Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic

Published Posted on by | By TZTA News
Spread the love

በሐይል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ችግራችን ተባብሶአል ይላሉ

መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም፡ ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ፣ የክልላቸው ባለስልጣናትም ሆኑ የፌደራል መንግስቱ መፍትሄ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ገለጸዋል።

በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከመሀል ከተማ እንዲወጡ ተደርገው፣  ባከል እየባለች በምትጠራ ገጠራማ ቀበሌ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መገደዳቸውን በባከል ቀበሌ የሚገኙ አንድ አርሶደአደር ተናግረዋል::

ህጻናት፣ እርጉዝ ሴቶች እና በሽተኞች ሳይቀሩ ቀን በጸሀይ፣  ሌሊት በብርድ እያንዳንዷን ቀን እንዲያስልፉ መገደዳቸውን የ3 ልጆች አባት የሆኑት አባ ወራ በሀዘን ይገልጻሉ

በመጀመሪያው ዙር ተፈናቅለው በባህርዳር ከተማ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል አንድ አርሶአደር የክልሉ ባለስልጣናት ጉዳዩ የክልል ስድስት ጉዳይ በመሆኑ ክልል ሶስት አያገባውም የሚል ምላሽ እንዳገኙ ከባህርዳር ተናግረዋል።


አርሶ አደሩ ከአማራ ክልል መንግስት ተስፋ አስቆራጭ መልስ ሲያገኙ ወደ ተፈናቀሉበት ክልል ተመልሰው ጥያቄ ማቅረባቸውን ይሁን እንጅ ያገኙት መልስ ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን ገልጸዋል

አርሶአደሩ በሌሎች ክልሎች ሄዳችሁ መስራት አትችሉም ከተባልን የክልሉ መንግስት መሬት ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻቸው  ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጡትም ተማጽነዋል

በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም እያወገዙት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በማናቸዉም የኢትዮጵያ ግዛት የመኖርና የመስራት መብት እንዳለዉና ይህም እስኪረጋገጥ ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል ገልጿል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ድርጊቱ  የዐማራውን ዘር የማጥፋቱ ዘመቻ አንድ አካል ነው በማለት ኮንኗል።

በአማራ ተወላጆች ላይ የተዶለተዉ ሴራ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተዶለተ ሴራ አካል ነዉ በሚል ርእስ ድርጊቱን ያወገዘው ሌላው ድርጅት ደግሞ ግንቦት7 የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የነጻነት ንቅናቄ ነው።  ንቅናቄው  በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በማነጣጠር እየተፈጸመ ያለው የማፈናቀልና  የማጥቃት  እርምጃ በአገሪቱም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ሁሉ  በዘረኝነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ  በደል ነው ብሎአል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ኢሳት የሁለቱ ክልሎች ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረግ መጀመራቸውን ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ በድጋሜ ጠየቀ

መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በዘፈቀደ የሚካሄዱ እስሮችን የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  አካል የሆነው ፍሪደም ናው የተባለው ተቋም እንደገለጸው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አስሮ እስካሁን ማቆየቱ አለማቀፍ ህግን የሚጻረር ነው ።

አምስት ገለልተኛ ፓናሊስቶች የጋዜጠኛ እስክንድርን እስር በመመርመር፣ እስሩ ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ፣ ጋዜጠኛው በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጋዜጠኛው አያያዝ እና የፍርድ ሂደት አለማቀፍ ህጎች የሚሉትን የተከተለ እንዳልነበር ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጸረ ሽብርተንነት ህጉን በመጠቀም የግል ጋዜጠኞችን ማፈኑን ማቆም አለበት በማለት የፍሪደም ናው ዋና ዳይሬክተር ማራን ተርነር ተናግረዋል። ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ብቻ ሳይሆን እውነተኛ የጸጥታ ስጋቶችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረትም የሚያሰናክል ነው በማለት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ፍሪደም ናው ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነጻ ህግ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል

አልጀዚራ ከታነቀ በኋላ ጠንካራ ሪፖርት አቀረበ

ጎልጉል፡ የአልጀዚራ የቴሌቪዥን ስርጭት ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይተላለፍ መደረጉን አልጀዚራ ድርጊቱን በመቃወም ያስታወቀው በሳለፍነው ሳምንት ነበር። ጣቢያው ስርጭቱ የተቋረጠበትን ምክንያት እንዲገልጹለት ኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ቢያቀርብም መልስ እንዳልተሰጠው አስታውቋል። አልጀዚራ የቢቢሲ የስለላ ሪፖርት የኢትዮጵያን መንግስት ባጋለጠ ማግስት ማስተባበያ የሚመስል ስርጭት አስተላልፎ እንደነበር የሚያስታውሱ መንግስትን በመደገፍ መልኩ ሳይሆን አልጀዚራ ለበርካታ ጉዳዮች ሽፋን እንደማይሰጥ በመጥቀስ “የጁን አገኘ” ሲሉ ተጠምደዋል። አልጀዚራ በወቅቱ የምግብ እህል ርዳታ ለፖለቲካ አላማ ይውላል በተባለበት ቦታ አርሶ አደሮች ቤታቸው ድረስ በመግባት ነበር ሰፊ ከኢቲቪ የበለጠ ሪፖርት ያቀረበው።

የአልጃዚራ ድረገጾች እንዲታነቁ የተደረጉበት ዋናው ምክንያት የቴሌቪዥን ጣቢያው ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ በሰጠው ሽፋን እንደሆነ አመልክቷል። እንደ ጉግል የመረጃ ትንተና በኢትዮጵያ ውስጥ የእንግሊዝኛው ድረገጽ ባለፈው ዓመት ሀምሌ ወር 50ሺ ተጠቃሚ የነበረው ሲሆን፣ በመስከረም ወር የተጠቃሚው ቁጥር ወደ 114 ወርዷል። የአረቢኛው ድረገጽም ከ5,371 ተጠቃሚዎች ወደ 2 መውረዱን ያሳያል። ይህንን መረጃ የዘረዘረው አልጀዚራ ይህ መረጃ የሚያሳየው ጣቢያው በነሃሴ ወር የኢትዮጵያ መንግስት በእምነት ጣልቃ እንደሚገባ ካስተላለፈ በኋላ በተወሰደው የእግድ ርምጃ መሆኑንን አመልክቷል። አልጀዚራ ከታገደ በኋላ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታና የጋዜጠኞችን እስር በስፋት በዶክመንታሪ መልክ አቀናብሮ አስተላልፏል።

አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!!

ጎልጉል፦ በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር “እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን” ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

የውሃ ችግር ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን፣ በዚህም ቢሆን እንደ ልብ ማግኘት እንደማይቻል አመልክቷል። በስፍራው ያለውን የውሃ ችግር አስመልክቶ ሎጊያ የሚገኝ ጎልጉል የአይን ሪፖርተር አስተያየቱን እንዲሰጠን ጠይቀነው የበኩሉን ማጣራት ካደረገ በኋላ ችግሩ መኖሩን አረጋግጦልናል። ቡሬ አካባቢ ያለው ውሃ ችግር በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም በተመሳሳይ የሚቸገሩና በድርቅ የተመቱ ቦታዎች እንዳሉ አመልክቷል። አንዳንድ የወታደር ተሽከርካሪዎች ውሃ እንደሚሸጡ መረጃ ማግኘቱንም ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu