Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic, Canadian, Ethiopian, World

የትዝታ ጋዜጣ አሳታሚና ኢዲተር አቶ ተሾመ ወልደአማኑኤል ከኦንቴሪዮ ሌፍተናንት ጎቨርነር ኤልሳቤት የመዳሊያና የሰርትፊኬት ሽልማት አገኙ

Published Posted on by | By TZTA News

የትዝታ ጋዜጣ አሳታሚና ኢዲተር አቶ ተሾመ ወልደአማኑኤል ከኦንቴሪዮ ሌፍተናንት ጎቨርነር ኤልሳቤት የመዳሊያና የሰርትፊኬት ሽልማት አገኙ

አቶ ተሾመ ወልደአማኑዔል ከሌፍትናንት ጎቨርነር ሽልማት ሲቀበሉ

ቬምበር 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦንቴሪዮ መንግሥት ኩዊንስ ፓርክ በሌፍተናንት ጎቨርነር ልዩ አዳራሽ ከ6፡00 ጀምሮ ለናሽናል ኢቲኒክ ፕረስና ሚዲያ ካውንስል ኦፍ ካናዳ የክብር ተሸለሚዎችና የረዥም ጊዜ ለኮሚኒቲያቸው አስተዋፆ ላደርጉ አባላት የሜዳሊያና የሰርትፊኬት ስጦታ ተደርጓል።

ይህን የክብር ሽልማት ያበረከቱት በኦንቴሪዮ 29ነኛዋ ሌፍተናንት ጎቨርነር የተከበሩ ኤልሳቤት ዶስደዌል ሲሆኑ በእለቱ ለዚህ ክብር የተደረገላቸው 15 ኢድተሮችና አታሚዎች፤ ለዘጠኝ ጋዜጠኞች፤ ለ15 በኮሚኒቲ ስራቸው በከፍተኛ ተሳትፎ ላደርጉ ምሁራን እንዲሁም 2 በኢሌክትሮኒክስ ሚዲያ አስተዋጾ ላደረጉ ያጠቃልላል። እያንዳንዳቸው ያደርጉትን ገድል እየተነገረ ከሌፍተናንት ጎቨርነር የሜዳሊያና የሰርትፊኬት ሽልማት ተበርክቶላአቸዋል።
በዚህም እለት አቶ ተሾመ ወልደአማኑዔል የትዝታ ኢትዮጵያን ጋዜጣ አዘጋጅ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ሲሆኑ ለረዥም ጊዜ ለኮሞኒቲያቸው ላደረጉት አስተዋጾኦና አገልግሎት ከኦንቴእሪዮ ሌፍትናት ጎቨርነር የሰርትፊኬትና የመዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዚህ እለት ቤተሰቦቻቸውና ባለበታቸው ተገኝተዋል።

በተለይም በክፍተኛ ውጣና ውረድ ላጋጠማቸው ችግሮች ሳይበገሩ ጥበብ በተሞላበት አመራርና ዘዴ ለካናዳውያን ኢትዮጵያውያን ለረዥም ዓመታት አገልግሎት ሰጥተዋል። ባላቸው የዕለት በእለት ጥረት፣ ድፍረትና አመራር፣ ለኢትዮጵያዊ ባህል ዕኩልነትና ክብር ለዲሞክራሲ በካናዳ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርገዋል። ለዚህም ይህ የክብር ሽልማት ተስጥቷቸዋል። በመጨረሻም የኮክቴል ግብዣ ተደርጎ የበዓሉ ፍፃሜ ሆንዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @