Logo

Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
ad ad ad ad ad

Amharic News, Breaking News Amharic, Ethiopian

Published Posted on by | By TZTA News

Spread the love

በአለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢሕአዴግ ጐጠኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲሽር የአፋኝ አመራሩ ቁንጮዎች ከትከሻው እንዲወዱ፤ ኢሕአዴግ/ወያኔን አውርዶ ያሻውን መሪዎችን በነፃነት መርጦ እንዲሰይም ሲጠይቅና ስሞታ ሲያቀርብ አያሌ አመታትን አሳልፏል። ግንቦት 1997 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ መሻት የሚፈጸምበት፣ ዓላማው ግብ የሚመታበት መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም ቅሉ በጐጠኛ አስተዳደሩ ኢ-ሰብዓዊ የጨቁነህ ግዛ እርምጃ፣ በአገዛዙ በተሾመው የምርጫ ቦርድ ፍርደ ገምድልነት ተኮላሽቶ ቀርቷል:: የአመራሩ ግፍና ጭካኔ ተዘርዝሮ የማያልቅ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጽም እኔን እስካልበረደኝ ድረስ ምን አገባኝ በማለት ቸል ላልነውም ለኛ ለለዘብተኛ ኢትዮጵያውያን ሀፍረት የሚያከናንበን መሆኑን ልብ ይሏል:: በምርመራ ስም እንድ አገዛዙ የፕሮፖጋንዳ አጠራር “ሽብርተኞች” ነገር ግን በእውነታው የነጻው ፕሬስ ባለሙያዎችና የነጻነት ታጋዮች ላይ የሚደረገው ሰቆቃ ባሳለፍነው 3 ሳምንታት አጸያፊ ይዘት ያላቸው ካላቸው ክስተቶች መካከል አንዱ ነው። በግንቦት 7 የፍትህና የነጻነት ንቅናቄ ሪፖርት መሰረት “በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው” ይላል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ጦማርያን፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
የነጻነት ትግሉ የደበዘዘ ቢመስልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ ጥያቄዎች፣ መፈክሮች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል– ከእነዚህም የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሙስሊሞች፣ ኦርቶዶክሶ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች … ወዘተ ይገኙበታል። ከእነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተለይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያለ በጽናት ሲታገል ሦስት ዓመታትን አሳልፈዋል። እነዚህ ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በሚል ጥያቄያቸው ብቻ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
የክርስቲያን ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው ኢሰላማዊ አሸባሪ ድርጅት ላይ የኢሕአዴግ አገዛዝ፣ በአገዛዙ በተሾሙት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ፓትርያርክ የቸልተኛነት አቋም ተወስዷል ብለው ራሱ ኢሕአዴግ/ወያኔ በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዋቸውን ባሰሙ ዜጎች ላይ አገዛዙ የፈጸመው ድብደባ እና እንግልት የጭቆና አገዛዙን የሚያጋልጥ ድርጊት መሆኑን መገንዘብ ተችሏል:: ወያኔ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው በወገኖቻችው ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ አስመልክቶ ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች እነርሱም ተደብድበዋል፤ ወደ ጅምላ እስር ቤቶች ተግዘዋል። ኢስላማዊው አክራሪ አይሲስ የፈጸመውን አሰቃቂ ወንጀል ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ ጋር ለማገናኘት ብሎም የሐሰት ወሬ ለመንዛት በወያኔ ከመጋረጃ ጀርባ አቀነባባሪዎች አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣት ዜጎች ስደት በምክንያትነት የሚያቀርቡት ሕገ ወጥ ደላሎችን ብቻ ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጎጠኝነት እና ግጭት በኢትዮጵያውያን መካከል እንዲፈጠር ለማድረግ ያለመ ዕኩይ ዓላማ ነው።
ሌላው የወያኔ ጨቋኝነት መገለጫ የ2007 ዓ.ም ምርጫ ነው:: በዚህ ምርጫ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌላው ዓለም ተሰምቶና ተደርጎ የማይታወቅ የ100% አሸናፊነት የምርጫ ውጤት:: ይህ ውጤት በአምባገነኑ በደርግ ዘመን እንኳን ያልተፈፀመ የረገጣ ውጤት ነው:: ለአንድ ተቃዋሚ እንኳን አንድ ወንበር የተነፈገበት የስስት ምርጫ ነው:: ይህ ውጤት እንኳን ዴሞክራሲ በሰፈነባቸው ዓለማት ቀርቶ ስለዴሞክራሲ ያልሰሙና በጭቆና ውስጥ ያሉ ሀገሮች የይስሙላ ምርጫ ቢያካሄዱ እንኳ አሸናፊው አካል 100% ውጤት አያገኝም፤ እንኳን ጉድለት ባለባቸው ምድራውያን ገዢዎችና መንግሥታት ቀርቶ 100% ፍፁም በሆነውና ምንም ጉድለት በሌለበት በእግዚአብሔር መንግስት እንኳ አንድ የተቃዋሚ ወንበር አለ (ሳጥናኤል) ታዲያ ወያኔ ከእግዚአብሔር በልጦ ነው አንድ ተቃዋሚ እንኳን አጣሁ እያለ የሚያላዝነው?ኡ.ኡ.ቴ…¡¡
በመጨረሻም ሃገር ወዳድ የሆነ ማንኛውም ዜጋ ቢሆን የወያኔን የግፍ አገዛዝ በተባበረ ክንድ ለመጣል ቸልተኛነት እንዳያሳይ እያሳሰብኩ እግዚአብሔር ሃገራችን ኢትዮጵያን በቸርነቱ ይጠብቅልን ብዬ ጦማሬን እቋጫለሁ::
አባ ኃይለጊዮርጊስ ድንቅነህ Abba Haile Georgis Dinkneh – Wetzlar – Germany ኦገስት 2015 ዓ.ም


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Comment validation by @

 
Logo
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu
Webmaster Savas Can Altun Teknoloji Bilgisayar Google s4v4s ASk Question Webmaster Sitesi Webmaster Forumu