Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic, Ethiopian

የኒዮሊበራሊዝምና የኢህአዴግ ግብግብ

Published Posted on by | By TZTA News

(በአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል)
ahayder2000@gmail.com
(ይህ ጽሑፍ በኅብረ-ብዕር መጽሔት ቅጽ 01 ቁጥር 02 ሕዳር 2007 እትም ላይ ታትሟል፡፡ መጽሔቱን ያላገኙ እንዲያነቡትና
ለመወያያም ይሆን ዘንድ በዚህ ዌብሳይት ላይ እንዲታተም ተልኳል)
መግቢያ
“ኒዮሊበራሊዝም” የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ በተመለከተ መጣጥፍ ለማዘጋጀት አስቤ የነበረው፤ ስለጽንሰ ሃሳቡ ምንነት፣ ታሪካዊ
አመጣጥ፣ በዓለምም ሆነ በሀገራችን ላይ ስላለው አንደምታ እና የሀገራችን ፖለቲከኞች በጉዳዩ ላይ የሚያራምዱትን አቋም በተመለከተ
ዳሰሳ ለማድረግ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፣ ጽሁፉን በማዘጋጅበት ወቅት እና ጽሁፉን ካዘጋጀሁ በኋላ ሁለት አጋጣሚዎች ተፈጠሩ፡፡
አንደኛው አጋጣሚ ለጽሁፉ ዝግጅት የሚረዳኝን መረጃ በማሰባስብበት ጊዜ እና በጉዳዩ ዙሪያ እያነበብኩ በሄድኩ ቁጥር፤ አሁን ካለው
የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አብረው ሊታዩ የሚገባቸው መሰረታዊ ሃሳቦችን ማግኘት መቻሌ ሲሆን፤ ሁለተኛው አጋጣሚ ደግሞ
በኒዮሊበራሊዝም ዙሪያ ሁለት ክፍል ያለው ጽሁፍ አዘጋጅቼ ካጠናቀቅኩ በኋላ ለአንድ የቅርብ ወዳጄ የሆነ የታሪክ ምሁር አሳየሁት፡፡
ይኸው ወዳጄ ጽሁፉን ካነበበ በኋላ “የግንዛቤ ብዥታ ያለው በኒዮሊበራሊዝም ላይ ብቻ አደለም፡፡ ‘ልማታዊ መንግስት’ በሚለው
ጽንሰ ሃሳብም ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ ያለ አይመስለኝም፡፡ በነካ እጅህ ይህንንም በተመለከተ ጻፍና በመጨረሻ በሁለቱ ጽንሰ ሃሳቦች ዙሪያ
ያለውን ልዩነትና አንድነት እንዲሁም ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በየትኛው መንገድ ቢኬድ ያዋጣል የሚለውን መነሻ ሃሳብ ጨምረህ
ብታቀርብ ይሻላል” የሚል አስተያየት ሰጠኝ፡፡
እውነቱን ለመናገር ኒዮሊበራሊዝምም ሆነ ገዢው ፓርቲ እከተለዋለሁ የሚለው የልማታዊ መንግስት (Developmental State
theory) ንድፈ ሃሳቦች ተራ ነገሮች አደሉም፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊም እንደ ዓለም ማህበረሰብ አካልም ሁላችንንም የሚመለከቱ ናቸው፡፡
ህልውናችንን የሚነኩ ናቸው፡፡ በመሆኑም፤ በአንድ በኩል ያገኘኋቸውን መረጃዎች በተበጣጠሰ መልኩ ከማቀርባቸው ጊዜ ሰጥቼና ሰፋ
አድርጌ በጽሁፌ አካትቼ ባቀርባቸው የተሻለ መሆኑን አመንኩ፣ በሌላ በኩል የወዳጄንም የተቀደሰ ሃሳብ ያለምንም ማንገራገር
ተቀበልኩ፡፡
ከነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች በተጨማሪ፤ በእውቀትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ርእዮተ-ዓለማዊ ትንተና የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች
በ1960ዎቹ ያደርጉት የነበረና ዛሬም በዚያው መንገድ ብንሄድ በየጓዳው ከምናሰማው ሮሮ፣ ሀሜትና አሉባልታ እንደሚያወጣንና ወደ
ሰለጠነው አቅጣጫ እንደሚመራን በማሰብ፤ በጉዳዩ ላይ ከእኔ የተሻለ ግንዛቤና የትንተና ብቃት ያላቸው በተለያየ የሙያ መስክ
(በፖለቲካ ሳይንስ፣ ሶሲዮሎጂ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ፣ ሕግ፣…) የተሰማሩ ሊቃውንት ተከታታይ ምሁራዊ ስራዎችን እንዲያቀርቡ
ለመገፋፋት የሚረዳ የመነሻ ሃሳብ ማቅረብን መረጥኩ፡፡ በመጽሔቱ ዝግጅት ክፍልም በኩል ይኸው ሃሳብ ቅቡልነትን በማግኘቱ
የጽሁፌን ይዘት እንደ ገና ፈተሽኩና ጽሁፉን ለጊዜው በሦስት ክፍል አዘጋጀሁት፡፡
በዚህ እትም ይዤው የቀረብኩት የመጀመሪያው ክፍል በኒዮሊበራሊዝም ጽንሰ ሃሳባዊ ምንነት፣ ታሪካዊ አመጣጥና በዓለም ላይ
በታየው አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ የሚያተኩር ሲሆን፤ ሁለተኛው ክፍል በልማታዊ መንግስት ንድፈ ሃሳብ ምንነት፣
ታሪካዊ አመጣጥና በዓለም ላይ በታየው አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ አጠር ያለ ዳሰሳ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡
በመጨረሻም፤ የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ከሁለቱ ንድፈ ሃሳቦ አንጻር ለመዳደስ ይሞከራል፡፡
በተለይም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ኒዮሊበራሊዝምን እንዲያ አገር ለማጥፋት ያደፈጠ ጭራቅ ቅድርጎ የሚያቀርበው እውነት
ኒዮሊበራሊዝም ያን ያህል የገዘፈ አጥፊ ኃይል ስለሆነ ነው? ወይስ እኛን ያልገባን ኢህአዴግን ግን ልቡሰ-ጥላው (sub consciousness)
የገረው ነገር ይኖር ይሆን? ወይስ ነገሩ ተራ የፖለቲካ ጨዋታ ነው?… ለመሆኑ ኢህአዴግ በተቀዋሚዎች ላይ ድምጹን ከፍ አድርጎ
እንዲያ የሚጮኸው እውነት ኒዮሊበራሊዝም ለሀገራችን ስጋት ስለሆነ ነው? ወይስ ኒዮሊበራሊዝም በቅጡ ገብቷቸው ከልባቸው
አምነው የተቀበሉ “ፖለቲከኞች” በሀገራችን አሉ ብሎ ነው? ወይስ ለማደናገር? ለመሆኑ ራሱ ኢህአዴግ የኒዮሊበራሊዝምን ተጽእኖ
በአግባቡ ተከላክሏልና ነው ተቃዋሚዎች ላይ ጣቱን የሚቀስረው?… ኧረ! ለመሆኑ ኢህአዴግ የከበርቴ ሀገሮችን (ሲፈልግ የልማት
አጋሮቼ ይላቸዋል) እርዳታ፣ ብድርና ድጋፍ እንክት አድርጎ እየተጠቀመ መለስ ብሎ ጭራቅነታውን ጮክ ብሎ የሚነግረን አማርኛ
አይሰሙም ብሎ ነው ወይስ አሁንም እኛን ለማደናገር?


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu