Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Breaking News

Published Posted on by | By TZTA News

Spread the love

     
     ባልፈው ሃምሌ ወር ውስጥ ብቶሮንቶ የምገኙ የሙስሊም ህብረተሰብ ድምፃችን ይሰማ በማለት በቶሮንቶ ከተማ በኢትዮጵያ ቆንሲል ፊት ለፊት ጩኸታቸውን በማስማት ልዩ ልዩ መፈክሮችን በመያዝ ስላማዊ ሰልፍ አድርገውል። የሙስሊሙ መሪ ቢስምላሂ ሮህማን ሮሂም በማለት ከዚህ የሚቀጥለውን ንግግር አስደምጠዋል።

“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣
ዛሬ እዚህ የተሰበሰነው ድምጻችንን ከፍ እያደረግነየጪህን ያለነውና፣ በመላ አገራችን የሚኖሩ ሙስሊሞች ከአንድ አእመት በላይ በየጁማው ድምፃችን ይሰማ እያሉ ያለቀሱትና የጮኹት፣ ሕገ መንግሥት ያረጋገጠላቸውን ሃይማኖታዊ መብት እንዳይጠቀሙ ለማደናቀፍ፣ መንግሥት በሃይማኖት ሥራ ጣልቃ በመግባት፣ እየወሰደ ያለውን የመብት ጥሰት፣ እስራትና ግርፈት፣ በመቃወምና የዲናችንን ሕልውና ለመጠበቅ እየተደረገ ያለውን መስዋእትነት ለመዘከርና በዚህ በተከበረ ወር ያለንን አንድነትና ጽናት እንዲሁም የትግል አጋርነትና አብሮነት ግልጽ ለማድረግ ነው። እንዲሁም ለዜግነት መብታቸውና ለዲናቸው ሲሉ የታሠሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና መሪውችን በተጨማሪም የእምነትና የዜግነት መብታችን ለድርድር አናቀርብም በማለት እየታገሉ ያሉ ሙስሊም እህቶቻችንና ወንድሞቻችንን፣ አይዟችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን እያልን፤ በጽናት፣ በአደብ፣ በሰላማዊና ሕጋዊ መንግድ ለትግሉና ለታጋዮች ያለንን አጋርነትና ጽናት በዓለም አካባቢ ጎልቶ እንዲሰማ ለማድረግ ነው።
እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግሥትና ጽናት ያለን አብሮ ነዋሪና ስላማዊ ዜጎች ስንሆን፣ ለአገራችን ልዕልናና እድገት፣ ለብልጽግናውና ተስፋዋ መስዋእት የምንሆን ጠንካራን አይቤሬ ዜጎች ነን።
ከሁሉም በላይ ግን የዲናችን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርብ፣ ዲናችን ሲነካ አውራው እንደተነካ ንብ ሆ ብለን የምንነሳ ቆራጥ አርበኞችና የሰላም መልዕክተኞች መሆናችንን ባለፈው አንድ አመት ተኩል ይታየውና የተዘገበው ሰላማዊው የሙስሊም እንቅስቃሴ ዓብይ ምስክር ነው።
ዛሬ እንዲህ ባንድ ቁመን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ረጋ ብሎ አስቦ ከሚሰራው ድራማና አጉል ውንጀላ ተቆጥቦ፣ የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ በአንክሮ መመልከት መፍትሄ መሻት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ልናስገነዝበው እንወዳለን።
* የምፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አሁኑኑ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።
* በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይቁም እንላለን።
* አህባሽ አይጫንብንም፣ ተቋሞቻችንም አይነጠቁም፤ ኢማሞችም በቦታቸው ይመለሱ፣ቂራቶች ይከፈቱ እንላለን።
*ማሰር ማሸበሩ ይቁም፣ በማሸበር የተገነባ አገር የለምና
እንላችዋለን።
* ሕገ መንግሥቱ ይከበር፣ ለሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ፍታሃዊ መልስ ይሰጥ። እንላለን።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለዲናቸውና ለመብታቸው ለሚያደርጉት ሰላማዊና ሕጋዊ እንቅስቃሴ አጋርነታችን ደግመን እየገለጽን፣ ጥያቀዎች እስከሚመለሱና መሪዎች እስኪፈቱ በአንድነት በጽና ታግሉን እንዲቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን።
እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ በእልህ ሳይሆን በአወንታዊ አመለካከት፣ በጉልበት ሳይሆን፣ በጥበብና በብስለት መመልከት፣ አወንታዊ መፍትሄ በመሻት አገራችንን ሕዝቧን ወደ ሰላማዊ የእድገት ጎዳና እንዲመራት ጥሪ እናቀርባለን። ኣላህ ክበር! በማለት ንግግራቸውን ቋጭተዋል።
በዚህ ሰልፍ ላይ የተለያየ መፈክሮች አሰምተዋል። እነዚህም፣ ሕገ መንግሥቱ ይከበር፤ ድምፅጻችን ይሰማ፤ የመንግስት ጣልቃገብነት አጥብቀን እንቃወማለን፤ መንግሥት እጁን ከህይማኖት ተቋማችን ላይ እጁን ያንሳ፤ ጥያቄዎች ይመለሱ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ በየክልሉ የታሰሩ ንፅሃን ዜጎች ይፈቱ፤ የኝፁሃንን ሕይወት ያጠፉ ለፍርድ ይቅረቡ፤ ድራማው ይብቃ፣ የተባረሩ ኢማሞች ወደ ቦታቸው ይመለሱ፤ የሙጅሊሱ አመራሮች ሙስሊሙን አይወክሉትም፤በጓሮ በር ገብተው ሙጅሊሱን የተቆጣጠሩ የመንግሥት ካድሬዎች ይውረዱ የሚል ነበር። በእንግሊዘኛም የተፃፍ መፈክር ተንጸባርቋል።
ስለዚህ ሰላማዊ ሠልፍ አንዳንዶችን አነጋግረን ነበር።
ስምዎን ማን ልበል?
ስይድ እባላልሁ።
ለምን ዛሬ ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ተገኙ?
ዛሬ አገራችን ያለውን እንቅስቃሴ አብሮ ለማካሄድ እንደምንችል የሚያሳይ ነው። እኛም እንዲሁም በአለም ላይ ያሉ የኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን ለመግለጽ ነው። በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ መንግሥት የሚያደርገው ድርጊት ለካናዳ መንግሥት ብሶታችንን መልክታችንን ለማስተላለፍ ነው። እንደገናም ለኢትዮጵያ መንግሥት ድምፃችንን ለማሰማት ነው።
ሌሎችም ተቃዋሚዎች አሉ፣ ለምን አብራችሁ ድምፃችሁ እንዲሰማ አላስተባበራችሁም?
ይሄ የጭር ጊዜ ዝግጅት ስለሆነ ነው። ሆኖም ከአሁን በፊት አብረን በመሆን ድምጻችንን አሰምተናል። ወደፊትም እንዲሁ ይሆናል። ለጊዜው የጊዜ እጥረት የተነሳ ነው። ግን አጋርነታችንን አብረን አሳይተናል።
ከመፈክር ሌላ ምን ታደርጋላችሁ? ስቴትመንት አለን እንሰጣችዋለን፤ ከዚህ በፊት ሰጥተን ግን መልስ የለም። ዛሬም እሰቴትመንቱን እናሰማለን።
በተጨማሪም አንዷን የሙስሊም ሴት ለምንድን ነው ዛሬ ሰላማዊ ሠልፍ የወጣሽው ስላት፤ …የኢትዮጵያ ጉዳይ በጣም አሳዝኖኝ ነው። ለምንድን ነው ሰው በሃገሩ መብት የማይኖረው ብዬ ነው የወጣሁት በማለት ተናግራለች።
ድምጻችውን በሚያሰሙበት ጊዜ ሃላፊ አግዳሚው መኪና ያለው በጥሩምባ የሌለው እጁን በማወዛወዝ አጋርነቱን ገልጿል።

 

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu