Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Breaking News

Published Posted on by | By TZTA News

Spread the love

የትዝታ ጋዜጣ አዘጋጅ በተለይ በሚመጣው መስከርም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በክርስቲ ፒት ፓርክ በሚደረገው የኢትዮጵያ ቀን አከባበር ጉዳይ የማህበሩን ፕሬዘዳንት አቶ ወስን ይጥናን ስለ አከባበሩ ጉዳይ ለአንባብያን እንዲገልጹ በሚከተለው አጭር ቃለ መጠይቅ ዘግቧል።

ትዝታ፡-
አስቀድሜ ለዚህ አጭር ቃለ መጠይቅ እንዳደርግልዎ ስለፈቀዱልኝ አመሰግናለሁ። ለመሆኑ ለመስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በዓል ምን ተዘጋጅታችኋል?
አቶ ወሰን፦
በቅርቡ ሰብቴምበር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቀን የ15ኛ ዓመቱን ያው በተለመደው በክርስቲ ፒት ፓርክ እናከብራለን። በዚህም ላይ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምን ያህል እንዳደገና እንዲሁም የተለያዩ ኢንተርቴመንቶች፣ ባህላዊ የሆኑ ሙዚቃና ዘፈን እንዲሁም የተለያዩ ምግቦችና ባህላዊ የሆኑ ቁሳቁሶች በድንኩዋን ውስጥ ይሸጣሉ። የተለያዩ የኮሚኒቲው ነጋዴዎች እቃቸውን ለማስተዋወቅና ለመሸጥ እድል ይኖራቸዋል። በተጨማሪ ተቋማቱ ቢዝነሳቸውን ያሳውቃሉ ማለት ነው። ሌላው የልጆች ተሳትፎ ይኖራል፣ የወጣቶችም እንዲሁ። ከቶሮንቶ አካባቢ ለምሳሌ ከኪችነር የሚመጡ በተለያየ ተሳትፎውስት የሚገኙ ይኖራሉ።እንዲሁም ደግሞ የቢራ መጠጫ ቦታም አለ አመታዊ መጽሔትም እየተዘጋጀ ነው። በመጽሔቱ ላይ የተለያዩ ነጋዴዎች የንግዳቸውን ማስታወቂያ ያወጣሉ።
ትዝታ፦
በቅርቡ የኢትዮጵያ ቀን ሲከበርከአምናው ዘንድሮ ለየት ያለ ነገር ካለ?
አቶ ወሰን፦
ጥያቄው የዚህ አመት የኢትዮጵያ ቀን የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው ለሚለው መልስ የተለየ የሚያደርገው ሁላችንም እንደምናውቀው የኢትዮጵያ መሃበር ላለፉት ሁለት ሶስት አመት ተደራራቢ የሆኑ ችግሮች ደርሰውበት ነበር የባጀት ችግር ነበር ከዚያም አልፎ የቦርድ አባላት ችግር ነበር ያለመግባባት ነበር አሁን እነዚህን ችግሮች ወደሁዋላ ጥለን በተለይ ሜይ 18 በተደረገው ጉባዔ ሁሉን አንድላይ ያቀራረበ ባንድነት በመተሳሰብ ለመሃበራችን እድገትና መሻሻል ቃል የገባንበትና መሃላ ያደረግንበት ስለሆነ በዚህ አመት የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር በዚህ መንፈስ ይሆናል፤ ሁሉን ነገር በጋራ በደስታ የምናከብርበት ይሆናል ማለት ነው። በዚህም ላይ እንግዶች ተጋብዘዋል በአካባቢያችን ያሉ የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም ሌሎች አባቶችና የሃይማኖት መሪዎች ተጋብዘዋል፣ እንግዲህ ይሄ አመት በጣም በጥሩ ሁኔታ እንደምናከብር ነው የሚሰማኝ የበለጠም ቃል የምንገባበት ይሆናል ።
ትዝታ፦
ልዩነቱን ብትገልጽልኝ?

አቶ ወሰን፡-
በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ። ይሄ በአል ይሄ ቀን የህዝቡ ነው። ለመሃበሩ ተመርጠውም ሆነ በፈቃደኝነት የሚሰሩት ያው ለህዝቡ ነው። ይሄ በአል የመላው ኢትዮጵያ ኬኔዲያን አባላት በሙሉ ማንኛውም አባላት ወይም ኢትዮጵያውያን ለሚያፈልግ ነገር በሙሉ ለመጠየቅ ለመረዳት 1950ዳውን ፎርላዝ አቪኒው በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 416-694-1522 በመደወል ምን እናግዝ ምን እንርዳ በማለት የጋራ በአላችንን በጋራ ለማክበር መዘጋጀት አለብን። በአሉ የሁላችንም ነው ማለት መቻል አለብን። በተለይም ወጣቱን ከፍል አደራ የምላው በተለያየ ሁኔታ መሳተፍ እንዳለባቸውነ የምገልጸው።

ትዝታ፦
አሉ የምታቸው ደካማ ጎኖች ብትገልጽልኝ?
አቶ ወሰን፦
ጥሩ ጥያቄ ነው ባለፈው አመትና በዚህ አመት በተለይ ከማዘጋጃበት ወይም ሲቲሆል ቶሮንቶ የምናገኘው ፈቃድ ማለትም ለፓርኩ ለምሳሌ ህዝቡ በደንብ እንዲረዳና እንዲያውቅ የምፈልገው የተከለከሉ ነገሮችን እዚያ ውስጥ ማድርግ የተሰጠንን ፈቃድ ሊያሳጣን ይችላል። በአላችንን ለማክበር ላንችል እንችላ፤ ለምሳሌ ፓርክ ውስጥ መኪና ማስገባት ለምንም ምክንያት ቢሆን የተከለከለ ነው፣ የተከለኩሉ መጠጦችን መሸጥ ለምሳሌ ጠጅ ጠላ አረቄ የመሳሰሉትን ለኛ ባህላችንና በአላችን ቢሆንም በካናዳ ህግ ደግሞ ፓርክ ውስጥ የተከለከለ ነው። ሌላው ከፍተኛ ድምጽ ማዘጋጃ ቤቱ የሚሰጠን ገደብ አለ እሱም መድረክ ላይ ሲሆን እሱም የድምጹ መጠን አለው፣ በየ ድንኳን ውስጥ የድምጽ ጩኽትም እንዲሁ የተከለከለ ነው፣ በአካባቢ የሚኖሩትን ሊረብሽ ስለሚችል ነው። የተፈቀደው መድረክል ላይ ብቻ መሆኑ እንዳይዘነጋ! ሌላው ደግሞ የሴኩሪቲ ጉዳይ ነው በዚህ ቀን ክ10 እስከ 15ሺህ ሰው ይመጣል ብለን እንገምታለን፤ ስለዚህ በአሉን በሰላም አክብረን ደስ ብሎን ወደ የቤታችን እንድንሄድ እያንዳዳችን በዕለቱ ያሉትን ፖሊሶችም ሆኑ ጠባቂዎችን ማገዝ መተባበር ይኖርብናል። ሌላው ደግሞ ጽዳትን በተመለከተ የተጠቅምንብትንም ሆነ በየቦታው የውደቁ ቆሻሻዎችን ማንሳትና በተገቢው ቦታ መድረግና መተባበርና መረዳዳት በአሉ ያንድና የሁለት ሰው ብቻ ሳይሆን የሁላችንም መሆኑን ያለመዘንጋት የውዴታ ግደታ አለብንና; ቅድም እንደጠቀስኩት ይህን ዝግጅት ማንም አይደለም እኛው እራሳችን ነን በፈቃደኝነት የሚሰሩና በመደበኝነት የሚሰሩ የኮሚቴ አባላት ጋር ነው ሲሰራ የቆየው፣ አሁን ግን በርከት ያለ አቅምና የሰው ሃይል ያስፈልገናል። ባለፈው አመት በጣም ጥሩ አደርግን የምለው ከመሃበሩ ምንም አይነት ወጭ ሳይወጣ ባሰባሰብነው ገንዘብ የተሸፈነው በዚህም አመት እንዲሁ ይሆናል እላለሁ። ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ፈንድ ሬዚንግ ወይም የገንዘብ ማሰባሰቢያ እየፈጠርን ለምሳሌ ማንኛውም ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ ኢትዮጵያ መሃበር ቢሮ እየመጣ የቻለውን ያህል መለገስ ይችላል በተጨማሪ ከላይ እንደጠቀስኩት ብዙ እንግዶች አሉን ሜሩም ይመጣሉ።
ትዝታ፦
ምን መልክት አልህ ?
አቶ ወሰን፦
ብዙዎቹ ያውቁታል ግን በኔ ሃሳብ ለየት ያሉ እቃዎችን ማቅረብ ዋጋውን ተመጣጣኝ ማድረግ ብዙ ገዥዎች ይኖራሉ። ገዥዎችም ደግሞ አይ እኔ ኢትዮጵያ ስሄድ አመጣለሁ ወይም ሰው ያመጣልኛ ከማለት በተቻለ መረዳዳት ነው። ሌላው የልጆች የሆነ ነገር እንደ መጽሐፍ ዲቪዲ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ የመሳሰሉ ነገሮችንቢኖሩ፣ ይሄ አሁን የምሰጠው ሃሳብ ግላዊ ነው ።
ትዝታ፦
ወጣቶች እንዲሳተፉ ምን አሳብ ተሰጣለህ?
አቶ ወሰን፦
ጥሩ ጥያቄ ነው የዛሬ 30፣ 25ና 20 አመት የመጡ የልጅ ልጅ የማየት ደረጃ የደረሱ አሉ እና ከዚህ በኋላ ልጆቹን ወጣቶቹን የማቅረብ ግዴታ አለብን፤ ከነሱ ብዙ እንማራለን እዚህ ያሉ ወጣቶች ብዙ አወንታዊ የሆኑ ለውጦችን ሊያመጡ ስለሚችሉ ከንሱ ጋር ማቅረብ መቀራረብ ያስፈልጋል። የበአል ዝግጀት ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ወጣቶችን ሊስብ የሚችል ለነሱ ተጠሪ ሊሆን የሚችል ዝግጅት መኖር አለበት፤ ብዙ ጊዜ የምናዘጋጀው አዋቂውን ክፍል የሚያሳትፍ ብቻ ስለሆነ ወጣቶችና ሕጻናቶችም የሚያካፍል መኖር አለበት። ምእንዲሁ በአሁኑ ሰአት የአማርኛ መማሪያ ክፍል በየሳምንቱ እሁድ አለን። ወደ 20 የሚሆኑ ተማሪዎች ይሳተፋሉ ምን መሆንና ማድረግ እንደአለባቸው የነሱ የሆነ ፕሮግራም አላቸው። አንድ ወጣት ኮርድኔት የምታደርግ አግኝተናል ወጣት እርብቃ ትባላለች በእስዋ አማካኝነት ይሰባሰባሉ። ሌላዋ ወጣት ጅቱ የምትባለዋ ደግሞ እሷም እንዲሁ የሰመሩ መጠነኛ ፕሮግራም ላይ ትሰራለች ማለት ነው እየሞከርን እንገኛለን።
ትዝታ፦
የኢትዮጵያ መሃብር እስከ ዛሬ 5 አመት የት ይደርሳል ?
