት አሰባስቦ አንድ አድርጎ በጋራ ነጥቦች ላይ የሚያወያይ ህብረትና አንድነትን ሊፈጥር የሚችል ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ ጥቆማዎችን አቅጣጫዎችን ሁሉን አባላትን ከተቀበሏቸው በኋላ ኮንስትቲሽኑ በሚፈቅደው መሠረት ተግባራዊ ይሆናል። ስለዚህ ፎረሙ የሚሰራው ብመተዳደሪያ ድንቡ ተገዢ ስለሆነ ፎረሙ ማንኛውም ውሳኔ ተፈፃሚነት አለው።
ለ) ፎረሙ ማደራጀት ስንጀምር መቼ ወም እንዴት ይሁን፣ ምን አይነት ሃሳቦች እናካት፣ ምን ያህል ሰው እንጥራ፣ ይህን የመሰለ ተግባራዊ ይሆኑ ነገሮችን ከማለት ባሻገር ትልቁ ፎረም የተስተካከል የሚሆነው የተለያየ ሃሳብ ያላቸውን አባላት መሳብ መቻል አለብን። እንዘያን ሃሳቦች ሊይዙ ወይም ሊያንፀባርቁ የሚችሉ ሰዎችን መያዝ አለብን፣ ከወዲሁ ሞዴል አድርገን ማሰብ መቻል አለብን። እንደአባል ኮሚቴው መሰባጠር አለበት። ከአንድ አይነት አመለካከት ከፖለቲካ ከሃይማኖት የተከፋፈለ ነው የሚለውን ያን አስተሳሰብ ሰርዞ መሆን እንዲችል የሁሉም ድምፅ መሰማት የሚችልበት ስብስብ እንዲሆን ማለት ነው።

የፎረሙ ክርይተሪያ እንደ መመዘኛ ያየነው 1ኛ/ በተለያየ ደረጃ ቀደም ሲል በቦርድ ውስጥ ገብተው ከጅምሩ ጀምረው ለረዢም ጊዜ ያገለገሉና ስለ ማህበሩ ታሪካዊ ሂደት ግንዛቤ ያላቸውን ሰዎች 2ኛ/ ቀጥሎ የወጣቶችን ድምፅ ቀጣዩን ጀነሬሽን ከኮሚኒቲው ጋር ብዙ የማይገናኙትን ድምፆች ይዞ ሊመጣ የሚችል 3ኛ/ሞር እንዲፔንደት የሆነ ራቅ ብሎ ማህበሩን በቦርድነት ያልገቡና ያልተሳተፍ ግን የራሳቸው አመለካከት ሊኖራቸው የሚችሉ ሰዎችን ስለማህበሩ የተለያዩ ሰዎችን ብናመጣ ሞር ተፈፃሚ የሆነ አቅጣቻ መፍጠር እንችላለን በሚል ሁኔታ ነው።

የፎረሙ ብዛት በቁጥር 18 እስከ 20 አባላት ያሉበት ሲሆን በአዘቦት ቀን ደግሞ ክ12 እስከ 13 አባላት ይገኛሉ። ያለው ስሜት ያለው መቀራረብ በጥሩ ሁኔታ እንደሆነ ነው።

ሐ) በማንኛውም ሰዓት ሰኞ እስከ ሜይ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚያ በኋላ ደግሞ የፎረሙን ግኝት በሪፖርትና በዶኩመንት አቀዳጅቶ ፋይናላይዝድ ወይም የመጨርሽ ይሆናል። ዶክመንቴሽን ለማድረግ ቀጣይ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። ከዚያ በኋላ ድግሞ እነዚህ አቅጣጫ ጠቋሚዮችን፣ ሃሳቦችን መትገበር ውስጥ ስለምንገባ በማንኛውም ሰዓት ማንም ኢትዮጵያዊ መጥቶ መሳተፍ የሚችልበት ሁኔታ ነው ያለው፣ እዚህ ላይ ግልጽ ላደርግልህ የምፈልገው የማህበሩ አባላትን ብቻ አይደለም “ኢትዮጵያውንን ሁሉ” ነው ይዘን ጉዞ መቀጠል ያለብን ምክንያቱም አባላት መሆን ያለመሆን ካሉት ችግሮች ጋር የተዛመደ በመሆኑ ችግሮችን ስንፈታ ሁሉም ወደ ተሻለ አባልነት ይሳተፋል ብለን ስለምናምን ነው። እንደ ቦርድ እንደ ኢትዮጵያ ማህበር ከቦርዱም በላይ ባለው ሜምበርሺፕ ቀጥሎም እንደ ኮሚኒቲ ማለት ነው። ደረጃዎችን ስናይ አሁን ይህን መሃበር ከብዙ አጥብቂኝና ከብዙ ችግሮች ሊወጣ የሚችለው ብቸኛ አማራጭ በእኔ እምነት በጣም ግልጽነትና ሁሉንም ነገር በቀናነት በማየት ነው። ችግሮች ይኖራሉ በዚያ ሂደት ውስጥ መፍትሄ እየሰጠን መጓዝ የምንችልበትን ሁኔታ መፍጠር ነው። ወደ ኋላ ምን ያህል መሄድ እንደማይቻል አይተንዋል። ስለሆነም 90% ወደ ኋላ ሄደናል። ለእኔ ብቸኛ አማራጭ 100%ና 200% ደብል ትሪፕ እያደረግን መሄድ ነው። ያን ለማድርግ ደግሞ ፈቃደኝነቱ በቦርዱም በእኔም ባለኝ ሃላፊነት ሙሉ በሙሉ አለ። እኔ የምጠራው የኮሚኒቲውን አባል በቦርዱ ስም ሆኜ ከማራቅ ተገናኝተን ወደ መፍጥሄ ሃሳብ ብንሄድና ብንነጋገር ባለፈው ይነበሩትን ችግሮች የምንወጣው በጋራ በሰላም ስንነጋገር ነው።

ትዝታ፦
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ማህበር ስንት ሕጋዊ የቦርድ አባላት አሉት። አንድ አንድ ግለሰቦች ለዚህ ጥያቂያቸውን ሲሰሙ ይታያሉ። ስለዚህ አስተያየትዎን ቢያካፍሉን?

አቶ ወሰን፦
አጭር መልስ የኢትዮጵያ ማህበር ቦርዱ ሕጋዊ ነው። ሕጋዊ ነው የምለው ይህን ማህበር ወደ ተሻለ ቅድም እንዳልኩህ አንዳንድ ጉዳዮች እስከችግራቸው እነዚህ ሰዎች ሜይ 17 ከውጪ መጥተው አይደለም የቦርድ አባል የሆኑት በአጋጣሚ ሆኖ ሂደቱ ጥሩ አልነበረም ስልህ ስብሰባው አባላቱ ቢሟላም ሰዓቱ እየመሸ ሲሄድ ሜክ ኢት ወይም ብሬኪት የሆነበት ጊዜ ነበር። የሂደቱ ግድፈት ችግር ሊኖር ይችላል። ለውጤቱ እዚያው ካሉ አባላት ውስጥ ተጠቁመው ግን እያንዳንዱ አባላት ድምፅ አልሰጠም ማለት በምርጫ ሳጥን ውስጥ አይደለም የተመረጠው ነገር ግን በቆጠራና በሆታን ጭብጨባ ሲሆን አባል የሆኑ ናቸው። በምርጫ ሳጥን ድምጽ ቢሰጥ ኖሮ በጣም ጥሩ ይሆን ነበር። ብዙውን ጊዜ የግምት ስራ ይሆናል። ሕጋዊ ነው፣ ሕጋዊ አይደልም እዚያ ውስጥ ብዙ መግባትም አልችልም። የሕዝብ ጥያቄ ነው። አውቃለሁ! ሰምቻለሁ! ይህን ጥያቄ እንዲያውም እላይ ተጠይቋል። ስለዚህ ጉዳይ ስለ ማህበሩ አደረጃጀት ፎረሙ በጣም ትልቅ ሥራ እየሰራ ነው። የሚዲዬሽን ግሩፕ ቀደም ብሎ ቅሬታ ከነበረባቸው ግሩፖች ጋራ በተናጠል አናግሮ በተመሳሳይ የቦርድ አባላት ጋራ በተናጠል አናግሮ በመጨርሻ በጋራ አነጋግሮ አንድ የሆነ መፍተሄ ደርሷል። አንተ እንደጠየቅኸኝ ማለት ዛሬ ኤፕሪል 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ያለው ሁኔታ የመቀራረብ አብሮ የመስራት ሁኔታ ከፍተኛ እየሆነ ነው ያለው። እነዚህን ሁኔታ ሁሉም ገታ አድርጎ የፎረሙ ሕጋዊ የሆኑ ነገሮችን አቅጣጫ አስይዞ ስህተቶች እንዳይደገሙ የሚሆንበት መንገድ መፍጠር ነው። ያለው ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው።

ከሚዲያሺን ኮሚቲ ሌሎቹ አራቱ የፎረም አወቃቀር ሁኔታ መጥቀስ ከቻልኩ
1ኛ/ የአኮሚዲሽንና ሆስፒታሊቲ የሚል ነው።
የፎረሙን ቦታ የሚያዘጋጅ በእለቱ ተግባራዊ የሚሆንትን ነገሮች እንድ ምግብ፣ መዝናኛ የመሳሰሉትን መስተንግዶ የሚያደርግ ነው።
2ኛው ግሩፕ ፕሮሞሽንና ፓብሊኬሽን ነው። ይኸኛው ፕሮሞት የሚያደርግ ግሩፕ ሲሆን ለምሳሌ ፍላየር፣ ፖስተር ጋዜጣዊ መገለጫ እያወጣ ሕዝቡ እንዲያውቀው የማያደረግ ሰሞኑን ጀምሮ የምንሰራበት ነገር ነው።
3ኛው ፕሬዘንቴሽንና ዶክመንቴሽን ነው። ቢሚቀጥለው የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ለምሳሌ በእለቱ ሦስት ዋና ዋና አርእስቶች ላይ የሚያቀርቡ አሉ።
ሀ) በይበልጥ የኢትዮጵያ ማህበር በ30 ዓመታት ምን ይመስላል የሚል ነው።
ለ) አሁን ማህበሩ የሚገኝበትን ሁኔታ ጥንካሬውን ድክመቱን ውጤቱን አንዳንድ በተለይ ወደፊት ከሚደረገው እንዴት ይታያል ከሚለው አንፃር ነው።
ሐ) በአጠቃላይ ይሄ ማህበር ከዬት ወዴት ይሄዳል በሚል በመገምገም ሊያሳይ የሚችል ነው። ከአራት እስከ ስድስት የሚሆኑ ወጣት አባላትን ከሴቶች፣ ከአዛውንቶች ያካተተ ውይይት የሚካሄድበት ነው። በነዚህ ሁኔታ የሚያዘጋጅ ግሩፕ አለን። እነዚህን ደግሞ ሪፖርት አድርጎ ጽፎ ዶክመንት አድርጎ አዎንታዊ ውጤታም አድርጎ የሚያቀርብ አንድ ግሩፕ አለ።

4ኛ/ ባጀትና ፈንድ ሬዚንግ ነው።
ይህንን የፎረሙን ወጪ እራሱ መፈፀም አለበት። ማህበሩ ምንም ሪሶርስና አቅም ስለሌለው የራሱን ፈንድ ሬዚንግ እያደረገ ነው ያለው። ምን አልባት ጥሩ ኢንፎርሜሽን ፌቡሩዋር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. አንድ ጌት ቱጌዘር አድርጓል። በፎረሙ አዘጋጅና በማህበሩ ዙሪያ የተለያየ ሀለፊነይ ወስደው የሚሰሩ ሰዎቹ የበለጠ እንዲቀራረቡና አብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ፈንድ ሬዚንግ ብሉር ላይ ባለው ላሊበላ ሬስቶራንት ተደርጓል። ሌላም የፈንድ ሬዚንግ ፕላኖች አሉ ስለዚህ በዚህ ደረጃ ላይ ነው ያለው ማለት ንው።

ስለፎረሙ አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። ፌቡራሪ 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በወጣው ትዝታ ጋዜጣ ላይ ከአባላት አንድ የተጻፈ አርቲክል አለ። ሌላው ላይ ብዙ ማለት አልፈልግም። ስለ ፎረሙ ስለተነሳ ከየት ወደየት እየሄድን ነው የሚለው ፓርት ለትዝታ አንባቢዮች ትንሽ እንትን እንዳይል ነው። “ባለፈው በዲሴምበር አካባቢ ለይስሙላህ ያህል አንድ ስብሰባ ተጠሮ ነበር ይባላል። ፎረሙ በሳል የሆኑትን የቦርድ አባላትን በማግለል ትልቁን የጥፋት አሻራ ያሳረፉትንና መምራት ያልቻሉትንና ለማህበሩ መፍትሄ የማያመጡትን ሁሉ ሳይቀር የማህበሩ አባል ያልሆኑትን ሁሉ ያካትታልና በማህበሩ ውስጥ ከልባቸው ያልሆኑትንና መፍትሄ ያመጣሉ ተብለው የተገመቱትን ሰብስበው እንደነበረ ከዚያው ወሬ የነፈሰው ወሬ ተስምተዋል” ይላል። ስለ ፎረሙ ብዙ ለመግልጽ ሞክሪያለሁ ምን ያህል የይስሙላ ወይም ብዙ ኮሜንት ባደርግ ባልፈልግም የላቀና በሁለት ሦስት ኮሚቴ ውስጥ ከምናደርገው የበለጠ ነው። ምናልባት ፎረሙ ኮሚቴ ውስጥ የሚሰሩትን ብታነጋግር ብትችል የበለጠ አሁን ምን ተሰርቶ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አሁን ካነበብኩልህ ጋር ምን ያህል የላቀ ሥራ እንደተሰራ መረዳት ትችላለህ እና ይህንን በዚህ ልተወው።

ጠቅለል ባለ ሁኔታ የፎረሙ አደረጃጀት ከሚያዋቅሩት ሰዎችን ከመጋበዝ ጀምሮ በፎረሙ እለት በሚዘጋጁ ፕሬዘንቲሽኖች በተለያዩ ኮሚቲ ውስጥ ያሉትን የተራራቁ ስዎችን በማቀራረብ የኮሚቲ አባላት ጨምሮ ሌላ ስሜት ያላቸውን ሁሉ ነው እያሰባሰብና እየሰራ ያለውና ቅሬታም ጥያቄም ሁሉ ያላቸውን ለመቅረፍ ይሞክራል። በቀጣይ ስብሰባ አድርጎ አንተ እንዳስቀመጥከው የቦርድ አባላትና ከቦርድ ውጭ ያሉትን አንድ ላይ በመሆን ጥሩ የመግባባት የጥያቄና የመልስ የመረዳዳት ነበር። ነገር ግን ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሂደት ቀስ እያሉ ገንቢ በሆነ መልኩ እየታየ መሆኑ አለበት እንጂ እንደ ማያዣ ማየት እንደሌለብን፣ ተግባብተናል። ፎረሙ ውጤታማ ከሆነ ቀድም እንዳልኩት በሚቀጥሉት ሁልት፣ ሶስትና አራት ሳምንታት በምናደርገው ሥራ በርከት ያሉ ሰዎችን እንጋብዛለን። በዚህ አጋጣሚ ማለት የምፈልገው ስለፎረሙ ጥያቄ ካለ በስልክም፣ በእሜልም በመልክትም መጠየቅ ይቻላል። ተጨማሪ ጥያቄም ካለ ፌስ ቡክ እየከፈትን ነው፣ ፖስተሮች ይወጣሉ፣ በቀጣይነት ደግሞ ፕሬስ ሪሊዝ በትዝታ ጋዜጣ ላይ ይወጣል ግንኙነት ይቀጥላል። እስካሁን የመቀራረብ ስራ ጨምሮ ብዙ የተንጠለጠሉ ሥራዎችን ነው እያከናወን ያለነው። አሁን በአንድ ድምጽ መለእክት በማስተላለፍ ደረጃ ላይ ነው ያለነው። በእኔ እምነት ከአሁን በኋላ የተሻለ መተማመን ይኖረናል ብዬ ነው የምለው።

ትዝታ፦
ባለፈው ስሞን ኤፕሪል 13 ቀን 2013 ዓ.ም. እርሶ በተገኙበት ስብሰባ ተደርጎ ነበር። ይህ ምንን በተመለከተ ነበር? ከማንስ ጋር ነበር በአጭሩ ቢያስረዱን?

አቶ ወሰን፦
የፎረሙ ኦርጋናይዚንግ ኮሚቴው ኖቬምበር 23 ጀምሮ ሥራውን ሲስራ ቅድም እንዳልኩት 17 እና 18 አባላትን ይዞ እየትጓዘ ነው ያለው። አምስት የፎረሙ ዎርኪንግ ግሩፖች አሉ። ከዚያ ውስጥ አንዱ የሚዲዬሽን ግሩፕ አለ። የተቋቋመበት ምክንያት ፎረሙ ውጤታማ ስራ ሊሰራ የሚችለው እንዲሁ የሚያቀራርቡና እንዲሁም በአንድ ቅሬታ ከማህበሩ ራቅ ያሉና የተገለሉ ሰዎችን መሳብ መቻል አለበት።

6ቱ አባላት አንድ ላይ ሆነው በማህበሩ ላይ ቅሬታ አለን በሚሉ በጽሑፍ ለማህበሩ አቅርበው ነበር። ያንን በተመለከተ እነዚህ ስድስት አባላት ለማነጋገር ቀጥሎም ግራና ቀኝ በማየት ቅዳሜ እለት ኤፕሪል 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ስድስቱ የፎረሙ የሚዲዬሽን አባላት ቀደም ሲል 6 ቅሬታ አለን ከሚሉ አባላት ጥያቄ ያቀረቡ፣ በተጨማሪ በኦገስት ለማህበሩ በሕግ ባለሙያ የተደገፈ ደብዳቤ ለማህበር ካስገቡት ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በቦርዱም በኩል በስድስቱም ቅሬታ አቅራቢ በኩል በሚዲየሽን ኮሚቲው አስማሚነት ጥሩ የማቀራርብ ውይይት ተደርጎ ነበር። አንድ ውይይት ብቻ አልነበረም ሁለት ጊዜ የሚዲያሽን ኮሚት ከስድስቱ ቅሬታ ካላቸው አባላት ጋር ተገናኝተዋል ከቦርዱ ጋርም እንዲሁ። ስለሆነም ቅዳሜ ኤፕሪል 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በጣም ጥሩ ደስ የሚል ከስህተት ለመማር የማይስችል ውይይት ተደርጓል።

በዚያን ቀን የተጠየቁት ዋና ዋና ጥያቄዎች
1ኛ/የሕንፃ ፈንድ የሚል ሲሆን ማህበሩ የራሱን ሕንጻ ለመግዛት የተቀመጠ ያለፉት ዓመታት ገንዘብ ነበር ታዲያ ይሄ እንዴት ነው የሚገኘው የሚል ነበር። ይህ ተገቢ ጥያቄ ነበር። እሱን ያው በደንብ አስረድተናል። ገንዘቡ በምንም ሁኔታ እንዳልተነካና እንደማይነካ፣ ገንዘቡን ማሳደግ እንጂ በምንም መልክ የምንነካበት መንገድ የለም። ሌላ ሪዘርቭ አለን ከሪዘርቩ ነው እስከአሁን የምንጠቀመው፣ ይሄን ደግሞ ልንነጋገርበት የምንችለው ኤ.ጂ.ኤሙ ባለበት ነው በማለት ለማሰመን ሞክረናል። በመልሱም ረክተዋል።

2ኛ/ ይህ የኮሚቲ ፎረም ሜይ 18 የሚካሄደውን የሚሰጣቸውን ሪኮማንዴሽኖች አንተም ቅድም ጠይቀህኛል ቦርዱ ለመቀበልና ይዞ ለመሄድ ምን ያህል ፈቃደኛ ነው? ቅድም እንደገለጽኩልህ 101% ቦርዱ ፈቃደኛ ነው ይህንን ተግባራዊ የምናደርገው ቅድም አንተ በአግባቡ እንደጠየከኝ የማህበሩን አቅም አገናዝቦ የሚሄድ ሥራ ነው፣ ግን በጽንሰ ሃሰአቡ ደረጃ ፌቃደኛ ሆነን እንቀበለዋለን። ለዚህም ነው በሚዲሽን ኮሚቲ አመራር ሰጪነት በቦርዱና በስድስቱ ቡድኖች ጋር ውይይት ማድርግ የተስማማነው።

የማህበርተኛ ክፍያ በተመለከተ ቅድም እንደገለጽኩልህ ከጀንዋሪ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምረን ተግባራዊ ነው ብለን ወስነናል። አሁን ግን ቅሬታዎችም ጥያቄውችም ስለ አሉ ማስተናገድም ግዴታ ነው። ከዚህ በኋላ ቦርዱ እየተነጋገረ በተለይም ከሜይ 18 በፊት አንድ እልባት ሰጥተነው እንደማነቆ ችግር እንዳይሆን እየሰራን ነው ያለነው።

እነዚ 6 ቅሬታ አቀረቡ የተባሉት ሰዎች ፎረሙ ውስጥ 100% ሊሳተፉ ይችላሉ። መቼ እንደምንገናኝ ምን እንደምናደርግ በግልጽ ነገርናቸዋል። በማንኛውም ቦታ ገብተው እንዲሳተፉ ጥሪ አድርገናል። በተጨማሪ አብረው የሚሰሩትን ኤፕሪል 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በምናደገው ጌት ቱጌዘር ጥሪ አድርገንላቸዋል።

በቦርዱና በ6ቱ ቅሬታ ያላቸው ሰዎች ጋር አስታራቂ ኮሚቲ ወይም የሚዲየት ኮሚቴው ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል እነርሱም፦
1ኛ/ ሊቅ ካህናት ምሳሌ እንግዳ የሚዲያሽኑ ኮሚቲ ስብሳቢና የፎረሙ አባል ናቸው
2ኛ/ ዶ/ር ቡሻ ታአ
3ኛ/ አቶ ባዩ
4ኛ/ ወ/ሮ ፋናዬ
5ኛ/ወ/ሮ ማለዳ እንዚህ ነበሩ።
የሚዲዬሽን ኮሚቲ ተጠሪነቱ ለፎረሙ ሰብሳቢ ሲሆን የፎሬሙ ተጠሪነት ለቦርዱ ነው። ፕሬዘዳንቱ በምርጫ ፎርሙን ቸር የሚያደርግ ሲሆን ተጠሪነቱ ለቦርዱ ነው።

ትዝታ፦
የወደፊት የኢትዮጵያ ማህበር ራእይ ምን ይመስላል?

አቶ ወስን፦
በራእይ ደረጃ እንደትልቅ ማናቆ ይታይ የነበረውን ችግር በብዙ ሰዎች ከፍተኛ ጥረት እዚህ ሲደርስ አሁን ዛሬ ስናወራ ጥሩ መንፈስና መቀራርብ እንዳለ የተራራቁ ሁኔታዎች ሁሉ መፍትሄ እንዳገኙና ኮሚኒትው ፎረሙ በጣም ውጤታማ በመሆኖ በቁጥር፣ በስብጥርና በተለያዩ አመለካከት ያላቸው ማህበሩ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚሉ ሰዎች ሁሉ አቅፎ አወያይቶ የጋራ የሆነ ጠቋሚ መስመሮችን አሲዞ ከሄድ ውጤታማ ነው እንላለን።

የቅርብ ራእዩ ሜይ 18 2013 ዓ.ም. የሚደረገው ነው። ከዚያ ቀጥሎ አሁንም የሰራንባቸው ያሉትን ውጤታማ የሚያደርግ ነው። ሪኮማንዴሽን ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ለምሳሌ የማህበሩ የራሱ የሆነ ሕንፃ እንዲኖረው መተግበር የሚለውን ቦርዱ ከዚህ በፊት ያሉ ቦርዶች እንዳደርጉት አንድ አመት አክሽን ፎከስ እንዲሆን እንፈልጋለን እናስባለን ሳይሆን እናደርጋለን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማህበሩ የራሱ ሕንጻ እንዲኖረው እናደርጋለን። ቅድም እንዳልኩት የቤት ኪራይ ወጫችን ከአቅም በላይ ነው። ስለዚህ ራእይ አንበለው አክሽን ፕላን ማህበሩ የራሱ ሕንጻ እዲኖነረው ነው።

ሁለተኛው የሰራተኛና የሪሶርስ ችግር ሲሆን ሌሎች ብዙ በርካታ ችግሮች ቅድም እንዳልኩህ የክራይስስ፣ የእናቶች፣ የሴቶች፣ የልጆች ብዙ ችግሮችን እንሰማለን፣ ወደ እኛም ይመጣሉ ይህን በተቻለ መጠን መልስ ሊሰጥ የሚችል ከኮሚኒቲው የተወጣጣ የበጎ ፈቃደኛ፣ በገንዘብም ሁኔታ ሆነ ከሌላም በሂደትም በካናዳ በሦስቱም መንግሥት ያሉት ፈንድ የሚገኝበትን አፕላይ እያደረግን በፕሮግራም የማህበሩ አባላት ጥሩ አገልግሎትን የሚገኙብት ለማመቻቸት።

ሌላው ትልቁ እራይ ደግሞ የሚቀጥለው ጀነሬሽን ወጣቱ ተስትፎ አድርጎ በዚህ ኮሚቲ ውስጥ ያገባኛል የእኔ ነው የሚል ስሜት ኖሮበት ተሳትፎ የሚያደርግበትን መንገድ መክፈት በራሱ መመራት የሚችል ሪሶርሶች እንዳይጎተቱብን በቂ የተገነባ ኮሚኒቲ መፍጠር መቻል ይህም ቢሆን ራእይ ነው። በዚህ መልክ አይዋለሁ።

ከሁሉ በላይ ደግሞ ከአለፉት አመታት ሳንውቃቀስ ስህተቶች ተፈጥረው በሞኝነት ከመጠፋፋት ይልቅ በመቀራረብና በመወያየት መፍትሄ መስጠት አለብን። 50ሺህ ኢትዮጵያዊ በቁጥር ትልቅ ነው። ልንሠራ እንችላለን። ራእይ ባልለውም አክሽንና ፎከስ ናቸው እላለሁ።

ትዝታ፦
ከላይ ያልተጠቀሰ ለአንባቢያን የሚሉት ነገር ካለ?

አቶ ወሰን፦
ለአንባብያን ወይም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምለው በቅርቡ ሜይ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. የምናደርገው የኮሚኒቲ ፎረም ወይም የመወያያ መድረክ ትልቅ ድልድይ ስለሚሆን ነው። የወደፊቱ ጉዞአችን ሜይ 18 ቀን በመገኘት አድራሻውን በዚሁ ጋዜጣ ላይ ማየት ይቻላል። ግን የሰው ቁጥር በዝቶ ቅድሚያ እንድናዘጋጅ፤ በፋነንሽያል ሆነ በሌላ መንገድ እርዳታ ያስፈልገናል። አዳራሽ ከመከራይት ጀምሮ ምግብ አቅርቦት ቁርስና ስናኮች ያስፈልጋሉ። ይህ ፎረም ሙሉ ቀን ነው የሚካሄደው፣ በተለይ የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች እንዲተባበሩን ጥሪ አደርጋለሁ። እንዲሁም ማስታወቂያዎችን እያወጣን ነው ደብዳቤዎች እየተዘጋጁ ነው። ድርጅቶች እስፖንሰር እንዲያደርጉን እየጠየቅን ነው። በአስተያየትም ሆነ አሁን ያለበትንም ወደፊት በማንኛውም መገንናኛ ዘዴዎች ማድረግ ይቻላል። ሜይ 18 ቀን ውጤታማ እናድርገው።

ወደፊቱ የኢትዮጵያ ቀን አለን። በዚያም እንዲሁ እርዳት እንፈልጋለን።

ከዚያ ደግሞ ሕንፃ ግዢ ውስጥ እንገባለን። ፈንድ ያስፈልገናል። በአጠቃላይ ማህበሩ በራሱ እንዲሄድ የሚደረግበትን መንገድ መፍጠር ወሳኝ ነው። ከዚያ ውጭ ምንም የለም። ወጣቶች መሳተፍ እንዲችሉ እነሱን የሚስብ ፕሮግራም ማድረግ አለብን። የሴቶች፣ የአዛውንቶች፣ የሁሉንም ቢሆን ይሄ አጭር መልእክት ነው። ኢትዮጵያ ማህበር ቤታችሁ ነው አብርን ሆነን መስራት ነው።

April 23, 2013

Posted on by   | Reply

A PATH TO A BETTER ONTARIO

Posted on by   | Reply

A PATH TO A BETTER ONTARIO

TORONTO – Ontarians deserve a province offering more jobs, growth and opportunity than we have today. But to make it happen, government needs to live within its means and follow a plan to grow more good jobs, PC leader Tim Hudak said today. “Over the past decade, a series of deliberate.....

Scholar accuses Ethiopian authorities of “ethnic cleansing”

Posted on by   | Reply

Scholar accuses Ethiopian authorities of

By Ethiomedia  April 3, 2013Dr.Yacob HailemariamWASHINGTON, DC (Ethiomedia) - Ethiopian authorities could be charged with the crimes of "ethnic cleansing" at anytime in their life, a leading law professor said on Tuesday.Yacob Hailemariam, a prominent opposition leader who previously was a senior UN Prosecutor at the Rwanda Genocide Trials, told.....

CANADIAN OLYMPIC COMMITTEE WELCOMES HARPER GOVERNMENT’S INVESTMENT IN THE AJAX PAN AM BALL PARK

Posted on by   | Reply TORONTO –Today, the Canadian Olympic Committee issued the following statement in response to the Harper Government's announced investment in the Ajax Pan Am Ball Park: “As Canada prepares to welcome the Americas to the GTA and the Golden Horseshoe area for Toronto 2015, the Canadian Olympic Committee welcomes the Harper Government’s investment.....

Speaking notes for The Honourable Jason Kenney, P.C., M.P. Minister of Citizenship, Immigration and Multiculturalism

Posted on by   | Reply

Speaking notes for The Honourable Jason Kenney, P.C., M.P. Minister of Citizenship, Immigration and Multiculturalism

Minister Kenney announces that, since 2008, the backlog of permanent resident applications has been reduced by about forty percent, paving the way for a faster and more effective immigration system in 2013 and beyond – Mississauga, OntarioAt a news conference to announce that the immigration backlog been reduced by about.....

Posted on by   | Reply በሐይል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ችግራችን ተባብሶአል ይላሉ መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም፡ ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ፣ የክልላቸው ባለስልጣናትም ሆኑ የፌደራል መንግስቱ መፍትሄ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ገለጸዋል።በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች.....