አቶ ወሰን፦
ከምኞት ጋር ሊሆን ይችላል። መለወጥ ያለባቸው ነገሮች በሃሳብ ደረጃ አሉ። በ15 አመት ውስጥ አንድ ደረጃ መድረስ በጣም ቀላል ነበር፣ ሄደንበታል። ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮች ይኖራሉ። የምንጨምራቸው ወይም የምንቀንሳቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ትልቅ መሆን አይደለም ለኔ ማደግ፣ የዛሬ 5አመት ከክርስቲ ፓርክ ትልቅ ቦታ ልንሄድ እንችላለን፣ ነገርግን ቁም ነገሩ የፓርኩ ትልቅነት ሳይሆን የህዝቡ ቁጥር መጨመር ከህጻናት ጀምሮ እስከ አዛውንት በበአሉ የተደሰቱ መሆናቸውን አመቱን በሙሉ ሲያወድሱ ሲያስታውሱ ደስታቸውን ሲገልጹ በተለይ ደግሞ አቅም የሌላቸውን እራሳቸውን መርዳት የማይችሉትን መርዳት መቻልና ለነሱ የሆነ ዝግጅት ማዘጋጀት አልፈን ሌሎችን መርዳት የምንችል መሆን ይኖርብናል። ትንሽ ወጣብለን ማሰብ መቻል ይኖርብናል። እኛ ይሄ ይሆናል ብለን ከምናስበው የኢትዮጵያ ንግድ ያላቸውን የሚስብ እንዲሁም ጥሩ ነገር በመስራት ያደጉ ወገኖችን ማስተዋወቅና ማወደስ ሲሆን በኮሚኒታችን ውስጥ ጥሩ ነገር የሰሩን ማድነቅ ብዙም ባይታይብንም ይህንን ንገር ወደፊት ማድረግ እንዳለብን መረዳት ነው። በትምህርት የደከሙትን ደግሞ መርዳት መደገፍ አለብን ቅድም እንዳልኩት 40እና 50ሺህ በጣም በተወጣጠረ ሁኔታ ሳይሆን በካንፓኒ ደረጃ የሶሻል ኢንተረስት አልን ብለን የምንሰርው ስራ መሆን አለበት ማንኛውም በመሃበር ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ወደፊት ስራ ለሰሪው በሚለው መሆን አለበት የኢትዮጵያ መሃበር የዛሬ 5 አመት እኔ ግዜው ፈቅዶልኝ ብሰራ ሌሎችስ እንዴት ነው የሚሳተፉት ብዬ አስባለሁ።
ትዝታ፦
ከላይ እኔ ያልጠቀስኩት የሚሉት ካለ?
አቶ ወሰን፦
ኢትዮጵያውያን ኬኔዲያን 15አመቱን በሚያከብርበት ቀን እንዲሁም የኢትዮጵያ የዘበን መለወጫ ወይም እንቁጣጣሽ አንድላይ ነው የሚከበረው፣ ስለዚህ ለኛ በቻ ሳይሆን እዚህ ደግሞ ተወልደው ላደጉት ልጆች ጭምር ለዚያም ነው ኢትዮጵያን ኬኔዲያን ቀን ብለን ስም የምንሰጠው ምንም ሰው የኔ ሊለው የማይችለው የሁሉም ኢትዮጵያዊ በአል ነው እንዲያውም ሌሎችም አፍሪካን ኬኔዲያን ጭምር ሲሆን ጎደኞቻችንን መጋበዝ መቻል አለብን። በዚህ አጋጣሚ በጣም ማስገንዘብ የምፋልገው የትዝታ ጋዜጣን አዘጋጅ አቶ ተሾመን ማመስገን ነው እጅግ በጣም አመሰግናለሁ በመሃበራችን ስም በሁልጊዜ ትብብርህና ያለክፍያ ማስታወቂያዎችን በጋዜጣው ላይ በማውጣትህ አመሰግናለሁ።
ትዝታ፦ አቶ ወሰን ስለሰጡን አጭር ቃለ መጠይቅ እናመሰግናለን።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu